የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwex ርዕስ 12
  • ሐቀኝነት የሚያስገኘው ውጤት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሐቀኝነት የሚያስገኘው ውጤት
  • የይሖዋ ምሥክሮች ተሞክሮዎች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ያለብኝን የጤና ችግር መቋቋም የምችለው እንዴት ነው?
    ንቁ!—2008
  • ከአንባቢዎቻችን
    ንቁ!—2008
  • ተቃዋሚ የነበረ ሰው እውነትን ተማረ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
  • በትንሣኤ እስክንገናኝ ድረስ
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2022
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋ ምሥክሮች ተሞክሮዎች
ijwex ርዕስ 12
አንድ ሰው ቦርሳውን ረስቶ ከካፌ ሲወጣ።

ሐቀኝነት የሚያስገኘው ውጤት

በደቡብ አፍሪካ የምትኖር ዳኒዬል የተባለች የይሖዋ ምሥክር በአንድ ካፌ ውስጥ የተረሳ ቦርሳ አገኘች። በቦርሳው ውስጥ ገንዘብና ክሬዲት ካርዶች የያዘ ዋሌት ነበር። ዳኒዬል ቦርሳውን ለባለቤቱ መመለስ ስለፈለገች በቦርሳው ውስጥ አድራሻ ወይም ስልክ ቁጥር ለማግኘት ሞከረች፤ ሆኖም ያገኘችው የሰውየውን ስም ብቻ ነው። ሰውየው በሚጠቀምበት ባንክ አማካኝነት አድራሻውን ለማግኘት የሞከረች ቢሆንም አልተሳካላትም። ሆኖም ዳኒዬል ተስፋ አልቆረጠችም፤ በቦርሳው ውስጥ ባገኘችው የሐኪም ቤት ደረሰኝ ላይ ወዳለው ስልክ ቁጥር ደወለች። ስልኩን ያነሳችው በሐኪም ቤቱ የእንግዳ መቀበያ ክፍል የምትሠራ ሴት ነበረች፤ እሷም የዳኒዬልን ስልክ ቁጥር ለሰውየው ለመስጠት ተስማማች።

ሰውየው ከሐኪም ቤቱ ተደውሎ ዳኒዬል ቦርሳውን እንዳገኘችውና ልትመልስለት እንደምትፈልግ ሲነገረው በጣም ተገረመ። ከዚያም ቦርሳውን ለመውሰድ ዳኒዬልንና አባቷን አገኛቸው። እነሱም አጋጣሚውን ተጠቅመው፣ እሱን ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት ያደረጉት ለምን እንደሆነ አስረዱት። የይሖዋ ምሥክሮች በመሆናቸው ምክንያት የመጽሐፍ ቅዱስን መመሪያዎች ለመከተል ጥረት እንደሚያደርጉ ገለጹለት። ምንጊዜም ሐቀኝነት ለማሳየት የሚሞክሩት ለዚያ እንደሆነ ነገሩት።—ዕብራውያን 13:18

ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ሰውየው ለዳኒዬልና ለአባቷ የጽሑፍ መልእክት በመላክ ቦርሳውንና ዋሌቱን ስለመለሱለት በድጋሚ አመሰገናቸው። እንዲህ በማለት ጽፎላቸዋል፦ “እኔን ለማግኘት ላደረጋችሁት ከፍተኛ ጥረት በጣም አመሰግናችኋለሁ። ስላገኘኋችሁ በጣም ደስ ብሎኛል፤ ያሳያችሁኝን የወዳጅነት መንፈስ መቼም አልረሳውም። አመስጋኝነቴን ለመግለጽ የገንዘብ መዋጮ ማድረግ እፈልጋለሁ። አምላክን ለማገልገል ስትሉ ብዙ መሥዋዕት እንደምትከፍሉ አውቃለሁ። ያደረጋችሁት ነገር ጥሩ ሰዎች እንደሆናችሁ ይመሠክራል፤ ይህን ከዳኒዬል ሐቀኝነትና ታማኝነት ማየት ችያለሁ። ስለዚህ በድጋሚ አመሰግናለሁ፤ አምላክ አገልግሎታችሁን ይባርክላችሁ።”

ከተወሰኑ ወራት በኋላ የዳኒዬል አባት ሰውየውን በድጋሚ አነጋግሮት ነበር፤ ሰውየውም ከጥቂት ጊዜ በፊት ስላጋጠመው ነገር ነገረው። ዕቃ እየገዛ ሳለ መሬት ላይ ቦርሳ ወድቆ አገኘ። የቦርሳውን ባለቤት አግኝቶ ቦርሳውን ከመለሰላት በኋላ እንዲህ እንዲያደርግ ያነሳሳው ምን እንደሆነ ገለጸላት። እሱም ከተወሰነ ጊዜ በፊት ሌላ ሰው በሐቀኝነት ቦርሳውን እንደመለሰለት ነገራት። እንዲህ ብሏል፦ “ሐቀኝነትና ደግነት የሚንጸባረቅበት አንድ ድርጊት ሌላውም ሰው ተመሳሳይ ነገር እንዲያደርግ ያነሳሳዋል፤ በዚህ መልኩ መላው ኅብረተሰብ ተጠቃሚ ይሆናል።”

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ