የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g94 10/8 ገጽ 17
  • ተወርዋሪ ኮከቦች የሚመጡት ከየት ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ተወርዋሪ ኮከቦች የሚመጡት ከየት ነው?
  • ንቁ!—1994
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ከፕላኔቶች ባሻገር ምን ይገኛል?
    ንቁ!—2000
  • ንዑሳን ፕላኔቶችና ጅራታም ኮከቦች፣ ከምድር ጋር መላተም በመገስገስ ላይ ናቸው?
    ንቁ!—1999
  • ፕላኔቷ ምድር ዕጣዋ ጥፋት ነውን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
  • ምድርን እንደ ጋሻ ሆነው የሚከልሉ አስደናቂ ነገሮች
    ንቁ!—2009
ንቁ!—1994
g94 10/8 ገጽ 17

ተወርዋሪ ኮከቦች የሚመጡት ከየት ነው?

“አቤት፣ ተመልከት! እዚያ ጋም ሌላኛው ይታያል!” “የት አለ? የቱ ጋ?” በምሽት ሰማይ ላይ ተወርዋሪ ኮከቦችን እየፈለግህ ሳለ እንዲህ ያሉ ቃላት ተናግረህ አታውቅምን? ከበላይህ በተንጣለለው የከዋክብት መስክ ላይ በድንገት መስመር እየሠራ የሚሄድ የብርሃን ፈለግ ለመጀመሪያ ጊዜ ስትመለከት ከከዋክብት አንዱ ሰማይን አቋርጦ እየተወረወረ ያለ ሊመስልህ ይችላል። እርግጥ ተወርዋሪ ኮከቦች የማይገባቸውን ስያሜ መያዛቸው እውነት ነው። “ተወርዋሪ” ሊሆኑ ቢችሉም ነገር ግን ኮከቦች አይደሉም።

የጠፈር ተመራማሪዎች ሚቲዮርስ ብለው ይጠሯቸዋል። መጠነኛ የሆነ ኮከብ ዓለማችንን ከሚልዮን ጊዜ በላይ ሊውጣት ቢችልም እነዚህን በሚልዮን የሚቆጠሩ ሚቲዮርስ የምትውጣቸው የኛው ፕላኔት ናት። ሚቲዮርስ ምንድን ናቸው? ከየትስ ይመጣሉ?

ሚቲዮርስ ከጅራታም ኮከቦች ጋር ግንኙነት አላቸው። ታዋቂዋ ምሳሌ የሐሌይ ጅራታም ኮከብ በፀሐይ ዙሪያ በምታደርገው የ76 ዓመት ጉዞ በ1986 ምድርን አቋርጣ ስታልፍ ታይታ ነበር። ጅራታም ኮከቦች በአብዛኛው የተሠሩት ከበረዶና ከአቧራ ስለሚመስል አንዳንዴ ቆሻሻ የበረዶ ኳሶች ተብለው ይጠራሉ። አንድ ጅራታም ኮከብ ወደ ፀሐይ በሚቀርብበት ጊዜ የላይኛው ገጽ ይሞቅና አቧራ እንዲሁም ጋዝ ይለቃል። የፀሐይ ጨረር የሚፈጥረው ግፊት በአንጸባራቂው አቧራ ውስጥ ያለውን ጠጣር ቁስ ወደ ታች ይገፋዋል። ጅራታሙ ኮከብ የፍርስራሹን አቧራማ ፈለግ ትቶ ሲያልፍ ከዚያም በኋላ በሕዋ ውስጥ የሚቀሩት ቅንጣቶች ሚቲዮሮይድስ ተብለው ይጠራሉ። አብዛኛው የጅራታም ኮከብ አቧራ በዓይን የሚታይ ሚቲዮርስ ከመሆን በጣም ያነሰ ነው። ትንሹ ክፍልፋይ የአሸዋ ቅንጣት የሚያህል ሲሆን ጥቂቶቹ ደግሞ አነስተኛ ጠጠርን ያህል ይተልቃሉ።

አልፎ አልፎ ጅራታም ኮከብ የሚሽከረከርበት ምህዋር የመሬትን ምህዋር ያቋርጣል። ይህም ማለት ምድር የጅራታሙን ኮከብ ምህዋር በምታቋርጥበት ጊዜ ከዚያ የብናኝ ፈለግ ጋር ሁልጊዜ ትገናኛለች ማለት ነው። ይህ በሚከሰትበት ጊዜ ትንንሾቹ ሚቲዮሮይድስ በሕዋ ውስጥ በሴኮንድ 71 ኪሎ ሜትር በሆነ ከፍተኛ ፍጥነት ይምዘገዘጋሉ። ሚትዮሮይድስ በሚወድቁበት ጊዜ ትልልቆቹ ይግሉና ይቃጠላሉ፤ ይህም ሚቲዮርስ በመባል የሚታወቁትን ሰማይን እያቋረጡ የሚያበሩ ነጭ መስመሮች በሰማይ ላይ ይፈጥራል።

መሬት የአንድን ጅራታም ኮከብ ምህዋር በምታቋርጥበት ጊዜ ራዲያንት ተብሎ ከሚጠራ በሰማይ ላይ ከሚገኝ አንድ ነጥብ ተነሥተው ወደ ተለያዩ አቅጣጫዎች ሚቲዮርስ ሲወረወሩ ይታያሉ። በዓመቱ ውስጥ መደበኛ በሆነ ጊዜ ከእነዚህ ራዲያንቶች የሚቲዮር ናዳ ይዘንባል። አንዱ የታወቀው ትዕይንት ፐርሲድ የሚባለው ሲሆን ይህንን ስሙን ያገኘው መነሻው ፐርሲስ በሚባለው የሰሜናዊው ኅብረ ኮከብ ውስጥ ስለሚገኝ ነው። በየዓመቱ በነሐሴ 12 ወይም 13 ገደማ ፐርሲድ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በሚደርስበት ጊዜ አስደናቂ የሆነ ትዕይንት ይታያል። በእነዚህ ጊዜያት በየሰዓቱ ከ60 በላይ ሚቲዮርስ ይረግፋሉ።

ጥቅምት 21 አካባቢ በህዋ ላይ ከቀረ የሀሌይ ጅራታም ኮከብ ብናኝ የተፈጠረ ነው የሚባልለትን የጥንቱን አኩሪድስ የሜቲዮርስ ናዳ የሚመስለውን የኦሪዮኒድስ የሚቲዮርስ ናዳ ተመልክተህ ይሆናል። እንደ አስትሮኖሚ መጽሔት ዘገባ የሃሌይ ጅራታም ኮከብ “መላ አካሏን ከማጣቷ በፊት 100,000 ጊዜ በፀሐይ ዙሪያ መሽከርከር ትችላለች” በማለት ሳይንቲስቶች ገምተዋል። መላምታቸው ትክክል ከሆነ የሀሌይ ጅራታም ኮከብ በሚቀጥሉት 7,600,000 ዓመታት ውስጥ መደበኛ የሆነ ጉብኝት ታደርጋለች! ከብዙ ጊዜ በኋላም ቢሆን ፈለግ የሚጥለው አቧራ ለምድር ነዋሪዎች ረዘም ላለ ዕድሜ ተወርዋሪ ኮከቦቸ ማስገኘቱን ይቀጥላል። ዛሬ የምናያቸው አብዛኞቹ ሚቲዮርስ የሚመጡት ጥንቱኑ ሕልውናቸው ካከተመ ጅራታም ኮከቦች ይመስላል።

ሳይንቲስቶች በዓለም ዙሪያ በየቀኑ ወደ 200 ሚልዮን የሚጠጉ በዓይን ሊታዩ የሚችሉ ሚቲዮርስ እንዳሉ ይገምታሉ። አስደናቂዎቹ ብዛት ያላቸው የሚትዮር ናዳዎች በሚቀጥለው ዓመት ሳያቋርጡ ይኖራሉ፤ ለወደፊቱም በሚልዮን የሚቆጠሩ ይቀሩናል!

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ