ራስዎን ጠይቀው ያውቃሉን?
እስላሞችንና አይሁዶችን ከሕዝበ ክርስትና ሃይማኖቶች የሚለያቸው ዋነኛው ገደል ምንድን ነው? “የቅድስት ሥላሴ” ትምህርት ነው። ይህ ቀኖና ምን ይላል? ሥላሴ በአትናቴዎስ ድንጋጌ ላይ “አንድነት በሦስትነት ያለው አምላክ . . . አብ አምላክ ነው፣ ወልድ አምላክ ነው፣ መንፈስ ቅዱስም አምላክ ነው። ቢሆንም ሦስቱም አንድ አምላክ ናቸው እንጂ ሦስት አምላኮች አይደሉም” ይላል። ሦስቱም ዘላለማዊ፣ ሦስቱም ሁሉን ቻይ ሲሆኑ አንዳቸው ከአንዳቸው አይበልጡም፣ አንዳቸውም ከአንዳቸው አያንሱም። ሦስቱም አምላክ ሲሆኑ በአንድነት አንድ አምላክ ይሆናሉ። የሃይማኖት ሊቃውንት ትምህርቱ ምሥጢር ነው ይላሉ።
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሥላሴ የሚናገረው ነገር አለን?a የሚከተሉት ጥያቄዎች ወደ አንዳንድ መደምደ ሚያዎች ሊያደርሱዎት ይችላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጣቸው መልሶች በገጽ 26 ላይ ይገኛሉ።
1. እግዚአብሔር ጥንትም ሆነ አሁን ሥላሴ ከነበረ አይሁዳውያን ይህን ትምህርት በዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች (“በብሉይ ኪዳን”) ውስጥ አግኝተውት ነበርን?
2. የዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች ስለ እግዚአብሔር ምን ይላሉ?— ዘዳግም 6:4፤ መዝሙር 145፤ ዘካርያስ 14:9
3. በዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ ስለ መንፈስ ቅዱስ የተነገረ ነገር አለን?— መሳፍንት 15:14፤ ዘካርያስ 4:6
4. መንፈስ ቅዱስ በዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ የተገለጸው የራሱ አካልና ሕልውና እንዳለው ነው ወይስ የአምላክ አንቀሳቃሽ ኃይል እንደሆነ?— መሳፍንት 14:6፤ ኢሳይያስ 44:3
5. የዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች መሲሕ ወይም ቅቡዕ እንደሚመጣ ይናገራሉን?— ዳንኤል 9:25, 26
6. በዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ መሲሑ ከእግዚአብሔር ጋር እኩል እንደሆነ የሚያመለክት ጥቅስ ይገኛልን?— መዝሙር 2:2, 4–8፤ ኢሳይያስ 45:18፤ 61:1
7. በዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ ይሖዋ ሦስት አካል ያለው አንድ አምላክ መሆኑን እንድናምን ጠንካራ ምክንያት የሚሰጥ ጥቅስ ይገኛልን?— ኢሳይያስ 44:6፤ 46:9, 10
8. ኢየሱስን ወደ ምድር የላከው ማነው? ከሆነስ ከሁለቱ ማን ይበልጣል?— ዮሐንስ 5:19, 23, 30፤ 8:42፤ 14:28፤ 17:3
9. ኢየሱስ ራሱ እግዚአብሔር እንደሆነ ተናግሮ ያውቃልን?— ዮሐንስ 7:28, 29፤ 14:6
10. ኢየሱስን ብዙ ሰዎች አይተውታል። እግዚአብሔርን ግን ያየው ሰው ነበረን?— ዮሐንስ 1:18፤ 6:46
11. ኢየሱስ ‘እግዚአብሔር ወልድ ነኝ’ ነው ያለው ወይስ ‘የእግዚአብሔር ልጅ’?— ዮሐንስ 10:36፤ 1 ዮሐንስ 4:15፤ 5:5, 13
12. ኢየሱስ ከአብ ጋር እኩል ነኝ ብሎ ያውቃልን?— ዮሐንስ 14:28፤ 20:17
13. “እኔና አብ አንድ ነን” የሚሉት ቃላት ለሥላሴ ማስረጃ ሊሆኑ ይችላሉን?— ዮሐንስ 10:30፤ 17:21፤ ማቴዎስ 24:36
14. የመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት ኢየሱስን እንዴት ተመልክተውት ነበር?— ዮሐንስ 1:29, 34, 41, 49፤ 6:69፤ 1 ቆሮንቶስ 11:3
15. እግዚአብሔርስ ኢየሱስን እንዴት ይመለከተው ነበር?— ማርቆስ 9:7፤ ሉቃስ 2:9–11
16. የግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎች (“አዲስ ኪዳን”) የዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች መንፈስ ቅዱስ የአምላክ አንቀሳቃሽ ኃይል ስለመሆኑ የሚያመለክቱትን ያስተባብላሉን?— ማቴዎስ 3:11፤ ሉቃስ 1:41፤ ዮሐንስ 14:26፤ ሥራ 1:8፤ 4:31፤ 10:38
17. ኢየሱስ በተጠመቀበት ጊዜ አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ የት ነበሩ? ታዲያ አንድም ሦስትም ነበሩን?— ማቴዎስ 3:16, 17
18. ከሙታን የተነሳው ኢየሱስ በሰማይ ምን ዓይነት ቦታ አግኝቷል?— ሥራ 7:55, 56፤ ሮሜ 8:34፤ ቆላስይስ 3:1፤ ዕብራውያን 12:2
19. ይህን ከፍተኛ ቦታ ለኢየሱስ የሰጠው ማን ነው?— ፊልጵስዩስ 2:9–11
20. ታዲያ ይህ ኢየሱስን እግዚአብሔር ያደርገዋል ወይስ በአጽናፈ ዓለሙ ውስጥ ከእግዚአብሔር ሁለተኛ ደረጃ ያለው አካል?— 1 ቆሮንቶስ 11:3፤ ፊልጵስዩስ 2:9–11
21. በአጽናፈ ዓለሙ ውስጥ የሁሉ የበላይ የሆነው ሉዓላዊ ገዥ ማን ነው?— ዘዳግም 3:24፤ ሥራ 4:24–27፤ 1 ቆሮንቶስ 15:28
[የግርጌ ማስታወሻ]
a ስለዚህ ጉዳይ ሰፋ ያለ ግንዛቤ ለማግኘት ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር የተባለውን መጽሐፍ ገጽ 380–1 እና ገጽ 405–25፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን? የተባለውን ብሮሹር ይመልከቱ። ሁለቱም የታተሙት ኒው ዮርክ በሚገኘው የመጠበቂያ ግንብ መጽሐፍ ቅዱስና ትራክት ማኅበር ነው።