የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g98 2/8 ገጽ 3
  • ከጦርነት ጋር የሚመጣጠን እልቂት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከጦርነት ጋር የሚመጣጠን እልቂት
  • ንቁ!—1998
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ድልና አሳዛኝ ሽንፈት
    ንቁ!—1998
  • ከሳንባ ነቀርሳ ጋር ለሚደረገው ፍልሚያ የተቀየሰ አዲስ ስልት
    ንቁ!—1999
  • የሳንባ ነቀርሳ አገርሽቷል!
    ንቁ!—1996
  • ምድር አቀፍ መፍትሔ ሊገኝ ይችል ይሆን?
    ንቁ!—1998
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—1998
g98 2/8 ገጽ 3

ከጦርነት ጋር የሚመጣጠን እልቂት

የሃያ ሦስት ዓመቷ ማርሊን ሰውነቷ እየከሳና እየተዳከመ ሲመጣ ከእርግዝናዋ ጋር የተያያዘ ችግር መስሏት ነበር። ያለማቋረጥ ያስላት ስለነበረ ይህንኑ ለሐኪሟ ተናገረች። የመተንፈሻ አካልዋን ላይኛ ክፍል ኢንፌክሽን እንደያዛት ከነገራት በኋላ አንቲባዮቲክ መድኃኒት አዘዘላት። ቆየት ብሎ ሌሊት ሌሊት ማላብ ሲጀምራት ማርሊን በጣም ተጨነቀች። ወደ ሐኪሟ ተመለሰችና ደረቷን ራጅ እንድትነሳ አዘዛት።

በራጁ ላይ ያለው ጥላ መሰል ምልክት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ የሚያስገድድ ነበር። ሐኪሙ ግን ማርሊንን በስልክ ማግኘት አልቻለም። “ሐኪሙ እናቴን ፈልጎ አገኘና በጣም የታመምኩ መሆኔን ነገራት” ትላለች ማርሊን። “እናቴ ልትፈልገኝ መጣችና በፍጥነት ወደ ሐኪሙ እንድሄድ ነገረችኝ። እርሱም ወደ ሆስፒታል ላከኝና እንደገና ራጅ ከተነሣሁ በኋላ እዚያው ተኛሁ።”

ማርሊን ሳንባ ነቀርሳ እንደያዛት ሲነገራት በጣም ደነገጠች። ወዲያው የምትሞት መሰላት። የሳንባ ነቀርሳ መድኃኒቶች ስትወስድ ከቆየች በኋላ ግን ጤነኛ ሆነች።

ማርሊን ሳንባ ነቀርሳ እንደያዛት ሲነገራት የደነገጠችበትን ምክንያት መረዳት አያስቸግርም። እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ብዙ ሰዎች፣ የጤና ባለሞያዎችም ሳይቀሩ ሳንባ ነቀርሳ ከበለጸጉ አገሮች ፈጽሞ እንደጠፋ ያምኑ ነበር። በለንደን በሚገኝ የሕክምና ማዕከል የምትሠራ አንዲት የጤና ረዳት “ከቡቦኒክ ወረርሽኝ ጋር ያከተመ ይመስለኝ ነበር። እዚህ መጥቼ መሥራት ከጀመርኩ በኋላ ግን በሽታው ገና ያልሞተ መሆኑን ብቻ ሳይሆን በመሐል ከተማ ብዙ ሰዎችን እየፈጀ እንዳለ ተገነዘብኩ” ብላለች።

ሳንባ ነቀርሳ ጠፍቶባቸው በነበሩ አገሮች መልሶ ሲያገረሽ በሽታው በነበረባቸው አገሮች ደግሞ በጣም ተባብሷል። ድል ከመደረግ ይልቅ ከጦርነትና ከረሐብ የማይተናነስ ቀሳፊ ሆኗል። የሚከተሉትን መረጃዎች ተመልከት:-

◼ ዘመናዊው የሕክምና ሳይንስ በጣም አስደናቂ የሆነ እድገት ቢያሳይም ሳንባ ነቀርሳ ባለፉት መቶ ዓመታት 200 ሚልዮን የሚያክሉ ሰዎችን ለመቃብር ዳርጓል።

◼ በአሁኑ ጊዜ ሁለት ቢልዮን የሚያክሉ ሰዎች ከዓለም ሕዝቦች አንድ ሶስተኛ የሚሆኑት ማለት ነው፣ ቲ ቢ ባሲለስ በተባለው ባክቴሪያ ተለክፈዋል። በተጨማሪም በያንዳንዱ ሴኮንድ አንድ ሰው በበሽታው ይለከፋል።

◼ በ1995 የሳንባ ነቀርሳ ሕመምተኞች ቁጥር 22 ሚልዮን ያክል ነበር። ከእነዚህ መካከል፣ በአብዛኛው ባልለሙ አገሮች የሚኖሩ ሦስት ሚልዮን ሰዎች ሞተዋል።

ሳንባ ነቀርሳን የማሸነፍ ኃይል ያላቸው መድኃኒቶች እያሉ ይህ በሽታ የሰው ልጆችን ሕይወት መቅጠፉን ያላቆመው ለምንድን ነው? ድል ሊደረግ የሚችልበት ጊዜ ይመጣ ይሆን? ራስህን ከዚህ በሽታ ለመጠበቅ የምትችልበት መንገድ ይኖራል? የሚቀጥሉት ርዕሶች ለእነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ።

[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የኒው ጀርሲ የሕክምና ትምህርት ቤት—ብሔራዊ የሳንባ ነቀርሳ ማዕከል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ