የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g98 2/8 ገጽ 8-9
  • ምድር አቀፍ መፍትሔ ሊገኝ ይችል ይሆን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ምድር አቀፍ መፍትሔ ሊገኝ ይችል ይሆን?
  • ንቁ!—1998
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጪው ድል
  • ከሳንባ ነቀርሳ ጋር ለሚደረገው ፍልሚያ የተቀየሰ አዲስ ስልት
    ንቁ!—1999
  • ድልና አሳዛኝ ሽንፈት
    ንቁ!—1998
  • የሳንባ ነቀርሳ አገርሽቷል!
    ንቁ!—1996
  • ከጦርነት ጋር የሚመጣጠን እልቂት
    ንቁ!—1998
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—1998
g98 2/8 ገጽ 8-9

ምድር አቀፍ መፍትሔ ሊገኝ ይችል ይሆን?

ሳንባ ነቀርሳ ምድር አቀፍ የሆነ መፍትሔ የሚፈልግ ምድር አቀፍ ችግር እንደሆነ ሊቃውንት ይስማማሉ። በየሳምንቱ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አኅጉራዊ ድንበሮችን ስለሚሻገሩ በተናጠል ሳንባ ነቀርሳን ለመቆጣጠር የሚችል አገር የለም።

ዓለም አቀፍ ትብብር መኖሩና የበለጸጉ አገሮች በከፍተኛ ደረጃ በሳንባ ነቀርሳ የተጠቁ ድሃ አገሮችን መርዳታቸው አስፈላጊ እንደሆነ ብዙዎች ያምናሉ። ዶክተር አራታ ኮቺ እንደሚሉት “የበለጸጉ አገሮች ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ የገዛ አገሮቻቸው የውጊያው አውድማ ከመሆናቸው በፊት ያልበለጸጉ አገሮች ሳንባ ነቀርሳን እንዲዋጉ መርዳት ይኖርባቸዋል።”

ባለጠጋ አገሮች ግን ይበልጥ አሳሳቢና ቅድሚያ ሊሰጧቸው የሚገቡ ናቸው በሚሏቸው ችግሮች የተዋጡ በመሆናቸው ፈጥነው የእርዳታ እጃቸውን አልዘረጉም። አንዳንድ ድሃ አገሮችም ቢሆኑ ለጤና አጠባበቅ ጉዳዮች ቅድሚያ ከመስጠት ይልቅ በርካታ ገንዘብ ለጦር መሣሪያ ማከማቻ ያውላሉ። በ1996 አጋማሽ ላይ ከሳንባ ነቀርሳ በሽተኞች መካከል ዲ ኦ ቲ ኤስ በተባለው የሕክምና ዘዴ ሕክምና የተደረገላቸው 10 በመቶ ለሚሆኑት ብቻ ነበር። ይህ መጠን የሳንባ ነቀርሳ ወረርሽኝ እንዳይባባስ ለመከላከል የሚያስችል አይደለም።

የዓለም ጤና ድርጅት “ሳንባ ነቀርሳን ለማዳን የሚያስችለው እውቀትና ብዙ ወጪ የማይጠይቁ መድኃኒቶች ከተገኙ በርካታ ዓመታት አልፈዋል። በአሁኑ ጊዜ ዓለም የሚፈልገው እነዚህ መድኃኒቶች በመላው ዓለም ውጤታማ በሆነ መንገድ ሥራ ላይ እንዲውሉ የሚያደርግ ወሳኝ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል ሥልጣን፣ ተሰሚነትና አዘኔታ ያላቸውን ሰዎች ነው” ብሏል።

መጪው ድል

ሰብዓዊ ባለ ሥልጣኖች ለችግሩ መፍትሔ ያስገኛሉ የሚል አስተማማኝ ተስፋ ሊኖረን ይችላል? የመጽሐፍ ቅዱሱ መዝሙራዊ በመንፈስ ተነድቶ “ማዳን በማይችሉ በሰው ልጆችና በአለቆች አትታመኑ” ሲል ጽፏል። ታዲያ በማን መታመን እንችላለን? ይኸው ጥቅስ በመቀጠል “የያዕቆብ አምላክ ረዳቱ የሆነ፣ ተስፋውም በአምላኩ በእግዚአብሔር የሆነ ሰው ምስጉን ነው። እርሱም ሰማይንና ምድርን ባሕርንም በእነርሱ ያለውንም ሁሉ” ፈጠረ ይላል።—መዝሙር 146:3, 5, 6

ይሖዋ አምላክ የምድር ፈጣሪ እንደመሆኑ መጠን በሽታን ፈጽሞ ለማጥፋት የሚያስችል ኃይልና ጥበብ አለው። ርኅራኄስ አለው? ይሖዋ በራሱ ነቢይ አማካኝነት የሚከተለውን ቃል ሰጥቷል:- “ሰውም የሚያገለግለውን ልጁን እንደሚምር እንዲሁ [ሕዝቦቼን] እምራቸዋለሁ።”—ሚልክያስ 3:17

የመጨረሻው የመጽሐፍ ቅዱስ ምዕራፍ ለሐዋርያው ዮሐንስ ስለ ተሰጠ አንድ ራእይ ይገልጻል። “በየወሩ እያፈራ አሥራ ሁለት ፍሬ የሚሰጥ የሕይወት ዛፍ” ተመለከተ። እነዚህ ምሳሌያዊ ዛፎችና ዛፎቹ የሚያፈሯቸው ፍሬዎች ታዛዥ የሆኑ የሰው ልጆች ለዘላለም እንዲኖሩ የሚያስችሏቸውን መለኮታዊ ዝግጅቶች ያመለክታሉ።—ራእይ 22:2

ዮሐንስ በመቀጠል “የዛፉም ቅጠሎች ለሕዝብ መፈወሻ ነበሩ” ሲል ጽፏል። ምሳሌያዊዎቹ ቅጠሎች ለሰው ልጅ መንፈሳዊና አካላዊ ፈውስ የሚያስገኙትን የአምላክ በረከቶች ያመለክታሉ። ስለዚህ በአምላክ በሚገዛው አዲስ የጽድቅ ሥርዓት ውስጥ ሳንባ ነቀርሳ ሙሉ በሙሉና ለዘላለም ድል እንደሚደረግ እርግጠኞች ልንሆን እንችላለን።—ራእይ 21:3, 4

[በገጽ 8, 9 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የሰው ልጅ ዘላቂ የሆነ ፈውስ እንደሚያገኝ አምላክ ቃል ገብቷል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ