የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 12/10 ገጽ 29
  • ከዓለም አካባቢ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከዓለም አካባቢ
  • ንቁ!—2010
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የምድር መናወጥ—‘ከባድ እልቂት እያስከተለ ያለው የተፈጥሮ አደጋ’
  • አደገኛ ሥራ
  • የዕቃዎች ዋጋ በመቀነሱ ቤት ዘራፊዎች ቀነሱ
  • የተፈጥሮ አደጋዎች ይህን ያህል የበዙት ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ተፈጥሮ አደጋዎች ምን ይላል?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የተፈጥሮ አደጋዎች የዘመኑ ምልክት ናቸውን?
    መጠበቂያ ግንብ—1993
  • የተፈጥሮ አደጋዎች ሲከሰቱ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2010
g 12/10 ገጽ 29

ከዓለም አካባቢ

የሰርቢያ የሃይማኖታዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር የይሖዋ ምሥክሮችን የሚወክለው ሕጋዊ ድርጅት ያቀረበውን የምዝገባ ጥያቄ ተቀብሏል። የመንግሥት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የይሖዋ ምሥክሮች በዚህ አካባቢ እንቅስቃሴ ማድረግ የጀመሩት ቢያንስ ከ1930 አንስቶ ነው።

በ2009 በመላው ዓለም ከኢንተርኔት ላይ ከተቀዱት ሙዚቃዎች መካከል 95 በመቶ የሚሆኑት ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ የተቀዱ ናቸው።—ታይም፣ ዩናይትድ ስቴትስ

የምድር መናወጥ—‘ከባድ እልቂት እያስከተለ ያለው የተፈጥሮ አደጋ’

መቀመጫውን ጄኔቫ፣ ስዊዘርላንድ ያደረገው የተባበሩት መንግሥታት ዓለም አቀፍ የአደጋ ቅነሳ ስትራቴጂ “ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ እጅግ ከባድ እልቂት ያስከተለው የተፈጥሮ አደጋ የምድር መናወጥ” እንደነበረ ገልጿል። በዚህ ጊዜ ውስጥ በተፈጥሮ አደጋ ከሞቱት ሰዎች 60 በመቶ የሚሆኑት ሕይወታቸውን ያጡት በምድር መናወጥ ነበር። በዓለም ላይ እጅግ ከፍተኛ የሕዝብ ብዛት ካላቸው 10 ከተሞች ውስጥ 8ቱ የሚገኙት የምድር መናወጥ በሚያጠቃቸው አካባቢዎች በመሆኑ ይህ “የተፈጥሮ አደጋ” ወደፊትም ቢሆን ከባድ አደጋ ማድረሱ የማይቀር ነው። ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ ከባድ እልቂት አስከትለዋል ተብለው በተፈረጁት 3,852 አደጋዎች ከ780,000 የሚበልጡ ሰዎች አልቀዋል።

አደገኛ ሥራ

መቀመጫውን ቪየና፣ ኦስትርያ ውስጥ ያደረገው ኢንተርናሽናል ፕሬስ ኢንስቲትዩት እንደዘገበው “በ2009 በሞያቸው ምክንያት 110 የሚያህሉ ጋዜጠኞች ተገድለዋል። ይህም ባለፉት አሥርተ ዓመታት ከተገደሉ ጋዜጠኞች ቁጥር አንጻር 2009ን ተወዳዳሪ የሌለው ዓመት እንዲሆን አድርጎታል።” ግጭት ባለባቸው እንደ አፍጋኒስታን፣ ኢራቅ፣ ፓኪስታንና ሶማሊያ ባሉት አገሮች በቅርብ ዓመታት “በጋዜጠኞች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ተፈጽሟል” በማለት ሪፖርቱ ዘግቧል። በዚህ ምክንያት ስለነዚህ አካባቢዎች በቂ መረጃ ማግኘት ባለመቻሉ “ከባድ የሆኑ ጉዳዮችን በተመለከተ የመረጃ ክፍተት ተፈጥሯል።” ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ ለጋዜጠኞች አደገኛ በመሆን የአንደኝነቱን ደረጃ የያዘችው ኢራቅ ስትሆን ፊሊፒንስ፣ ኮሎምቢያ፣ ሜክሲኮና ሩሲያ እንደ ቅደም ተከተላቸው ቀጣዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል።

የዕቃዎች ዋጋ በመቀነሱ ቤት ዘራፊዎች ቀነሱ

ከለንደን የተላለፈ የሮይተርስ ዜና ዘገባ በእንግሊዝ፣ የሌስተር ዩኒቨርሲቲ የክሪሚኖሎጂ መምህር የሆኑት ጀምስ ትሬድዌል የተናገሩትን በመጥቀስ “ርካሽ የኤሌክትሮኒክ ዕቃዎች በብዛት መግባታቸው” የብሪታንያን ቤት ዘራፊዎች ከሥራ ውጭ ሊያደርጋቸው እንደሚችል ገልጿል። ለምሳሌ፣ የአዳዲስ ዲቪዲ ማጫወቻዎች ዋጋ መርከሱ ያገለገሉ የዲቪዲ ማጫወቻዎችን ዋጋ አሳጥቷቸዋል። ትሬድዌል “እነዚህን ዕቃዎች መስረቅ ምንም ጥቅም የለውም” ብለዋል። ይሁን እንጂ የዕቃ ዋጋ መቀነስ ወንጀል ጨርሶ እንዲጠፋ አላደረገም። እንዲያውም በተቃራኒው በአሁኑ ጊዜ ሌቦች “ሰዎች ይዘዋቸው በሚንቀሳቀሱ እንደ ሞባይል ስልኮችና አይፓዶች” ባሉ ይበልጥ ውድና ተፈላጊ በሆኑ ዕቃዎች ላይ ማነጣጠር ጀምረዋል። በዚህ ምክንያት ቤት ይዘርፉ የነበሩ ወንጀለኞች አሁን በሰዎች ላይ ጥቃት በማድረስ ንብረታቸውን ወደ መቀማት ተሸጋግረዋል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ