የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w93 12/1 ገጽ 2-4
  • የተፈጥሮ አደጋዎች የዘመኑ ምልክት ናቸውን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የተፈጥሮ አደጋዎች የዘመኑ ምልክት ናቸውን?
  • መጠበቂያ ግንብ—1993
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ተፈጥሮ አደጋዎች ምን ይላል?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የተፈጥሮ አደጋዎች ይህን ያህል የበዙት ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ለተፈጥሮ አደጋዎች ተጠያቂው አምላክ ነውን?
    መጠበቂያ ግንብ—1993
  • የተፈጥሮ አደጋዎች ሲከሰቱ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
ለተጨማሪ መረጃ
መጠበቂያ ግንብ—1993
w93 12/1 ገጽ 2-4

የተፈጥሮ አደጋዎች የዘመኑ ምልክት ናቸውን?

“ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፣ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤ እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።” እነዚህ ቃላት ኢየሱስ ክርስቶስ ከላይ የተዘረዘሩት ከፍተኛ እልቂት የሚያስከትሉ ሁኔታዎች፣ የዓመፅ መስፋፋትና የአምላክ መንግሥት ምሥራች በመላው ዓለም መሰበክ የአሁኑ ‘የነገሮች ሥርዓት መደምደሚያ’ መቅረቡን የሚያመለክተው ጣምራ ምልክት መጀመሩን የሚያሳዩ እንደሚሆኑ ከ19 መቶ ዓመታት በፊት ለደቀ መዛሙርቱ ሲገልጽ የተናገራቸው ናቸው። — ማቴዎስ 24:​3–14

በዚህ መሠረት የሚከተለውን ጥያቄ መጠየቅ አለብን:- “የቀድሞዎቹ ትውልዶች ካዩት የበለጠ መቅሰፍታዊ የመሬት መናወጥ፣ አውሎ ነፋስ፣ የውኃ መጥለቅለቅ፣ ድርቅና ረሀብ እያየን ነውን? የሳይንስና ቴክኖሎጂ እድገት ቢኖርም በዚሁ ሳቢያ በአሁኑ ዘመን ከሌላው ዘመን የበለጡ ብዙ ሰዎች ስቃይ እየደረሰባቸው ነውን?

ብዙ ሰዎች አዎን ብለው ይመልሳሉ። ለምሳሌ ያህል ኒው ሳይንቲስት የተሰኘ መጽሔት “ዓለም በ1990ዎቹ ዓመታት ውስጥ ከፊተኞቹ አሥርተ ዓመታት ይበልጥ ብዙ መቅሰፍቶች እንደሚደርሱ ሊጠብቅ ይችላል” በማለት አስጠንቅቋል። በተመሳሳይም በሰኔ 1991 የዓለም ሜትሮሎጂያዊ ድርጅት ዲሬክተር ዩ ኤን ክሮኒክል መጽሔት ላይ እንደሚከተለው በማለት ተናግረዋል:- “አዝማሚያው በጣም ግልጽ ነው። ከ1960ዎቹ እስከ 1980ዎቹ ዓመታት ድረስ . . . ታላላቅ የተፈጥሮ አደጋዎች አምስት እጥፍ፣ በአጠቃላዩ ኢኮኖሚ ላይ የደረሰው ጉዳት ሦስት እጥፍ ጨምሮአል።” የተባበሩት መንግሥታት የዓለም ጤና ድርጅት መጽሔት የሆነው ዎርልድ ሄልዝ ስለጉዳዩ መጠነኛ መግለጫ ሲሰጥ እንዲህ ብሏል:- “ለተፈጥሮ አደጋዎችና ለሚያስከትሏቸው አጥፊ ውጤቶች ምሳሌ የሚሆኑ ሁኔታዎች በታሪክ ዘመናት በሙሉ እንደነበሩ ሊደረስበት ይችላል። ይሁን እንጂ 21ኛው መቶ ዘመን እየተቃረበ ሲመጣ ብዙ ሕዝቦችን ለተፈጥሮአዊም ሆነ ለሰው ሠራሽ መቅሰፍቶች የሚያጋልጥ ተለዋዋጭ የሆነ የሥነ ሕዝባዊ፣ የሥነ ምሕዳራዊና (ኢኮሎጂካል) የቴክኖሎጂያዊ ሁኔታዎች ውሕደት ያጋጥመናል።”

የዓለምን ሁኔታዎች በትኩረት የሚከታተል ማንኛውም ሰው ከላይ እንደተጠቀሰው ባሉት አነጋገሮች አይገረምም። የዜና ማሠራጫዎች በፊሊፒንስ እንደደረሰው የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ፣ በካሊፎርኒያ እንደደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ፣ በባንግላዴሽ እንደደረሰው የውኃ መጥለቅለቅ፣ በሶማሊያ እንደደረሰው ረሀብ፣ በሀዋይ እንደ ደረሰው አውሎ ነፋስ ወይም በኒካራጉዋ እንደደረሰው ማዕበል ያሉ የሚዘገንኑ ወሬዎች አጥተው አያውቁም። በአንዱ ወይም በሌላው የምድር ክፍል አደጋ መድረሱን የሚገልጽ ዜና ሳይሰማ የሚያልፍበት አንድም ወር አይገኝም።

አንዳንድ ሰዎች ይህን ጉዳይ ከቁም ነገር አይጥፉትም። በተሻለ ሁኔታ ሪፖርት ስለሚደረጉና ስለሚመዘገቡ ብቻ ነው ብለው ይከራከራሉ። በተጨማሪም ከበፊቱ ይበልጥ ብዙ ሰዎች በአደጋዎች የሚጠቁት የሰዎች ቁጥር ከቀድሞው ስለበዛ ብቻ ነው ብለው ይከራከራሉ። ይሁን እንጂ እነዚህ የመከራከሪያ ምክንያቶች በቂ ናቸው ወይስ ሊታወቁ የሚያስፈልጉ ተጨማሪ ዝርዝሮች አሉ?

ከላይ በተጠቀሰው የኒው ሳይንቲስት መጽሔት ላይ የተባለውን ልብ በል። “በ1960ዎቹ ዓመታት 523 የተፈጥሮ አደጋዎች እንደደረሱ ሲዘገብ በ1970ዎቹ ዓመታት ደግሞ 767 የተፈጥሮ አደጋዎች እንደደረሱ ተዘግቦ ነበር። በ1980ዎቹ ዓመታት ግን የደረሱት የተፈጥሮ አደጋዎች ቁጥር 1387 ደርሶ ነበር።” ማብራሪያውንም በመቀጠል “ባለፉት አሥርተ ዓመታት ቁጥሩ ጨምሮ የታየው በቻይናና በሶቪየት ህብረት የሚደርሱ አደጋዎች በበለጠ ግልጽነት ሪፖርት ስለሚደረጉ ብቻ ሊሆን ይችላል” ብሎአል። ጨምሮም “ይህም ሆኖ ቁጥሩ [የአደጋዎቹ] እየጨመረ ነው” ብሏል። የአደጋዎች ቁጥር ያሻቀበው አደጋዎች በተሻለ ሁኔታ ስለሚዘገቡ ወይም ስለሚመዘገቡ ብቻ ነው ሊባል አይቻልም።

በተጨማሪም የመጋቢት 1992 ዩ ኤን ክሮኒክል መጽሔት “ባለፉት ሁለት አሥርተ ዓመታት የተፈጥሮ አደጋዎች ባመጡት ‘ጥፋት፣ መከራና ስቃይ’ ምክንያት 3 ሚልዮን የሚያህሉ ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ ሌሎች 800 ሚልዮን ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል” በማለት ዘግቧል። ይህም ማለት በምድር ላይ ከሚኖሩት ከ7 ሰዎች 1ዱ በአንድ ዓይነት አደጋ ወይም አሳዛኝ መከራ ተነክቷል ማለት ነው። ይህም በእርግጥ ናላ የሚያዞርና ዘመናችን የብጥብጥና የሁከት ዘመን መሆኑን እንዳንጠራጠር የሚያደርግ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ያለ የጭንቀት ዘመን እንደሚመጣ ትንቢት ስለተናገረ ለአደጋዎቹና በእነርሱም ምክንያት ለሚደርሰው ሥቃይ ተጠያቂው አምላክ ነው ማለት ነውን? ብዙ ሰዎች እንደዚህ ይመስላቸዋል። ሆኖም ማስረጃዎቹ ምን ያሳያሉ? ከሁሉ ይበልጥ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

[ምንጭ]

W. Faidley/Weatherstock

[ምንጭ]

Middle photo: Mark Peters/Sipa Press

WHO/League of Red Cross

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ