የርዕስ ማውጫ
ሚያዝያ 2013
© 2013 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania. All rights reserved.
የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ፦ በትዳር ጓደኛ ላይ የሚሰነዘር ጥቃት—መፍትሔው ምን ይሆን? 8-11
16 ኢንተርኔት ላይ ጽሑፎቻችን የሚገኙበት አቋራጭ!
ኢንተርኔት ላይ የሚገኙ
ወጣቶች
የወጣቶች ጥያቄ . . .
ጉልበተኞች ቢያስፈራሩኝስ?
“ያወጡልኝን ቅጽል ስሞች ወይም ይሉኝ የነበረውን ነገር ፈጽሞ አልረሳውም” በማለት የ20 ዓመቷ ሴሊን ተናግራለች። “የማልረባ፣ የማልፈለግና ከንቱ እንደሆንኩ እንዲሰማኝ ያደርጉ ነበር። ቢመቱኝ እመርጥ ነበር።” ኢንተርኔት ላይ የሚገኘው ይህ ርዕስ እንደሚከተሉት ላሉ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል፦ ጉልበተኛ የሆኑ ልጆች ሌሎችን የሚያስፈራሩት ለምንድን ነው? አብዛኛውን ጊዜ ጉልበተኞች የሚያስፈራሩት እነማንን ነው? ጉልበተኞች እያስፈራሩህ ከሆነ ምን ማድረግ ትችላለህ?
(በእንግሊዝኛ “ባይብል ቲቺንግስ/ቲንኤጀርስ” በሚለው ሥር ይገኛል)
ልጆች
በሥዕል መልክ የተዘጋጁ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን ከልጆቻችሁ ጋር አንብቡ። መልመጃዎች ያሉበትን ገጽ በመጠቀም ልጆቻችሁ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለተጠቀሱት ባለታሪኮች እና ስለ ሥነ ምግባር መሥፈርቶች ያላቸውን ግንዛቤ እንዲያሳድጉ እርዷቸው።
(በእንግሊዝኛ “ባይብል ቲቺንግስ/ችልድረን” በሚለው ሥር ይገኛል)