የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 2/14 ገጽ 12-13
  • የታሪክ መስኮት—ቆስጠንጢኖስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የታሪክ መስኮት—ቆስጠንጢኖስ
  • ንቁ!—2014
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አብያተ ክርስቲያናት—ሕጋዊ እውቅና ተሰጣቸው እንዲሁም መጠቀሚያ ተደረጉ
  • ምን ዓይነት ክርስትና?
  • ታላቁ ቆስጠንጢኖስ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
  • ሕዝበ ክርስትና የዚህ ዓለም ክፍል ለመሆን የበቃችው እንዴት ነው?
    መጠበቂያ ግንብ—1993
  • ማጭበርበሪያ የሆነች መንግሥት ተነሣች
    “መንግሥትህ ትምጣ”
  • ክፍል 12:-100–476 እዘአ​—የወንጌሉን ብርሃን ማዳፈን
    ንቁ!—1995
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2014
g 2/14 ገጽ 12-13
ከነሐስ የተሠራ የቆስጠንጢኖስ ሐውልት

የታሪክ መስኮት

ቆስጠንጢኖስ

ቆስጠንጢኖስ፣ ክርስትናን መቀበሉን በይፋ የተናገረ የመጀመሪያው የሮም ንጉሠ ነገሥት ነው። ይህን በማድረጉም በዓለም ታሪክ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል። ቆስጠንጢኖስ፣ ስደት ይደርስበት የነበረውን ይህን ሃይማኖት በመቀበል ሕዝበ ክርስትና እንዲቋቋም መንገድ ጠርጓል። በመሆኑም ዚ ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ እንደሚገልጸው ይህ የስመ ክርስትና ሃይማኖት በታሪክ ውስጥ ተወዳዳሪ ያልተገኘለት ተጽዕኖ ያሳደረ “ጠንካራ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ተቋም” መሆን ችሏል።

በጥንት ዘመን ስለኖረ ሮማዊ ንጉሠ ነገሥት መነጋገር ለምን አስፈለገ? የክርስትና ጉዳይ የሚያሳስብህ ሰው ከሆንክ ስለ ቆስጠንጢኖስ ማወቅህ ይህ ሰው በፖለቲካ እና በሃይማኖት ረገድ የተጫወተው ሚና እስከ ዛሬም ድረስ በብዙ አብያተ ክርስቲያናት እምነቶችና ልማዶች ላይ ተጽዕኖ እንዳሳደረ ለመረዳት ያስችልሃል። ይህን ያደረገው እንዴት እንደሆነ እስቲ እንመልከት።

አብያተ ክርስቲያናት—ሕጋዊ እውቅና ተሰጣቸው እንዲሁም መጠቀሚያ ተደረጉ

በ313 ዓ.ም. ቆስጠንጢኖስ በምዕራባዊው የሮም ግዛት ላይ ሲገዛ በምሥራቃዊው የሮም ግዛት ላይ ደግሞ ሊቺኒዩስ እና ማክሲሚኑስ ይገዙ ነበር። ቆስጠንጢኖስና ሊቺኒዩስ ክርስቲያኖችን ጨምሮ ለሕዝባቸው በሙሉ የአምልኮ ነፃነት ሰጡ። ቆስጠንጢኖስ፣ የክርስትና እምነት ግዛቱን አንድ እንደሚያደርግለት ስላመነ ለዚህ ሃይማኖት ጥበቃ ማድረግ ጀመረ።a

ይሁን እንጂ ቆስጠንጢኖስ አብያተ ክርስቲያናቱ በውዝግብ መከፋፈላቸውን ሲያይ ተደናገጠ። አብያተ ክርስቲያናቱ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ስለፈለገ “ትክክለኛውን” ትምህርት ለመለየትና ከዚያም ለማጽደቅ አሰበ። ጳጳሳቱ የእሱን ሞገስ ለማግኘት በሃይማኖታቸው ረገድ አቋማቸውን ማላላት ነበረባቸው፤ ይህን ያደረጉት ጳጳሳት ከግብር ነፃ የመሆን መብትና ዳጎስ ያለ የገንዘብ ድጋፍ ያገኙ ነበር። የታሪክ ምሁር የሆኑት ቻርልስ ፍሪማን እንዲህ ብለዋል፦ “‘ትክክለኛውን’ ዓይነት የክርስትና መሠረተ ትምህርት ይዞ መገኘት ወደ መንግሥተ ሰማያት ለመግባት መንገድ ከመክፈቱም ባሻገር እዚሁ ምድር ላይ ከፍተኛ ሀብት ያስገኝ ነበር።” በዚህ መንገድ የቀሳውስቱ መደብ በዓለማዊ ጉዳዮች ረገድ ከፍተኛ ተደማጭነት ማግኘት ጀመረ። የታሪክ ምሁር የሆኑት አርኖልድ ሂው ማርቲን ጆንስ “ቤተ ክርስቲያኒቱ ያገኘችው፣ ጠባቂ ብቻ ሳይሆን አለቃም ጭምር ነበር” በማለት ተናግረዋል።

“ቤተ ክርስቲያኒቱ ያገኘችው፣ ጠባቂ ብቻ ሳይሆን አለቃም ጭምር ነበር።”—አርኖልድ ሂው ማርቲን ጆንስ፣ የታሪክ ምሁር

ምን ዓይነት ክርስትና?

የቆስጠንጢኖስና የጳጳሳቱ መሻረክ በከፊል የክርስትናን፣ በከፊል ደግሞ የአረማዊ አምልኮን ትምህርቶች ያቀፈ ሃይማኖት አስገኘ። የንጉሠ ነገሥቱ ዓላማም ቢሆን ሃይማኖታዊ መቻቻልን መፍጠር እንጂ ሃይማኖታዊ እውነትን ፈልጎ ማግኘት ስላልሆነ ከዚህ የተለየ ውጤት እንደሚገኝ መጠበቅ አይቻልም። ደግሞም ቆስጠንጢኖስ የአረማዊ እምነት ተከታዮች ገዥ ነው። ሁለቱንም ሃይማኖታዊ ጎራዎች ለማስደሰት ሲል “በአጠቃላይ በድርጊቶቹና በመንግሥታዊ ጉዳዮች ረገድ ሆን ብሎ ግልጽ ያልሆነ አቋም” ይዞ ይንቀሳቀስ እንደነበረ አንድ የታሪክ ምሁር ጽፈዋል።

ቆስጠንጢኖስ የክርስትና ደጋፊ እንደሆነ ቢናገርም በአረማዊ አምልኮ ሥርዓቶች መካፈሉን አላቆመም። ለምሳሌ፣ እንደ ኮከብ ቆጠራና ሟርት ባሉት መናፍስታዊ ድርጊቶች ይካፈል ነበር፤ እነዚህ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያወግዛቸው ድርጊቶች ናቸው። (ዘዳግም 18:10-12) በሮም በሚገኘው የቆስጠንጢኖስ ቅስት ላይ ንጉሠ ነገሥቱ ለአረማዊ አማልክት መሥዋዕት ሲያቀርብ ይታያል። የፀሐይ አምላክ ምስል በሳንቲሞች ላይ እንዲታተም በማድረግና የፀሐይ አምልኮን በማስፋፋት ለዚህ አምላክ አክብሮት መስጠቱን ቀጥሎ ነበር። በዕድሜው መገባደጃ ላይም ኡምብርያ በምትባል ትንሽ የጣሊያን ከተማ ውስጥ ለቤተሰቡ እና ለእሱ ቤተ መቅደስ እንዲሠራ ብሎም በዚያ የሚያገለግሉ ካህናት እንዲሾሙ እስከ መፍቀድ ደርሷል።

ቆስጠንጢኖስ እስከ 337 ዓ.ም. ይኸውም ሊሞት ጥቂት ቀናት እስኪቀረው ድረስ ተጠምቆ “ክርስቲያን” አልሆነም። ብዙ ምሁራን፣ ቆስጠንጢኖስ ለመጠመቅ ያመነታው በግዛቱ የሚኖሩትን ክርስቲያኖችም ሆነ አረማውያን ፖለቲካዊ ድጋፍ ይዞ ለመቆየት ስለፈለገ እንደሆነ ይናገራሉ። በእርግጥም ያሳለፈው ሕይወትም ሆነ ሊሞት እስኪቃረብ ድረስ ሳይጠመቅ መኖሩ በክርስቶስ እንደሚያምን የሚናገረው ከልቡ ስለመሆኑ ጥርጣሬ እንዲፈጠር ያደርጋል። ይሁን እንጂ ስለ አንድ ነገር እርግጠኛ መሆን እንችላለን፦ ቆስጠንጢኖስ ሕጋዊ እውቅና የሰጣት ቤተ ክርስቲያን በፖለቲካም ሆነ በሃይማኖት ረገድ ኃያል ሆናለች፤ ቤተ ክርስቲያኒቷ ለክርስቶስ ጀርባዋን ሰጥታ ከዓለም ጋር ተወዳጅታለች። ኢየሱስ ተከታዮቹን አስመልክቶ “እኔ የዓለም ክፍል እንዳልሆንኩ ሁሉ እነሱም የዓለም ክፍል [አይደሉም]” በማለት ተናግሯል። (ዮሐንስ 17:14) የዓለም ክፍል ከሆነችው ከዚህች ቤተ ክርስቲያን፣ ቁጥር ሥፍር የሌላቸው ሃይማኖታዊ ቡድኖች ወጥተዋል።

ታዲያ ይህ ታሪክ ለእኛ ምን ትርጉም አለው? የማንኛውንም ቤተ ክርስቲያን ትምህርት ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር ሳንመረምር ትክክል እንደሆነ አድርገን መቀበል አይገባንም።—1 ዮሐንስ 4:1

a ቆስጠንጢኖስ የክርስትናን እምነት የተቀበለው ከልቡ ስለመሆኑ ብዙዎች ጥያቄ ያነሳሉ፤ አንድ የማመሳከሪያ ጽሑፍ እንደሚገልጸው እንዲህ ያለ ጥያቄ እንዲነሳ በተወሰነ መጠን ምክንያት የሆነው “በግዛት ዘመኑ መገባደጃ ላይ ሳይቀር አረማዊ የአምልኮ ሥርዓቶች እንዲካሄዱ በመፍቀዱ” ነው።

አጭር መረጃ

  • ቆስጠንጢኖስ በ306 ዓ.ም. የምዕራቡ የሮም ግዛት ንጉሠ ነገሥት ሆነ። ከ324 እስከ 337 ባሉት ዓመታት ደግሞ የምሥራቁም ሆነ የምዕራቡ ግዛት ብቸኛ ንጉሠ ነገሥት ነበረ።

  • ቆስጠንጢኖስ፣ የክርስቲያኖች አምላክ በሕልም ወይም በራእይ እንደተገለጠለትና በጦርነት እንደሚረዳው ቃል እንደገባለት ይናገር ነበር።

  • ቆስጠንጢኖስ በአንድ ውጊያ ላይ ድል የተቀዳጀው በአምላክ እርዳታ እንደሆነ ስለተሰማው “በሮም ከተማ ብዙ ሰው በሚተላለፍበት አደባባይ” ላይ በሚገኘው የራሱ ሐውልት እጅ ላይ የመስቀል ቅርጽ ያለው ጦር እንዲደረግ “ወዲያውኑ ትእዛዝ ሰጥቷል።”—ፖል ኬሬስቴሽ፣ የታሪክ ምሁር

  • ቆስጠንጢኖስ ፖንቲፌክስ ማክሲሞስ (ሊቀ ካህን ማለት ነው) የሚል የአረማዊ አምልኮ የማዕረግ ስም የነበረው ሲሆን በግዛቱ ውስጥ በሚገኙ ሃይማኖቶች ሁሉ ላይ የበላይ እንደሆነ ያስብ ነበር።

የቆስጠንጢኖስ ቅስት

የቆስጠንጢኖስ ቅስት በውጊያ ላይ ላገኘው ድል መታሰቢያ ነው

  • “አንድ ጥሩ ንጉሠ ነገሥት፣ ጥሩ ክርስቲያን ቢሆን እንኳ፣ ከአምላክ ወይም ከሥልጣኑ አንዱን ለመምረጥ መገደዱ አይቀርም። ቆስጠንጢኖስ ዙፋን ላይ ከተቀመጠ ብዙም ስላልቆየ የሥልጣን ጥማቱ ገና አልረካም፤ ሥልጣኑን ላለማጣትም ቢሆን ብዙ ኃጢአት ውስጥ መዘፈቅ ነበረበት።”—ሪቻርድ ሩበንስታይን፣ የግጭት አፈታትና የሕዝባዊ ጉዳዮች ፕሮፌሰር

  • “ቆስጠንጢኖስ ክርስትናን የተቀበለው ከልቡ ስለመሆኑ ጥያቄ እስካልተነሳ ድረስ፣ ቢያንስ ቢያንስ በዕድሜው መገባደጃ አካባቢ ክርስቲያን እንደነበረ ጥርጥር የለውም።”—ፖል ኬሬስቴሽ፣ የጥንታዊ ግሪኮችና ሮማውያን ታሪክ ፕሮፌሰር

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ