የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 7/14 ገጽ 4
  • መከራ ሲደርስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መከራ ሲደርስ
  • ንቁ!—2014
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መግቢያ
    ንቁ!—2020
  • የደረሰብኝን አሳዛኝ ሁኔታ መቋቋም የምችለው እንዴት ነው?
    የወጣቶች ጥያቄ
  • የአቀራረብ ናሙናዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2014
  • መከራ ሲያጋጥማችሁ
    ደስተኛ ቤተሰብ ሊኖርህ ይችላል
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2014
g 7/14 ገጽ 4
1. ከአንድ የተፈጥሮ አደጋ በኋላ የፍርስራሽ ክምር፤ 2. የሆስፒታል አልጋ፤ 3. የመኪና ግጭት

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ | መከራ ሲደርስብህ​—መቋቋም የምትችለው እንዴት ነው?

መከራ ሲደርስ

ይዋል ይደር እንጂ ሁሉም ሰው መከራ ይደርስበታል። ሁሉ ነገር የተሟላላቸው የሚመስሉ ሰዎችም እንኳ ከመከራ አያመልጡም።

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦

“ሩጫ ለፈጣኖች፣ ውጊያም ለኀያላን አይደለም፤ እንጀራ ለጥበበኞች፣ ወይም ባለጠግነት ለብልኆች፣ ወይም ሞገስ ለዐዋቂዎች አይሆንም፤ ጊዜና ዕድል [“ያልተጠበቁ ክስተቶች፣” NW] ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል።”—መክብብ 9:11

እንግዲያው ጥያቄው ‘መከራ ያጋጥምህ ይሆን?’ የሚል ሳይሆን ‘መከራ ሲያጋጥምህ ምን ታደርጋለህ?’ የሚለው ነው። ለምሳሌ፦

  • በተፈጥሮ አደጋ ንብረትህ በሙሉ ቢወድምብህስ?

  • ለሕይወት የሚያሰጋ በሽታ እንዳለብህ ቢነገርህስ?

  • የምትወደውን ሰው በሞት ብታጣስ?

የዚህ መጽሔት አዘጋጆች የሆኑት የይሖዋ ምሥክሮች፣ መከራ ቢደርስብህ ሁኔታውን እንድትቋቋመው አልፎ ተርፎም ስለ ወደፊቱ ጊዜ ጠንካራ ተስፋ እንዲኖርህ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚረዳህ ያምናሉ። (ሮም 15:4) ለዚህ ምሳሌ የሚሆኑ ሦስት ተሞክሮዎችን እስቲ እንመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ