መግቢያ
ሁሉም ሰው በሕይወቱ ውስጥ መከራ ያጋጥመዋል፤ ለምሳሌ የሕመም፣ የድንገተኛ አደጋ፣ የተፈጥሮ አደጋ ወይም የወንጀል ሰለባ ሊሆን ይችላል።
በዚህ ወቅት ሰዎች መልስ ማግኘት ይፈልጋሉ።
አንዳንዶች ሰዎች፣ መከራ የሚደርስባቸው በዕድላቸው ምክንያት እንደሆነና ችግሩን ማስቀረት የሚቻልበት መንገድ እንደሌለ ይናገራሉ።
ሌሎች ደግሞ መከራ የሚደርስባቸው ከዓመታት በፊት ወይም በቀድሞ ሕይወታቸው በሠሩት መጥፎ ነገር የተነሳ እንደሆነ ያምናሉ።
ብዙውን ጊዜ ሰዎች መከራ ሲደርስባቸው የተለያዩ ጥያቄዎች ይፈጠሩባቸዋል።