የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 1/15 ገጽ 6
  • ሊመረመር የሚገባው መልስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሊመረመር የሚገባው መልስ
  • ንቁ!—2015
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሕይወት እንዴት ጀመረ?
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
  • የይሖዋ ምሥክሮች ሁሉም ነገሮች የተፈጠሩት ቃል በቃል በስድስት ቀናት ውስጥ ነው ብለው ያምናሉ?
    ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች
  • ሕይወት እንዴት ጀመረ?
    ንቁ!—2015
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይነግረናል?
    ንቁ!—2021
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2015
g 1/15 ገጽ 6
የተከፈተ መጽሐፍ ቅዱስ

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ | ሕይወት እንዴት ጀመረ?

ሊመረመር የሚገባው መልስ

ብዙ ሰዎች ማስረጃዎቹን ከመረመሩ በኋላ ሕይወት የላቀ የማሰብ ችሎታ ካለው አካል እንደተገኘ ደምድመዋል። በአንድ ወቅት አምላክ የለሽነትን በጥብቅ ይደግፉ የነበሩትና የፍልስፍና ፕሮፌሰር የሆኑት አንተኒ ፍሉ ለዚህ ምሳሌ ይሆኑናል። እኚህ ምሁር ሕይወት እጅግ ውስብስብ መሆኑን ሲገነዘቡና አጽናፈ ዓለም ስለሚመራበት ሕግ ሲያውቁ አመለካከታቸውን ለውጠዋል። የጥንት ፈላስፎችን አመለካከት በመጥቀስ “የትም ያድርሰን የት ማስረጃው ወደሚመራን መሄድ አለብን” በማለት ጽፈዋል። በመሆኑም ፕሮፌሰር ፍሉ ማስረጃው የመራቸው፣ ‘ፈጣሪ አለ’ ወደሚለው መደምደሚያ ነው።

ቀደም ሲል በነበረው ርዕስ ላይ የተጠቀሱት ዠራርድም ተመሳሳይ ወደሆነ ድምዳሜ ደርሰዋል። ከፍተኛ ትምህርት የተከታተሉና በነፍሳት ጥናት ዘርፍ የተሰማሩ ቢሆንም እንዲህ ብለዋል፦ “ሕይወት የተገኘው ሕይወት ከሌለው ነገር በአጋጣሚ እንደሆነ የሚያሳይ አንድም ማስረጃ አላገኘሁም። ሕይወት ባላቸው ነገሮች ላይ የሚታየው ሥርዓታማነትና ውስብስብነት አንድ አደራጅና ንድፍ አውጪ ሊኖር እንደሚገባ አሳምኖኛል።”

አንድ ሰው የአንድን ሠዓሊ ሥራዎች በመመርመር ስለ ሠዓሊው ሊያውቅ እንደሚችል ሁሉ ዠራርድም ተፈጥሮን በመመርመር የፈጣሪን ባሕርያት ሊያስተውሉ ችለዋል። በተጨማሪም ዠራርድ ፈጣሪ ያስጻፈው መጽሐፍ እንደሆነ የሚታመነውን መጽሐፍ ቅዱስን ጊዜ ወስደው መርምረዋል። (2 ጢሞቴዎስ 3:16) ይህን በማድረጋቸውም ከሰው ልጆች ታሪክ ጋር በተያያዘ ለሚነሱ ጥያቄዎች የሚያረኩ መልሶችን አግኝተዋል፤ እንዲሁም በዛሬው ጊዜ በሰው ልጆች ፊት ለተደቀኑ ችግሮች መፍትሔው ምን እንደሆነ ተረድተዋል። በመሆኑም መጽሐፍ ቅዱስም ቢሆን የላቀ የማሰብ ችሎታ ያለው አካል ያስጻፈው መጽሐፍ መሆኑን ሊያምኑ ችለዋል።

በእርግጥም የመጽሐፍ ቅዱስ መልሶች ሊመረመሩ የሚገባቸው ናቸው፤ ዠራርድም ይህን ተገንዝበዋል። አንተም መልሶቹን እንድትመረምር እናበረታታሃለን።

ይህን ታውቅ ነበር?

መጽሐፍ ቅዱስ ፀረ ሳይንስ አይደለም። እንዲያውም ሰዎች ተፈጥሮን እንዲመረምሩ ያበረታታል። (ኢሳይያስ 40:26) መጽሐፍ ቅዱስ የሳይንስ መጽሐፍ ባይሆንም ከተረጋገጡ ሳይንሳዊ እውነቶች ጋር ሙሉ በሙሉ ይስማማል። ለምሳሌ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ክሪኤሽኒስቶች እንደሚሉት ምድር የተፈጠረችው የ24 ሰዓት ርዝመት ባላቸው ስድስት ቀናት ውስጥ እንደሆነ አይናገርም። በዘፍጥረት መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሰው “ቀን” የሚለው ቃል ረጅም ጊዜን ያመለክታል።a

a ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ሕይወት የተገኘው በፍጥረት ነው? የተባለውን ብሮሹር ተመልከት፤ ብሮሹሩ www.jw.org/am ላይም ይገኛል።

መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረው . . .

ሕይወት የሚገኘው ሕይወት ካለው ነገር ብቻ ነው። “የሕይወት ምንጭ ከአንተ [ከአምላክ] ዘንድ ነው።”—መዝሙር 36:9

አምላክ ዕፀዋትንም ሆነ እንስሳትን የፈጠረው “እንደየወገናቸው” ነው። (ዘፍጥረት 1:11, 12, 21, 24, 25) መጽሐፍ ቅዱስ ‘ወገን’ ሲል በዚያ ወገን ውስጥ የሚኖሩትን ዝርያዎች የሚገድብ አይደለም። በመሆኑም በአንድ ወገን ውስጥ በተወሰነ መጠን የሚለያዩ ዝርያዎች ሊኖሩ ይችላሉ።

አምላክ የሰው ልጆችን የፈጠረው የእሱን ባሕርያት ማንጸባረቅ እንዲችሉ አድርጎ ነው። ከእነዚህ ባሕርያት መካከል ፍቅር፣ ጥሩነትና ፍትሕ ይገኙበታል። አምላክ “ሰውን በመልካችን፣ በአምሳላችን እንሥራ” ብሏል።—ዘፍጥረት 1:26

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ