የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 6/15 ገጽ 10-11
  • ጋሊልዮ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጋሊልዮ
  • ንቁ!—2015
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሳይንስና ሃይማኖት
  • “ቢሆንም ትንቀሳቀሳለች!”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • የጋሊልዮና የቤተ ክርስቲያን ግጭት
    ንቁ!—2003
  • በሳይንስና በሃይማኖት መካከል የተፈጠረ ግጭት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
  • የተሳሳተ ግንዛቤ የተሰጠው መጽሐፍ
    ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2015
g 6/15 ገጽ 10-11
ጋሊልዮ

የታሪክ መስኮት

ጋሊልዮ

በ14ኛውና በ16ኛው መቶ ዘመን መካከል የነበሩ አውሮፓውያን የሳይንስ ሊቃውንትና ፈላስፎች የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ስለ ጽንፈ ዓለም ከምታስተምረው ትምህርት ጋር የሚጋጭ አመለካከት ማስፋፋት ጀመሩ። ጽንፈ ዓለምን በተመለከተ የተለየ አመለካከት ይዘው ብቅ ካሉት ሰዎች አንዱ ጋሊልዮ ጋሊሌ ነበር።

ከጋሊልዮ ዘመን በፊት ብዙ ሰዎች ፀሐይ፣ ፕላኔቶችና ከዋክብት በምድር ዙሪያ ይዞራሉ ብለው ያምኑ ነበር። ይህ አመለካከት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ከምታስተምራቸው ነገሮች አንዱ ነበር።

ይሁን እንጂ ጋሊልዮ በቴሌስኮፕ አማካኝነት ሰፊ ተቀባይነት ከነበረው ሳይንሳዊ ትምህርት ጋር የሚቃረን ነገር ተመለከተ። ለምሳሌ ያህል፣ ነቁጠ ፀሐይ (ሰንስፖትስ) በመባል የሚታወቁት በፀሐይ አካል ላይ የሚገኙት ነጠብጣቦች ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀሱ ተመለከተ፤ ይህም ፀሐይ በራሷ ዛቢያ ላይ እንደምትዞር እንዲያስተውል አስቻለው። እንደነዚህ ያሉ ግኝቶች የሰው ልጆች ስለ ጽንፈ ዓለም ያላቸው ግንዛቤ በእጅጉ እንዲሰፋ አስችለዋል፤ ሆኖም ጋሊልዮ ከካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጋር ፊት ለፊት እንዲጋጭ አድርገውታል።

ሳይንስና ሃይማኖት

ጋሊልዮ ግኝቶቹን ይፋ ሲያደርግ

ከተወሰኑ አሥርተ ዓመታት በፊት ፖላንዳዊው የሥነ ፈለክ ተመራማሪ ኒኮላውስ ኮፐርኒከስ ምድር በፀሐይ ዙሪያ ትዞራለች የሚለውን ጽንሰ ሐሳብ ማስፋፋት ጀምሮ ነበር። ጋሊልዮ፣ ኮፐርኒከስ ስለ ጠፈር አካላት እንቅስቃሴ ያደረገውን የምርምር ሥራ ካጠና በኋላ ከዚህ ጽንሰ ሐሳብ ጋር የሚስማማ መረጃ ሰበሰበ። መጀመሪያ ላይ ጋሊልዮ ስድብና ፌዝ እንዳይደርስበት በመፍራት ያስተዋላቸውን ነገሮች ይፋ አላወጣም ነበር። ከጊዜ በኋላ ግን በቴሌስኮፕ አማካኝነት የተመለከታቸውን ነገሮች ለራሱ ብቻ ይዞ መቀመጥ ስላልቻለ ግኝቶቹን ለሕዝብ አሳወቀ። አንዳንድ የሳይንስ ሊቃውንት ጋሊልዮ ያቀረባቸውን የመከራከሪያ ነጥቦች የተቃወሙ ከመሆኑም ሌላ ቀሳውስት በየመድረኮቻቸው ጋሊልዮን መንቀፍ ጀመሩ።

በ1616 “የዘመኑ ግንባር ቀደም ሃይማኖታዊ ሊቅ” የሚባሉት ካርዲናል ቤላርመን፣ በኮፐርኒከስ አመለካከት ላይ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አዲስ ድንጋጌ እንዳወጣች ለጋሊልዮ ነገሩት። ጋሊልዮ ይህን ድንጋጌ እንዲቀበል አጥብቀው አሳሰቡት፤ ከዚያ በኋላ ጋሊልዮ ለዓመታት ምድር በፀሐይ ዙሪያ ትዞራለች ብሎ በአደባባይ መከራከሩን አቆመ።

በ1623 የጋሊልዮ ወዳጅ የነበሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ኧርበን ስምንተኛ ሥልጣን ያዙ። በመሆኑም በ1624 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በ1616 የወጣውን ድንጋጌ እንዲሽሩ ጋሊልዮ ጠየቃቸው። ኧርበን ግን ጋሊልዮ እርስ በርሳቸው ይጋጩ የነበሩትን የኮፐርኒከስንና የአርስቶትልን ጽንሰ ሐሳቦች ከወገናዊነት ነፃ በሆነ ሁኔታ እንዲያብራራ ጠየቁት።

ከዚያም ጋሊልዮ ዳያሎግ ኦን ዘ ግሬት ወርልድ ሲስተምስ የተባለ መጽሐፍ ጻፈ። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጋሊልዮን ገለልተኛ እንዲሆን ቢያዙትም መጽሐፉ የኮፐርኒከስን ድምዳሜ የሚደግፍ ነበር። ብዙም ሳይቆይ ጋሊልዮን ይቃወሙ የነበሩ ሰዎች መጽሐፉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱን እንደሚሳደብ መናገር ጀመሩ። ጋሊልዮም በመናፍቅነት ስለተከሰሰና ብዙ ሥቃይ እንደሚደርስበት ስለተዛተበት የኮፐርኒከስን ትምህርቶች ለመካድ ተገደደ። በ1633 የሮም ኢንኩዊዚሽን ይባል የነበረው ፍርድ ቤት ዕድሜ ልክ የቁም እስር ፈረደበት፤ ጽሑፎቹም እንዲታገዱ ወሰነ። ጋሊልዮ ጥር 8 ቀን 1642 በፍሎረንስ አቅራቢያ በአርቼትሪ በሚገኘው ቤቱ ሞተ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጋሊልዮን ያወገዘችው በስህተት እንደነበረ አምነዋል

በመቶ ለሚቆጠሩ ዓመታት ከጋሊልዮ ሥራዎች አንዳንዶቹ ካቶሊኮች እንዳያነቧቸው በተከለከሉ መጻሕፍት ዝርዝር ውስጥ ተካትተው ቆይተዋል። ይሁን እንጂ ቤተ ክርስቲያኗ በ1979 የሮም ኢንኩዊዚሽን ከ300 ዓመታት በፊት ወስዶት የነበረውን እርምጃ ዳግመኛ ለማየት ወሰነች። በመጨረሻም በ1992 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጋሊልዮን ያወገዘችው በስህተት እንደነበረ አመኑ።

አጭር መረጃ

  • ጋሊልዮ ጋሊሌ በ1564 ጣሊያን ውስጥ በምትገኘው ጋደል ባለ ሕንፃዋ በምትታወቀው በፒዛ ከተማ ተወለደ። በፓዱዋ ዩኒቨርሲቲ ያስተማረ ሲሆን ከጊዜ በኋላ በፍሎረንስ መሥራትና መኖር ጀመረ።

  • ቴሌስኮፕን የፈለሰፈው ጋሊልዮ ባይሆንም የቴሌስኮፕን የማጉላት አቅም በእጅጉ አሻሽሏል፤ ይህም ጠቀሜታው እንዲጨምር አድርጓል።

  • ጋሊልዮ ስለ ጽንፈ ዓለም ባለው አመለካከት ምክንያት ከቤተ ክርስቲያን ቀኖና በሚያፈነግጡ ሰዎች ላይ ፍርድ ያስተላልፍ በነበረው የካቶሊክ ኢንኩዊዚሽን ሸንጎ ፊት እንዲቀርብ ተደርጓል።

ኢንኩዊዚሽን ጋሊልዮን አሠቃይቶታል?

አንዳንድ የታሪክ ሊቃውንት የሮም ኢንኩዊዚሽን በጋሊልዮ ላይ አካላዊ ሥቃይ እንዳደረሰ ይናገራሉ። የተላለፈበት የፍርድ ብይን የጋሊልዮን ትክክለኛ ዓላማ ለማረጋገጥ “ከባድ ምርመራ” ሊደረግበት እንደሚገባ ይገልጻል። ይህ አባባል እንዲህ ዓይነት ምርመራ የሚደረግበት ሰው “እንደሚሠቃይ” የሚያመለክት ሲሆን ግለሰቡ ቢያንስ “አካላዊ ሥቃይ እንደሚደርስበት መዛትንም” ሊያካትት ይችላል።

በተመርማሪዎች ላይ የሚደርሰው ሥቃይ ደረጃና መጠን እንደሚለያይ ሊቃውንት ይናገራሉ። ይህም የማሠቃያ መሣሪያዎችን ማሳየትን፣ ልብስ ማስወለቅን፣ ጥፍር አድርጎ ማሰርን ወይም በተለያየ መንገድ ማሠቃየትን ሊጨምር ይችላል። በጋሊልዮ ላይ ምን ዓይነት “ከባድ ምርመራ” እንደተደረገበት ግን በእርግጠኝነት አይታወቅም።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ