የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g16 ቁጥር 3 ገጽ 16
  • የጉንዳን አንገት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የጉንዳን አንገት
  • ንቁ!—2016
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የሰሃራው ብርማ ጉንዳን ሙቀት የሚከላከልበት መንገድ
    ንቁ!—2017
  • ካርፔንተር አንት የተባለው ጉንዳን አንቴናውን የሚያጸዳበት መንገድ
    ንድፍ አውጪ አለው?
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2016
  • “ወደ ገብረ ጉንዳን ሂድ”
    ንቁ!—1996
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2016
g16 ቁጥር 3 ገጽ 16

ንድፍ አውጪ አለው?

የጉንዳን አንገት

አንድ ጉንዳን በአፉ ሣር ይዞ

የሜካኒካል ምሕንድስና ባለሙያዎች፣ ጉንዳኖች ባላቸው ከአካላቸው ብዙ እጥፍ የሚበልጥ ክብደት የመሸከም ችሎታ ይደነቃሉ። በዩናይትድ ስቴትስ በሚገኘው የኦሃዮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ያሉ መሐንዲሶች፣ ጉንዳኖች ያላቸውን ይህን ችሎታ ለመረዳት ሲሉ የኮምፒዩተር ሞዴሎችን አዘጋጅተዋል፤ ሞዴሎቹ የጉንዳኖቹን አካል አወቃቀርና ባሕርይ እንዲሁም እንቅስቃሴ የሚያሳዩ ናቸው። ሞዴሎቹ የተሠሩት የጉንዳኖቹን ውስጣዊ የአካል ክፍል የሚያሳይ የራጅ ምስል (ረቂቅ ሲቲ ስካን) እና ጉንዳኖች ከባድ ሸክም ሲሸከሙ ኃይላቸውን የሚጠቀሙበትን መንገድ የሚያሳዩ ምስሎችን በመጠቀም ነው።

የጉንዳኖች አንገት ትልቅ ሚና አለው፤ ምክንያቱም አንድ ጉንዳን በአፉ የሚይዘው ከባድ ሸክም ሙሉ ክብደት የሚያርፈው አንገቱ ላይ ነው። በጉንዳኑ አንገት ውስጥ የሚገኙ ለስላሳ ሕብረ ሕዋሳት በደረቱ አካባቢ (ሰውነቱ) እና በጭንቅላቱ ላይ ካሉት ጠንካራ ድጋፍ ሰጪ አጥንቶች ጋር የተቆላለፉ ናቸው፤ ይህም በታጠፉ እጆች ላይ ጣቶች ከሚቆላለፉበት ሁኔታ ጋር የሚመሳሰል ነው። “ይህ መቆላለፍ ያለው ንድፍና አወቃቀር፣ የአንገቱ መገጣጠሚያ ለሚያከናውነው ተግባር ወሳኝ ነው” በማለት ከተመራማሪዎቹ አንዱ ይናገራል። “የአንገቱ መገጣጠሚያ ይበልጥ ጥንካሬ እንዲኖረው ያደረገው ነገር ጠንካራና ለስላሳ የአካል ክፍሎቹ የተያያዙበት መንገድ ሳይሆን አይቀርም፤ ምናልባትም መገጣጠሚያው ከባድ ሸክም እንዲሸከም የሚያስችለው ይህ ንድፍ ሊሆን ይችላል።” የጉንዳን አንገት እንዴት እንደሚሠራ በግልጽ መታወቁ ለሰው ሠራሽ ሮቦቶች ንድፍ መሻሻል አስተዋጽኦ ሊያበረክት እንደሚችል ተመራማሪዎች ተስፋ ያደርጋሉ።

ታዲያ ምን ይመስልሃል? ውስብስብ በሆነ መንገድ የተቆላለፈው ጠንካራ የጉንዳን አንገት በዝግመተ ለውጥ የተገኘ ነው? ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ