የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g17 ቁጥር 1 ገጽ 16
  • የሰሃራው ብርማ ጉንዳን ሙቀት የሚከላከልበት መንገድ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የሰሃራው ብርማ ጉንዳን ሙቀት የሚከላከልበት መንገድ
  • ንቁ!—2017
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2017
  • የጉንዳን አንገት
    ንቁ!—2016
  • ካርፔንተር አንት የተባለው ጉንዳን አንቴናውን የሚያጸዳበት መንገድ
    ንድፍ አውጪ አለው?
  • “ወደ ገብረ ጉንዳን ሂድ”
    ንቁ!—1996
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2017
g17 ቁጥር 1 ገጽ 16
የሰሃራው ብርማ ጉንዳን

ንድፍ አውጪ አለው?

የሰሃራው ብርማ ጉንዳን ሙቀት የሚከላከልበት መንገድ

የሰሃራው ብርማ ጉንዳን (ካታግሊፊስ ቦምቢሲና) ሙቀትን የመቋቋም ከፍተኛ ችሎታ ካላቸው በየብስ የሚኖሩ ፍጥረታት መካከል አንዱ ነው። ጉንዳኑን የሚመገቡ እንስሳት በጠራራው የሰሃራ ፀሐይ ምክንያት ጥላ ለመፈለግ በሚገደዱበት ወቅት ይህ ጉንዳን ለአጭር ጊዜ ከጉድጓዱ በመውጣት ምግብ ይፈልጋል፤ ከሚመገባቸው ነገሮች መካከል በከባድ ሙቀት የተነሳ የሞቱ ነፍሳት ይገኙበታል።

የሰሃራው ብርማ ጉንዳን ሙቀትን መከላከል እንዲችል ከሚረዱት ነገሮች መካከል ልዩ የሆኑት ፀጉሮቹ ይገኙበታል።

[50] μm

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ ብርማው ጉንዳን ሙቀት እንዲከላከል ከሚረዱት ነገሮች መካከል ሰውነቱ ከላይና ከጎን በኩል ፀጉር ያለው መሆኑ እንዲሁም ከታች በኩል ፀጉር አልባ መሆኑ ይገኙበታል። ጉንዳኑ አብረቅራቂ መልክ እንዲኖረው የሚያደርጉት እነዚህ ፀጉሮች መሃል ለመሃል ተቆርጠው ሲታዩ የሦስት ማዕዘን ቅርጽ ያለው ቱቦ ይመስላሉ። ከላይ በኩል ያሉት ሁለቱ የፀጉሩ ጎኖች ከላይ እስከ ታች በዓይን በማይታዩ ወጣ ገባዎች የተሸፈኑ ሲሆን ሦስተኛው ጎን ግን ልሙጥ ነው። የጉንዳኑ ፀጉር እንዲህ ያለ ንድፍ ያለው መሆኑ ሁለት ጥቅሞች አሉት። አንደኛ ፀጉሮቹ ከፀሐይ የሚመነጨውን በዓይን የማይታይ የሙቀት ጨረር አንጸባርቀው መመለስ እንዲችሉ ይረዳቸዋል። ሁለተኛ ጉንዳኑ ከአካባቢው የወሰደውን ሙቀት ማስወገድ እንዲችል ይረዳዋል። ፀጉር አልባ የሆነው የጉንዳኑ የታችኛው ክፍል ደግሞ ከበረሃማው መሬት የሚመጣውን በዓይን የማይታይ የሙቀት ጨረር አንጸባርቆ ይመልሳል።a

የሰሃራው ብርማ ጉንዳን ፀጉሮች ጎላ ተደርገው ሲታዩ የሦስት ማዕዘን ቅርጽ ያላቸው ትናንሽ ቱቦዎች ይመስላሉ

[10] μm

የሰሃራው ብርማ ጉንዳን ያለው ሙቀት የመከላከል ችሎታ የሰውነቱ ሙቀት ከ53.6 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ እንዳይበልጥ ይከላከልለታል፤ የሰውነቱ የሙቀት መጠን ከዚያ ካለፈ ጉንዳኑ በሕይወት መቆየት አይችልም። ተመራማሪዎች ይህ ትንሽ ፍጥረት ያለውን ችሎታ በመኮረጅ ያለማቀዝቀዣ መሣሪያዎች እርዳታ በራሳቸው የሚያቀዘቅዙ መሣሪያዎችን ለመሥራት ጥረት እያደረጉ ነው።

ታዲያ ምን ይመስልሃል? የሰሃራው ብርማ ጉንዳን ያለው ሙቀት የመከላከል ችሎታ በዝግመተ ለውጥ የተገኘ ነው? ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?

a ጉንዳኑ ሙቀትን እንዲከላከል ከሚረዱት ሌሎች ነገሮች መካከል በሰውነቱ ውስጥ ያሉት ፕሮቲኖች ኃይለኛ ሙቀት ቢኖርም በቀላሉ ወደ አሚኖ አሲድነት የማይቀየሩ መሆኑ፣ ረጃጅም እግሮቹ ሰውነቱ ትኩስ ከሆነው አሸዋ ከፍ እንዲልና በፍጥነት እንዲሮጥ የሚረዱት መሆኑ እንዲሁም አቅጣጫ የማወቅ ችሎታው በፍጥነት ወደ ጉድጓዱ እንዲመለስ የሚረዳው መሆኑ ይገኙበታል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ