የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • be ገጽ 71-ገጽ 73 አን. 3
  • ደብዳቤ መጻፍ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ደብዳቤ መጻፍ
  • በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በደብዳቤ መመሥከር
  • ስለ ደብዳቤው አጻጻፍ ጥቂት እንበል
  • የደብዳቤው መንፈስ
  • የናሙና ደብዳቤ
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2019
  • የደብዳቤ አጻጻፍ
    ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ
  • በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ውጤታማ ደብዳቤ መጻፍ
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2019
  • የጥያቄ ሣጥን
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
be ገጽ 71-ገጽ 73 አን. 3

ደብዳቤ መጻፍ

ደብዳቤ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን አኗኗርና ባሕርይ ለውጧል። ከክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት መካከል አብዛኞቹ በደብዳቤ መልክ የተጻፉ መልእክቶች ነበሩ። ዛሬም በደብዳቤ አማካኝነት አዲስ ክርስቲያኖችን እናንጻለን፣ ከጓደኞቻችን ጋር እንገናኛለን፣ ለየት ያሉ ኃላፊነት የተቀበሉ ወንድሞችንና እህቶችን እናበረታታለን፣ መከራ የደረሰባቸውን እናጽናናለን እንዲሁም ከጉባኤ ሥራዎች ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እንለዋወጣለን።​—⁠1 ተሰ. 1:​1-7፤ 5:​27፤ 2 ጴጥ. 3:​1, 2

ደብዳቤ መጻፍ በምሥክርነቱ ሥራም ትልቅ ድርሻ አለው። ከፍተኛ ጥበቃ በሚደረግባቸው የመኖርያ ሕንፃዎች የሚኖሩ ብዙ ሰዎችን እንደልብ ማነጋገር አስቸጋሪ ነው። ሌሎች ደግሞ ወደ ሌላ አካባቢ ሄደው ለረጅም ጊዜ ስለሚቆዩ ከቤት ወደ ቤት ስንሄድ አናገኛቸውም። አንዳንዶች ደግሞ ያሉት እስር ቤትን ጨምሮ ሰዎችን በቀላሉ ማግኘት በማይቻልባቸው ቦታዎች ነው።

አንዳንድ ጊዜ በሕመም፣ በአስቸጋሪ የአየር ጠባይ ወይም በሰዓት እላፊ ገደብ ምክንያት ከቤትህ መውጣት አትችል ይሆናል። ለዘመድህ ወይም መደበኛ ባልሆነ መንገድ ላነጋገርከው ሰው ተጨማሪ ምሥክርነት ለመስጠት ደብዳቤ መጻፍ ትችል ይሆን? ከጥናቶችህ መካከል ወደ ሌላ አካባቢ የሄደ ይኖር ይሆን? አንድ ደብዳቤ መጻፍህ ብቻ እንኳ መንፈሳዊ ፍላጎቱ እንዳይጠፋ ሊረዳው ይችላል። ወይም ደግሞ በቅርቡ ትዳር ለመሠረቱ፣ ልጅ ለወለዱ ወይም የሚወድዱትን ሰው በሞት ላጡ ሰዎች ደብዳቤ በመጻፍ ተስማሚ የሆነ ቅዱስ ጽሑፋዊ ሐሳብ ልታካፍላቸው የምትችልበት አጋጣሚ ይኖራል።

በደብዳቤ መመሥከር

ለማታውቀው ሰው ለመመሥከር ደብዳቤ ስትጽፍ በመጀመሪያ ራስህን ማስተዋወቅ ይኖርብሃል። በዓለም ዙሪያ በፈቃደኝነት በሚከናወነው ሥራ እየተካፈልህ መሆንህን ማሳወቅ ትፈልግ ይሆናል። ወይም ተስማሚ ሆኖ ካገኘኸው የይሖዋ ምሥክር መሆንህን ግለጽ። በአካል ሄደህ ከማነጋገር ይልቅ ደብዳቤ መጻፍ የመረጥኸው ለምን እንደሆነ ግልጽ አድርግለት። ደብዳቤውን ስትጽፍ በአካል እያነጋገርከው እንዳለህ አድርገህ አስብ። ያም ሆኖ ግን “እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ” በሚለው ምክር መሠረት ስለ ራስህ ምን ያህል መረጃ መስጠት እንዳለብህ አስቀድመህ ልታስብበት ይገባል።​—⁠ማቴ. 10:​16

ሰውዬውን በአካል ብታገኘው ኖሮ ትነግረው የነበረውን ነገር በደብዳቤህ ላይ አስፍር። ማመራመር በተባለው መጽሐፍ ላይ የሚገኝ መግቢያ ወይም በቅርብ በወጣ የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የሚገኝ አቀራረብ ልትጠቀም ትችላለህ። አንድ ጥያቄ አንስተህ እንዲያስብበት ልታደርገው ትችላለህ። አንዳንድ አስፋፊዎች ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎች ያለ ክፍያ መልስ የምንሰጥበት ፕሮግራም እንዳለን በቀጥታ በመግለጽ ከማስጠኛ ጽሑፎቻችን መካከል ከአንዱ ላይ የተወሰኑ ርዕሶችን ይጠቅሳሉ። ምሥክርነት ለመስጠት ተብሎ የሚጻፍ ደብዳቤ ምን መልክ ሊኖረው እንደሚችል የሚያሳይ ናሙና በገጽ 73 ላይ ይገኛል። ከዚህ ናሙና አንዳንድ ሐሳቦችን ልታገኝ ብትችልም የምትጽፈውን ደብዳቤ ይዘት መለዋወጥ ጥሩ ነው። አለበለዚያ ግን ሰዎቹ በተደጋጋሚ ተመሳሳይ ደብዳቤ ሊደርሳቸው ይችላል።

አንዳንድ ሰዎች ከማያውቁት ሰው የሚደርሳቸውን ረጅም ደብዳቤ ማንበብ አይፈልጉም። ስለዚህ ደብዳቤህን አጠር ማድረጉ ጥበብ ይሆናል። ሰውዬው ከመሰላቸቱ በፊት ሐሳብህን መቋጨት ይኖርብሃል። በመንግሥት አዳራሽ በሚደረገው ስብሰባ ላይ እንዲገኝ የስብሰባ መጋበዣ ወረቀት አያይዘህ መላኩ ተገቢ ይሆናል። አንድ ትራክት፣ ብሮሹር አለዚያም መጠበቂያ ግንብ ወይም ንቁ! ጨምረህ በመላክ ፍላጎት ካለው እነዚህን ጽሑፎች በየጊዜው ማግኘት እንደሚችል ግለጽለት። ወይም ደግሞ የጀመራችሁትን ውይይት ለመቀጠል እቤቱ ድረስ መሄድ ትችል እንደሆነ ጠይቀው።

ስለ ደብዳቤው አጻጻፍ ጥቂት እንበል

[በገጽ 73 ላይ የሚገኝ ሣጥን]

ለናሙና የቀረበውን ደብዳቤ ተመልከት። የሚከተሉትን ነጥቦች ልብ በል:- (1) በንጽሕና የተጻፈ ነው። (2) ተቀባዩ ፖስታው ቢጠፋበት እንኳ የላኪው ስምና አድራሻ ይኖረዋል። (3) የደብዳቤው ዓላማ በመግቢያው አንቀጽ ላይ ግልጽና ቀጥተኛ በሆነ መንገድ ሰፍሯል። (4) እያንዳንዱ ዋና ሐሳብ ራሱን በቻለ አንድ አንቀጽ ውስጥ ሰፍሯል። (5) ደብዳቤው በጣም በተራቀቁ ቃላትም የተጻፈ አይደለም፤ በጣምም ቅልል ያለ አይደለም። ይህ ከተጻፈበት ዓላማ ጋር የሚስማማ ነው።

አንድ የጉባኤ ጸሐፊ ለቅርንጫፍ ቢሮው እንደሚልከው ባለ ደብዳቤ ላይ የጉባኤው ስም፣ የጸሐፊው ስም፣ የፖስታ አድራሻው እንዲሁም ቀኑ ሊሰፍር ይገባል። በተጨማሪም የደብዳቤው ተቀባይ የሆነው ግለሰብ ወይም ድርጅት ስምና አድራሻ ይሰፍራል። ከዚያም ተገቢው የመግቢያ ሰላምታ ይከተላል። በደብዳቤው መደምደሚያ ላይ ከፊርማው በፊት “ከሰላምታ ጋር” የሚል መግለጫ ይኖራል። ፊርማው በእጅ የተጻፈ ሊሆን ይገባል።

ማንኛውንም ደብዳቤ ስትጽፍ የፊደል፣ የሰዋስውና የሥርዓተ ነጥብ ግድፈት እንዲሁም ስርዝ ድልዝ እንዳይኖር መጠንቀቅ ይኖርብሃል። ይህን ማድረግህ ደብዳቤህም ሆነ የያዘው መልእክት አክብሮት እንዲያገኝ ያስችላል።

በፖስታው ሽፋን ላይ ሁልጊዜ የላኪ አድራሻ ሊሰፍር ይገባል። የራስህ የፖስታ አድራሻ ቢሆን ይመረጣል። ለማታውቃቸው ሰዎች በደብዳቤ ምሥክርነት በምትሰጥበት ጊዜ የራስህን አድራሻ መስጠቱን ጥበብ ሆኖ ካላገኘኸው የመንግሥት አዳራሻችሁን ፖስታ ሣጥን ቁጥር መጠቀም ትችል እንደሆነ የጉባኤህን ሽማግሌዎች ጠይቅ። የመጠበቂያ ግንብ ማኅበሩን አድራሻ ለዚህ ዓላማ በፍጹም መጠቀም አይገባም። የማኅበሩን አድራሻ መጠቀም ደብዳቤው ከማኅበሩ ቢሮ የተላከ ስለሚያስመስል ግራ መጋባት ሊፈጥር ይችላል። ደብዳቤው ምንም የላኪ አድራሻ ሳይኖረው ጽሑፍ ጨምሮ መላክም ቢሆን ከማኅበሩ የተላከ ሊያስመስል ይችላል።

በተለይ ጽሑፍ ጨምረህ ከላክህ በቂ የፖስታ አገልግሎት ክፍያ ማከናወንህን አረጋግጥ። በብዙ አገሮች መጽሔት ወይም ብሮሹር ተጨምሮ ሲላክ የፖስታ አገልግሎት ክፍያው ለአንድ ደብዳቤ ከሚጠየቀው እጅግ የሚበልጥ ይሆናል።

የደብዳቤው መንፈስ

ደብዳቤውን ጽፈህ ስትጨርስ ይዘቱ ምን እንደሚመስል ለማየት እንደገና አንብበው። የደብዳቤው መንፈስ ምን ይመስላል? ወዳጃዊ በሆነና ማስተዋል በተንጸባረቀበት መንገድ የቀረበ ነው? ከሌሎች ጋር ባለን ግንኙነት ፍቅርና ደግነት ማሳየት እንፈልጋለን። (ገላ. 5:​22, 23) ደብዳቤህ አሉታዊ መንፈስ እንደሚያንጸባርቅ ከተሰማህ የቃላቱን አቀማመጥ አስተካክል።

ደብዳቤ የማይገባበት ቦታ የለም። ይህ በራሱ ለአገልግሎት ውጤታማ መሣሪያ እንዲሆን ያደርገዋል። የምትጽፈው ደብዳቤ ስለ አንተም ሆነ ስለ አቋምህ ሊናገር ስለሚችል ይዘቱ ምን ዓይነት እንደሆነ፣ ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆኑን እንዲሁም በአንባቢው ላይ የሚያሳድረው ስሜት ምን እንደሆነ ልታስብበት ይገባል። አንድ ሰው በሕይወት ጎዳና ላይ መጓዝ እንዲጀምር ለመርዳትና በዚያ እንዲቀጥል ለማበረታታት ደብዳቤ ትልቅ ሚና ሊጫወት ይችላል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ