የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb19 መጋቢት ገጽ 5
  • በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ውጤታማ ደብዳቤ መጻፍ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ውጤታማ ደብዳቤ መጻፍ
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2019
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ደብዳቤ መጻፍ
    በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
  • የደብዳቤ አጻጻፍ
    ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ
  • የጥያቄ ሣጥን
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • የJW.ORG አድራሻ ካርድን በሚገባ እየተጠቀማችሁበት ነው?
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ (2016)
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2019
mwb19 መጋቢት ገጽ 5

ክርስቲያናዊ ሕይወት

በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ውጤታማ ደብዳቤ መጻፍ

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ሐዋርያው ጳውሎስ የእምነት አጋሮቹን ለማበረታታት ከጻፋቸው 14 ደብዳቤዎች አንዱ 1 ቆሮንቶስ ነው። ደብዳቤ በምንጽፍበት ጊዜ፣ በሚገባ የታሰበባቸውን ቃላት መርጠን ለመጠቀም አጋጣሚ ይኖረናል፤ ተቀባዩም ቢሆን ደብዳቤውን ደጋግሞ ማንበብ ይችላል። ደብዳቤ ለዘመዶቻችንና ለሌሎች የምናውቃቸው ሰዎች ለመመሥከር የሚያስችል ጥሩ ዘዴ ነው። በተጨማሪም በአካል አግኝተን ልናነጋግራቸው ላልቻልናቸው ሰዎች ምሥራቹን ለማካፈል የሚያስችል ውጤታማ መንገድ ነው። ለምሳሌ ያህል፣ ምሥራቹ ሲነገረው ፍላጎት ያሳየ አንድ ሰውን በድጋሚ ቤቱ ለማግኘት ተቸግረን ሊሆን ይችላል። በሌላ በኩል ደግሞ በክልላችን ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ሰዎች የሚኖሩት ከፍተኛ ጥበቃ በሚደረግባቸው ሕንፃዎች፣ በቀላሉ መግባት በማይቻልባቸው ግቢዎች አሊያም ርቀው በሚገኙ አካባቢዎች ሊሆን ይችላል፤ በዚህም ምክንያት ሰዎቹን ማግኘት አስቸጋሪ ይሆናል። ታዲያ ለሌሎች በተለይም ለማናውቃቸው ሰዎች ደብዳቤ ስንጽፍ የትኞቹን ነገሮች ግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርብናል?

ሐዋርያው ጳውሎስ ደብዳቤ ሲጽፍ

ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?

  • አንዲት እህት ደብዳቤያቸው ላይ ምን ብለው እንደሚጽፉ ቆም ብለው ሲያስቡ

    ግለሰቡን በአካል ብታገኘው ኖሮ የምትነግረውን ነገር በደብዳቤህ ላይ አስፍር። በደብዳቤው መጀመሪያ ላይ ራስህን አስተዋውቅ፤ እንዲሁም የደብዳቤህን ዓላማ በግልጽ ተናገር። ከዚያም የግለሰቡን ትኩረት የሚስብ አንድ ጥያቄ ካነሳህ በኋላ ድረ ገጻችንን እንዲመለከት ልትጋብዘው ትችላለህ። ሰዎችን በቤታቸው መጽሐፍ ቅዱስ ስለምናስጠናበት ዝግጅት ንገረው፤ በተጨማሪም በማስጠኛ ጽሑፎቻችን ላይ የሚገኙ አንዳንድ ምዕራፎችን ጥቀስለት። ከደብዳቤው ጋር መጋበዣ፣ ትራክት አሊያም የአድራሻ ካርድ መላክ ትችላለህ

  • ደብዳቤህ እጥር ምጥን ያለ ይሁን። ግለሰቡ እንዳይሰለቸው ደብዳቤውን አታስረዝመው።​—የናሙና ደብዳቤውን ተመልከት

  • ደብዳቤህ ስህተት እንዳይኖረው ደግመህ አንብበው፤ በተጨማሪም ለማንበብ የማያስቸግር፣ ወዳጃዊ ስሜት የሚንጸባረቅበት፣ አንባቢውን ቅር የማያሰኝ እንዲሁም አዎንታዊ መልእክት የያዘ መሆኑን አረጋግጥ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ