መዝሙር 101
የመንግሥቱን እውነት ማሳወቅ
በወረቀት የሚታተመው
1. ካሁን በፊት ባዝነን ነበር፤
እውነተኛው መንገድ ጠፍቶን።
አምላክ ግን አበራልን፤
የመንግሥቱ እውነት ታየን።
የሱን ፈቃድ ስላወቅን፣
ላገዛዙ ታዛዦች ነን፤
ዝናውን ’ናውጃለን፤
ቅዱስ ስሙን እናሳውቃለን።
በየቤቱም፣ በመንገድም፣
የትም ቦታ እንሰብካለን።
ለሰው ሁሉ ’ናስተምራለን፤
ነፃ ’ሚያወጣውን እውነት።
ቃሉን ባለም እናስፋፋ፤
አምልኮውም ይታይ ልቆ።
ባንድነት እናገልግል፤
አምላክ በቃ ’ስኪለን ጊዜው አልቆ።