መዝሙር 110
የአምላክ ድንቅ ሥራዎች
በወረቀት የሚታተመው
(መዝሙር 139)
1. አምላክ መቀመጥ፣ መራመዴን፣
ታውቀዋለህ መተኛት፣ መንቃቴን።
የውስጤን ሐሳብ ትመረምራለህ፤
ንግግሬን አካሄዴን ታውቀዋለህ።
አየኸኝ ስፈጠር በስውር፤
አጥንቶቼን አውቀሃል በቁጥር።
ያካሌ ክፍል በሙሉ ተጽፏል።
ሥራህ ያስደንቃል፣
ኃይልህ ያስደምማል።
ጥበብህ ድንቅ ከማሰብም በላይ ነው፤
ነፍሴም ይህን በውል ነው ’ምታውቀው።
ጨለማ ውጦኛል ብዬ ባስብም፣
ያንተ መንፈስ ያገኘኛል እዚያም።
ካንተ ወዴት እሸሸጋለሁ?
መሰወሪያ፣ መደበቂያው የት ነው?
በከፍታም ሆነ በጥልቁ ሲኦል፣
በጨለማም፣ በባሕርም ቦታ የለም።