መዝሙር 46
ይሖዋ ንጉሣችን ነው!
በወረቀት የሚታተመው
1. ያህን በደስታ አወድሱት፤
ያምላክን ጽድቅ ያውጃሉ ሰማያት።
ከፍ እና’ርገው ስሙን፤ በደስታ እንዘምር፤
ሥራውን እናስብ ዘወትር።
(አዝማች)
ሰማይም ይደሰት፤ ምድርም እልል ትበል፤
ይሖዋ ንጉሣችን ሆኗል!
ሰማይም ይደሰት፤ ምድርም እልል ትበል፤
ይሖዋ ንጉሣችን ሆኗል!
2. ዓለም ይወቀው የሱን ግርማ፤
ማዳኑን ንገሩ፣ ሁሉም ሰው ይስማ።
ይሖዋ ንጉሥ ነው፤ ይገባል ሊመለክ።
በዙፋኑ ፊት እንንበርከክ።
(አዝማች)
ሰማይም ይደሰት፤ ምድርም እልል ትበል፤
ይሖዋ ንጉሣችን ሆኗል!
ሰማይም ይደሰት፤ ምድርም እልል ትበል፤
ይሖዋ ንጉሣችን ሆኗል!
3. ጻድቅ መንግሥቱ ተቋቁሟል፤
ልጁንም ሾሞታል፤ ሥልጣን ሰጥቶታል።
ክብር የሚገባው ይሖዋ ብቻ ነው፤
አማልክት ይስገዱለት አፍረው።
(አዝማች)
ሰማይም ይደሰት፤ ምድርም እልል ትበል፤
ይሖዋ ንጉሣችን ሆኗል!
ሰማይም ይደሰት፤ ምድርም እልል ትበል፤
ይሖዋ ንጉሣችን ሆኗል!
(በተጨማሪም 1 ዜና 16:9ን፣ መዝ. 68:20፤ መዝ. 97:6, 7ን ተመልከት።)