መዝሙር 66
ይሖዋን በሙሉ ነፍስ ማገልገል
በወረቀት የሚታተመው
1. ይሖዋ ሆይ፣ ሉዓላዊው፣
አንተን ልውደድህ ላምልክህም።
በሙሉ ነፍስ ላንተ ልደር፤
ታምነህብኛል አልክድህም።
ሕግጋትህን አከብራለሁ፤
በደስታ እታዘዛለሁ።
(አዝማች)
ይሖዋ ሆይ፣ ይገባሃል፤
በሙሉ ነፍስ አንተን ላገልግል።
2. ኮከብ፣ ጨረቃና ምድር፣
ይናገራሉ ያንተን ክብር።
ራሴን ላንተ እሰጣለሁ፤
ስምህንም አሳውቃለሁ።
ላገለግልህ ወስኛለሁ፣
አዎ፣ ቃሌን ’ጠብቃለሁ።
(አዝማች)
ይሖዋ ሆይ፣ ይገባሃል፤
በሙሉ ነፍስ አንተን ላገልግል።