መዝሙር 85
አንዳችን ሌላውን መቀበል
በወረቀት የሚታተመው
(ሮም 15:7)
1. ዛሬ ከኛ ጋር የተገኛችሁ፣
ደስ ብሎናል ስለመጣችሁ።
ቃሉን ’ንድንሰማ አምላክ ጋብዞናል፤
ጥሪውን አክብረን ቤቱ ተገኝተናል።
2. ይሖዋ ሰጠን ውድ ወንድሞችን፤
ሁሌም በደስታ ’ሚቀበሉን።
እናክብራቸው እንዲህ ያሉትን፤
እኛም እንቀበል እንግዶቻችንን።
3. ቅኖች እውነትን መጥተው ’ንዲማሩ፣
ለሰው ሁሉ ተከፍቷል በሩ።
ልባዊ ፍቅር እናሳያቸው፤
በ’የሱስ በኩል ነው አምላክ የሳባቸው።