የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 3/13 ገጽ 2
  • ሞቅ ያለ አቀባበል አድርጉላቸው!

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሞቅ ያለ አቀባበል አድርጉላቸው!
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ትልቅ ምሥክርነት ይሰጣል
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
  • እንግዶቻችንን መቀበል
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ (2016)
  • በመታሰቢያው በዓል ላይ የሚገኙትን ሰዎች እንዴት መርዳት እንችላለን?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
  • በመታሰቢያው በዓል ላይ ጥሩ አቀባበል አድርጉላቸው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
km 3/13 ገጽ 2

ሞቅ ያለ አቀባበል አድርጉላቸው!

1. ምሥክርነት ለመስጠት ከሁሉ የተሻለ አጋጣሚ የሚሰጠን የትኛው ወቅት ነው? እንዲህ የምንለውስ ለምንድን ነው?

1 በየዓመቱ የሚከበረው የመታሰቢያ በዓል ለሰዎች ምሥክርነት ለመስጠት ከሁሉ የተሻለ አጋጣሚ ይሰጠናል። ለምሳሌ በዚህ ዓመት በመታሰቢያው በዓል ላይ ከአሥር ሚሊዮን የሚበልጡ ተጋባዦች እንደሚገኙና ይሖዋና ኢየሱስ በቤዛው አማካኝነት ያሳዩንን ታላቅ ፍቅር በተመለከተ የሚሰጠውን ንግግር እንደሚያዳምጡ ይጠበቃል። (ዮሐ. 3:16፤ 15:13) ይሖዋ ባዘጋጀው በዚህ ስጦታ አማካኝነት ስለሚያገኙት በረከት የሚሰጠውን ትምህርት ያዳምጣሉ። (ኢሳ. 65:21-23) ሆኖም በዚህ ወቅት ምሥክርነት የሚሰጠው ተናጋሪው ብቻ አይደለም። በበዓሉ ላይ የሚገኙ ሁሉ ለእንግዶች ሞቅ ያለ አቀባበል በማድረግ ጥሩ ምሥክርነት መስጠት ይችላሉ።—ሮም 15:7

2. ለእንግዶች ሞቅ ያለ አቀባበል ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?

2 ፕሮግራሙ እስኪጀመር ቦታችሁን ይዛችሁ ከመጠበቅ ይልቅ ተጋብዘው ከመጡ ሰዎች ጋር ለመተዋወቅ ቅድሚያውን መውሰድ ትችላላችሁ። እንግዶች በበዓሉ ላይ ምን እንደሚከናወን በእርግጠኝነት ስለማያውቁ ፍርሃት ሊሰማቸው ይችላል። ፈገግ በማለት ሞቅ ያለ አቀባበል ካደረግንላቸው ዘና ሊሉ ይችላሉ። አንድ ሰው የመጣው የመጋበዣ ወረቀት ደርሶት መሆን አለመሆኑን ለማወቅ ስብሰባችን ላይ ሲገኝ የመጀመሪያ ጊዜው እንደሆነ አሊያም ከጉባኤው አባላት መካከል የሚያውቀው ሰው እንዳለ ልንጠይቀው እንችላለን። ምናልባትም አጠገባችን እንዲቀመጥ በማድረግ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ወይም መዝሙሮችን እንዲከታተል ልናሳየው እንችላለን። በዓሉ የሚከበረው በመንግሥት አዳራሽ ውስጥ ከሆነ ጥቂት ጊዜ ወስዳችሁ አዳራሹን ልታስጎበኙት ትችላላችሁ። በሌላ በኩል ደግሞ ከንግግሩ በኋላ ያልገባው ነገር ካለ ጥያቄውን ልትመልሱለት ትችላላችሁ። ከእናንተ በኋላ በዚያው አዳራሽ የመታሰቢያውን በዓል የሚያከብር ሌላ ጉባኤ ካለና አዳራሹን በፍጥነት መልቀቅ የሚጠበቅባችሁ ከሆነ ግን እንዲህ ልትሉት ትችላላችሁ፦ “በዓሉን እንዴት እንዳገኘኸው ብትነግረኝ ደስ ይለኛል። እንዴት መገናኘት እንችላለን?” ከዚያም በሌላ ጊዜ ለመገናኘት ቀጠሮ ያዙ። በተለይ ሽማግሌዎች የቀዘቀዙ አስፋፊዎችን ለማበረታታት ልዩ ጥረት ማድረግ ይኖርባቸዋል።

3. በመታሰቢያው በዓል ላይ ለሚገኙ እንግዶች ቅድሚያውን ወስደን አቀባበል ማድረጋችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

3 በርካታ እንግዶች የይሖዋ ሕዝቦች በመንፈሳዊው ገነት ውስጥ ያገኙትን ደስታ፣ ሰላም እና አንድነት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚመለከቱት በመታሰቢያው በዓል ላይ ሲገኙ ነው። (መዝ. 29:11፤ ኢሳ. 11:6-9፤ 65:13, 14) እንግዶች በመታሰቢያው በዓል ላይ ከተገኙ በኋላ የሚኖራቸው ስሜት በአብዛኛው የተመካው እኛ ቅድሚያውን ወስደን በምናሳያቸው አቀባበል ላይ ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ