የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lmd ትምህርት 3
  • ደግነት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ደግነት
  • ሰዎችን ውደዱ—ደቀ መዛሙርት አድርጉ
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢየሱስ ምን አድርጓል?
  • ከኢየሱስ ምን እንማራለን?
  • ኢየሱስን ምሰል
  • ስለ ሰዎች ማሰብ
    ሰዎችን ውደዱ—ደቀ መዛሙርት አድርጉ
  • “የደግነት ሕግ” ይምራችሁ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022
  • ጥላቻ በነገሠበት ዓለም ደግነት ለማሳየት መጣር
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
  • ደግነት በማሳየት ይሖዋን አስደስት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
ለተጨማሪ መረጃ
ሰዎችን ውደዱ—ደቀ መዛሙርት አድርጉ
lmd ትምህርት 3

ውይይት መጀመር

ኢየሱስ አንድን ዓይነ ስውር ለመፈወስ በደግነት ሲቀርበው።

ዮሐ. 9:1-7

ምዕራፍ 3

ደግነት

መሠረታዊ ሥርዓት፦ “ፍቅር . . . ደግ ነው።”—1 ቆሮ. 13:4

ኢየሱስ ምን አድርጓል?

ኢየሱስ አንድን ዓይነ ስውር ለመፈወስ በደግነት ሲቀርበው።

ቪዲዮ፦ ኢየሱስ ዓይነ ስውር ሰው ፈወሰ

1. ቪዲዮውን ተመልከት፤ ወይም ዮሐንስ 9:1-7ን አንብብ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች አስብባቸው፦

  1. ሀ. ኢየሱስ ለዓይነ ስውሩ ሰው በቅድሚያ ያደረገው ምንድን ነው? መፈወስ ወይስ ምሥራቹን መንገር?—ዮሐንስ 9:35-38⁠ን ተመልከት።

  2. ለ. ኢየሱስ ያደረገው ነገር ሰውየው ለምሥራቹ ጆሮ እንዲሰጥ ያደረገው ይመስልሃል? ለምን?

ከኢየሱስ ምን እንማራለን?

2. የምናነጋግረው ሰው እንደምናስብለት ከተሰማው ምሥራቹን ለመስማት ይበልጥ ፈቃደኛ ሊሆን ይችላል።

ኢየሱስን ምሰል

3. ራስህን በግለሰቡ ቦታ አስቀምጥ። ምን እንደሚሰማው ለመገመት ሞክር።

  1. ሀ. ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘ግለሰቡን የሚያሳስበው ነገር ምን ይሆን? የሚጠቅመው ወይም ትኩረቱን የሚስበው ነገር ምን ሊሆን ይችላል?’ ይህን ማድረግህ እንዲያው ለደንቡ ያህል ሳይሆን ከልብ የመነጨ ደግነት እንድታሳይ ያነሳሳሃል።

  2. ለ. ጆሮ ሰጥተህ በማዳመጥ ግለሰቡ የሚያሳስበው ነገር ግድ እንደሚሰጥህ አሳይ። ስለ አንድ ጉዳይ ያለውን አመለካከት ነግሮህ ወይም ያጋጠመውን ችግር አንስቶልህ ከሆነ የውይይቱን ርዕስ አታስቀይር።

4. በደግነትና በአክብሮት ተናገር። ለግለሰቡ ከራራህለትና ከልብህ ልትረዳው ከፈለግህ፣ በምትናገርበት መንገድ ላይ መንጸባረቁ አይቀርም። የምትጠቀምባቸውን ቃላትና የድምፅህን ቃና በጥንቃቄ አስብበት፤ ቅር የሚያሰኝ ነገር እንዳትናገር ተጠንቀቅ።

5. መልካም አድርግለት። ተገቢ እንደሆነ በሚሰማህ ጊዜ ሁሉ ግለሰቡን በተግባር ለመርዳት የሚያስችሉህን አጋጣሚዎች ተጠቀምባቸው። ደግነት ማሳየት ጥሩ ውይይት ለማድረግ መንገድ ሊከፍት ይችላል።

ተጨማሪ ጥቅሶች

ሮም 12:15, 16፤ ገላ. 6:10፤ ዕብ. 13:16

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ