የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w91 4/1 ገጽ 14-15
  • ኢየሱስ በድጋሚ የታየባቸው ሌሎች ጊዜያት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኢየሱስ በድጋሚ የታየባቸው ሌሎች ጊዜያት
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢየሱስ የተገለጠባቸው ሌሎች ጊዜያት
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
  • ከሞት የተነሳው ኢየሱስ ለብዙዎች ተገለጠ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • በተዘጋ ክፍል ውስጥ
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • ኢየሱስ ከሞት ተነሳ!
    መጽሐፍ ቅዱስ—የያዘው መልእክት ምንድን ነው?
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
w91 4/1 ገጽ 14-15

ኢየሱስ ሕይወቱና አገልግሎቱ

ኢየሱስ በድጋሚ የታየባቸው ሌሎች ጊዜያት

ደቀ መዛሙርቱ ገና እንዳዘኑ ናቸው። የመቃብሩን ባዶ መሆን ትርጉም አልተረዱም። ሴቶቹ የነገሯቸውንም ዜና አላመኑም። ስለዚህ እሁድ ረፋዱ ላይ ቀለዮጳና አንድ ሌላ ደቀመዝሙር ኤማሁስ ወደሚባል ከኢየሩሳሌም አሥራ አንድ ኪሎ ሜትር ወደሚርቅ መንደር ሄዱ።

በጉዞአቸውም ላይ በዕለቱ ስለ ተፈጸመው ነገር ሲወያዩ አንድ እንግዳ ሰው ከእነርሱ ጋር ተቀላቀለ። እርሱም “እርስ በርሳችሁ የምትነጋገሩአቸው እነዚህ ነገሮች ምንድን ናቸው?” ሲል ጠየቃቸው።

ደቀ መዛሙርቱም ወደ ታች እንዳቀረቀሩ ቆም አሉ፤ ቀለዮጳም “አንተ በኢየሩሳሌም ለብቻህ እንግዳ ሆነህ ትኖራለህን? በእነዚህ ቀኖች በዚያ የሆነውን ነገር አታውቅምን? አለው።”

እርሱም “ይህ ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀ።

“ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ” ብለው መለሱለት። “እርሱንም የካህናት አለቆችና መኳንንቶቻችን ለሞት ፍርድ እንዴት አሳልፈው እንደ ሰጡትና እንደ ሰቀሉት ነው። እኛ ግን እስራኤልን እንዲቤዥ ያለው እርሱ እንደሆነ ተስፋ አድርገን ነበር።”

ቀለዮጳና ጓደኛው በዕለቱ የተፈጸመውን አስደናቂ ነገር ገለጹ። ይህም ከሰው በላይ የሆኑ ኃያላን መላእክት መታየታቸውና መቃብሩ ባዶ መሆኑ ነበር። ከዚያ ቀጥለው ስለ እነዚህ ነገሮች ትርጉም ግራ እንደተጋቡ ገለጹ። በዚህ ጊዜም እንግዳው ሰው፦ “እናንተ የማታስተውሉ፣ ነቢያትም የተናገሩትን ሁሉ ልባችሁ ከማመን የዘገየ፤ ክርስቶስ ይህን መከራ ይቀበል ዘንድና ወደ ክብሩ ይገባ ዘንድ ይገባው የለምን?” በማለት በቁጣ ተናገራቸው። ከዚያም በቅዱሳት መጻሕፍት ስለ ክርስቶስ የተጻፈውን ተረጎመላቸው።

በመጨረሻም ወደ ኤማሁስ ሲቀርቡ እንግዳው ሰው ጉዞውን የሚቀጥል መሰለ። ደቀመዛሙርቱ የበለጠ መስማት ስለ ፈለጉ “ከእኛ ጋር እደር፣ ማታ ቀርቦአልና ቀኑም ሊመሽ ጀምሮአል” በማለት አጥብቀው ጠየቁት። ስለዚህ ቆየና ከእነርሱ ጋር በማዕድ ቀረበ። ጸሎት አቅርቦ እንጀራውንም ቆርሶ ሲሰጣቸው እርሱ ሥጋዊ አካል በመልበስ የተገለጠው ኢየሱስ እንደሆነ አወቁ። በዚያን ጊዜ ግን ተሰወረባቸው።

በዚህን ጊዜም ይህ እንግዳ ሰው ይህን ያህል እውቀት እንዴት ሊያገኝ እንደቻለ ተረዱ። ስለዚህም “በመንገድ ሲናገረን መጻሕፍትንም ሲከፍትልን ልባችን ይቃጠልብን አልነበረምን? ተባባሉ።” ወዲያውኑም ተነስተው በችኮላ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። ሐዋርያትንና አብረዋቸው የተሰበሰቡ ሰዎችንም አገኙ። ቀለዮጳና ጓደኛው አንድም ቃል ከመናገራቸው በፊት ሌሎቹ በጋለ ስሜት “ጌታ በእውነት ተነሥቶአል ለስምዖንም ታይቶአል” ብለው ተናገሩ። ከዚያም ሁለቱ ኢየሱስ ለእነርሱም እንዴት እንደተገለጠላቸው ተረኩ። በዚያ ቀን ለተለያዩ ደቀመዛሙርቱ ሲታይ ይህ አራተኛው ጊዜ ነበር።

ደቀመዛሙርቱ አይሁድን በመፍራት በሮቹን ቢቆልፉም እንኳን ኢየሱስ በድንገት ለአምስተኛ ጊዜ ተገለጠ። በመካከላቸውም ቆሞ “ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው።” ምትሐት የሚያዩ ስለመሰላቸው ተደናገጡ። ምትሐት አለመሆኑን በማብራራት ኢየሱስ “ስለ ምን ትደነግጣላችሁ? ስለ ምንስ አሳብ በልባችሁ ይነሣል? እኔ ራሴ እንደሆንሁ እጆቼንና እግሮቼን እዩ፤ በእኔ እንደምታዩት፣ መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውምና” አላቸው። አሁንም ቢሆን የእርሱን ሕያው መሆን በጣም አስደሳች ከመሆኑ የተነሳ የዚህን እውነተኛነት ለማመን ገና ያመነቱ ነበር።

እርሱ ኢየሱስ መሆኑን በእርግጥ እንዲያስተውሉ እነርሱን ለመርዳት “በዚህ አንዳች የሚበላ አላችሁን?” ብሎ ጠየቃቸው። የተጠበሰ ዓሣ ተቀብሎ ከበላ በኋላ እንዲህ በማለት ያስተምራቸው ጀመር፦ “ከእናንተ ጋር ሳለሁ [ከመሞቴ በፊት] በሙሴ ሕግና በነቢያት በመዝሙራትም ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይገባል ብዬ የነገርኋችሁ ቃሌ ይህ ነው።”

ከእነርሱ ጋር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንደ ማድረግ በሚቆጠረው ቆይታው ኢየሱስ እንዲህ ሲል አስተማራቸው፦ “ክርስቶስ መከራ ይቀበላል በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ይነሣል፣ በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል ተብሎ እንዲሁ ተጽፎአል። እናንተም ለዚህ ምስክሮች ናችሁ።”

በአንድ በሆነ ምክንያት ቶማስ በዚህ በጣም አስፈላጊ በነበረ የእሁድ ምሽት ስብሰባ ላይ አልነበረም። ስለዚህ በሚቀጥለው ቀን ሌሎቹ በደስታ “ጌታን አይተነዋል” አሉት።

ቶማስም “የችንካሩን ምልክት በእጆቹ ካላየሁ ጣቴንም በችንካሩ ምልክት ካላገባሁ እጄንም በጎኑ ካላገባሁ አላምንም አላቸው።”

ከስምንት ቀን በኋላም ደቀመዛሙርቱ እንደገና በቤት ውስጥ ተሰብስበው ነበር። በዚህን ጊዜ ቶማስ አብሯቸው አለ። በሮቹ የተቆለፉ ቢሆኑም ኢየሱስ አሁንም እንደገና በመካከላቸው ቆሞ፦ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው። ከዚያም ወደ ቶማስ ፊቱን አዞረና “ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤ እጅህንም አምጣና በጎኔ አግባው፤ ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን” በማለት ጋበዘው።”

ቶማስም “ጌታዬ አምላኬም” በማለት በደስታ ተናገረ።

ኢየሱስም “ስለ አየኸኝ አምነሃልን?” በማለት ጠየቀውና “ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው አለው።” ሉቃስ 24:11, 13-48፤ ዮሐንስ 20:19-29

◆ ሁለቱ ደቀመዛሙርት ወደ ኤማሁስ በሚወስደው መንገድ ላይ ሲጓዙ አንድ እንግዳ ሰው ምን ጥያቄ አቀረበላቸው?

◆ እንግዳው ሰው ደቀመዛሙርቱ በውስጣቸው ልባቸው እንዲቃጠል ያደረገ ምን ነገር ተናገረ?

◆ ደቀመዛሙርት እንግዳው ሰው ኢየሱስ መሆኑን የተረዱት እንዴት ነው?

◆ ቀለዮጳና ጓደኛው ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሱ ምን የሚያስደንቅ ዜና ሰሙ?

◆ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ለአምስተኛ ጊዜ የተገለጠው እንዴት ነው? በዚህን ጊዜስ ምን ተደረገ?

◆ ኢየሱስ ለአምስተኛ ጊዜ ከተገለጠ ከስምንት ቀን በኋላ ምን ነገር ሆነ? ቶማስ በመጨረሻ ኢየሱስ ሕያው መሆኑን ያመነው እንዴት ነው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ