የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w91 10/1 ገጽ 19
  • ‘በመንፈስ የተራቡ ደስተኞች ናቸው’

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ‘በመንፈስ የተራቡ ደስተኞች ናቸው’
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በትምህርት ቤት ውስጥ መንፈሳዊ ረሐብተኞችን ማጥገብ
    መጠበቂያ ግንብ—1993
  • አንዳንዶች ለጥያቄዎቻቸው መልስ ያገኙት እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
  • “ጥበብን የሚያገኝ ሰው ምስጉን [ደስተኛ አዓት] ነው”
    መጠበቂያ ግንብ—1993
  • የኢየሱስ በጎች ድምፁን ይሰማሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
w91 10/1 ገጽ 19

የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ሪፖርት

‘በመንፈስ የተራቡ ደስተኞች ናቸው’

ኢየሱስ “ስለ መንፈሳዊ ፍላጎታቸው የሚያስቡ ደስተኞች ናቸው” ብሎ ነበር። (ማቴዎስ 5:3 (አዓት) እንደነዚህ ያሉት ሰዎች ከአምላክ ቃል ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚገኘውን ሕይወት ሰጪ መልዕክት ይፈልጋሉ። ይህንንም እውቀት ማግኘታቸው የዘላለም ሕይወት ያስገኝላቸዋል።​—ማቴዎስ 4:4፤ ዮሐንስ 17:3

◻ በአንድ አፍሪካ አገር ውስጥ አንድ በመንፈሳዊ የተራበ ሰው የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን የያዘው መጽሐፌ የተሰኘውን መጽሐፍ ለማግኘት በቅዝቃዜና በጨለማ ውስጥ የአራት ሰዓት መንገድ ተጓዘ። ይሁን እንጂ የይሖዋ ምስክሮች በሚሰብኩበት መንደር ስደርስ የመጨረሻዋ መጽሐፍ ተበርክታ በማግኘቱ በጣም አዘነ። ሌሎች መጽሐፎች እስከሚመጡ ድረስ ለሦስት ቀናት በመንደሩ ውስጥ ቆየ። በመጨረሻም ይህንን ጥሩ መንፈሳዊ መጽሐፍ በማግኘቱ ተደሰተ።

የይሖዋ ምስክሮቹ በዚህ ራቅ ብሎ በሚገኝ አካባቢ በቆዩበት ወር 55 መጻሕፍትን፣ 365 ብሮሹሮችንና 145 መጽሔቶችን ሲያከፋፍሉ 5 ኮንትራቶችንም አግኝተዋል። አካባቢውን ለቀው በሚሄዱበት ጊዜም ትልልቆቹ ሰዎችም ሆኑ ትንንሾቹ ልጆች እየተከተሉ በክፔሌ ቋንቋ “ይሖዋ ከእናንተ ጋር ይሁን” ሲሏቸው በጣም ስሜታቸው ተነክቶ ነበር። ፍላጎት ያሳዩትን ተከታትሎ ለመጠየቅ ጥረት ተደርጓል።

በዚሁ አገር ውስጥ የምትገኝ አንዲት ሌላ ሴት በመንፈሳዊ የተራበች መሆንዋን አሳይታለች። ሴትየዋ ትከተለው የነበረው ቤተክርስቲያን ገንዘብ ያዥ ነበረች፤ እንዲሁም የምትኖርበት አውራጃ የመዝናኛ ባለ ሥልጣን ነበረች። ምስክሮቹ ሲያነጋግሯት ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ ለክርስትና ያወጣቸውን ብቃቶች እንደማታሟላ በሐዘኔታ ገለጸች። ምስክሮቹም በራስዋ መጽሐፍ ቅዱስ እውነተኛውን ሃይማኖት እንዴት ለይታ ለማወቅ እንደምትችል አሳዩአት። ከዚህ በኋላ በመንግሥት አዳራሹ በሚደረጉት ሁለት ስብሰባዎች ላይ ተገኘችና፦ “ያየሁትና የሰማሁት ነገር እውነቱ ይህ መሆኑን እንዳምን አድርጎኛል” አለች። በስብሰባዎቹና በስብሰባዎቹ የተገኙት ሰዎች ባሳዩት ጠባይ በጣም ተደነቀች። በመጀመሪያ ያነጋገሯት ምስክሮች የነገሯት ነገር ቅዠት ሳይሆን እውን የሆነ ነገር መሆኑን ተመለከተች። ከዚያን ጊዜ ጀምራ ከቤተክርስቲያንዋ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማቋረጥ እርምጃ ወሰደች፤ ይህም በአካባቢው ላለው ኅብረተሰብ ጥሩ ምስክርነት ለመስጠት አስችሏል።

◻ በኒው ካሌዶኒያ ውስጥ የሚኖር አንድ ወጣት ማሌኔዢያዊ የሃይማኖት አስተማሪ መንፈሳዊ ረሃብ ነበረበት። በእናቱ ቤት ውስጥ በጠረጴዛ ላይ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውነት የተባለ አንድ መጽሐፍ አግኝቶ ምዕራፍ 2 እና 3ን አነበበ። በዚያም ላይ ማብራሪያ የተሰጠባቸው እንደ ዘፀዓት 20:4, 5 እንዲሁም ዮሐንስ 4:23, 24 ያሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ልቡን ነኩት። በእነዚህ ጥቅሶች በተገለጸው መሠረት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በምስሎት መጠቀምን የምትፈቅደው ለምንድን ነው በማለት ቄሱን ጠየቀ። ቄሱም ጥያቄውን አድበስብሶት አለፈ። ሰውየው ወደ ሌሎች የተለያዩ “የክርስቲያን” ሃይማኖቶች ሄደ፤ ነገር ግን ለጥያቄዎቹ አጥጋቢ የሆኑ መልሶች አልሰጡትም። በመጨረሻም ቀደም ብላ ለእውነት ፍላጎት እንዳላት ካሳየችው ከእናቱ ጋር በይሖዋ ምስክሮች ስብሰባ ላይ ለመገኘት ወሰነ። በምስክሮቹ መካከል የተመለከተው ፍቅርና በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተው ትምህርታቸው በጣም አስደነቀው።

የስብሰባው ቦታ በጣም ሩቅ ቢሆንም በመንገድ የሚያልፉትን መኪናዎች እንዲያሳፍሩት እየለመነ ዘወትር ሳያቋርጥ ወደ ስብሰባዎች ይሄድ ነበር፤ ብዙም ሳይቆይ ለእውነት አቋም በመውሰድ ተጠመቀ። በአሁኑ ጊዜ ዲያቆን ሆኖ ያገለግላል። እናቱና ሁለት ሥጋዊ እህቶቹም የይሖዋ ምስክሮች ሆነዋል። ወጣቱ ሰው ከራሱ ጎሣ ለሆኑ ሰዎች በመስበክ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ጀምሯል። በአሁኑ ጊዜ በዚህ አካባቢ በዛ ያለ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በስብሰባዎች ላይ ይገኛሉ፤ ይህ ሁሉ ሊሆን የቻለው ወጣቱ ሰው በጠረጴዛ ላይ አንድ መጽሐፍ ቅዱስን የምታብራራ ጽሑፍ በመመልከቱ፣ መጽሐፍዋንም በማጥናቱና ያወቀውንም ነገር አቅልሎ ስላልተመለከተ ነው።

ይሖዋ በዛሬው ጊዜ በመከናወን ላይ ያለ ታላቅ የመንፈሳዊ ምግብ ፕሮግራም አለው። ብዛት ያላቸውም ሰዎች ከዚህ እየተጠቀሙ ነው። ኢሳይያስ “እነሆ፣ ባሪያዎቼ ይበላሉ እናንተ [የሐሰት ሃይማኖት አባሎች] ግን ትራባላችሁ” በማለት ስለዚህ ነገር በትክክል ተንብዮአል። (ኢሳይያስ 65:13) መንፈሳዊ ረሃባችንን ለማርካት ይሖዋ ካዘጋጀው ዝግጅት የምንጠቀም ከሆን ደስተኞች እንሆናለን።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ