መጽሐፍ ቅዱስ በእርግጥ ከአምላክ የመጣ ስጦታ ነውን?
“አምላክ ለሰው ልጆች ከሰጣቸው ስጦታዎች ሁሉ የላቀው ስጦታ መጽሐፍ ቅዱስ ነው ብዬ አምናለሁ።” ይህንን የተናገሩት የዩናይትድ ስቴትስ 16ኛ ፕሬዚዳንት አብርሃም ሊንከን ናቸው።a ለዚህ ረዥም ዕድሜ ላለው መጽሐፍ አድናቆታቸውን የገለፁት እርሳቸው ብቻ አይደሉም።
በ19ኛው መቶ ዘመን የእንግሊዝ መሪ የነበሩት ዊልያም ኢ ግላድስተን ሲያትቱ “መጽሐፍ ቅዱስ ልዩ ከሆነ ምንጭ የተገኘ መሆኑን የሚያረጋግጥ ባሕርይ አለው። ተፎካካሪዎች ከሆኑት መጻሕፍት በሙሉ በጣም ከፍተኛ የሆነ ብልጫ አለው” ብለዋል። በ18ኛው መቶ ዘመን የአሜሪካ መሪ የነበሩት ፓትሪክ ሄንሪም በተመሳሳይ እንዲህ ብለዋል፦ “መጽሐፍ ቅዱስ እስከ ዛሬ ከታተሙት መጽሐፍት ሁሉ ይበልጣል።” በቅዱሳን ጽሑፎች እጅግ የተደነቀው የፈረንሳዩ ንጉሠ ነገሥት ናፖሊዮን ቦናፓርት “መጽሐፍ ቅዱስ ተራ መጽሐፍ ሳይሆን የሚቃወሙትን ሁሉ ድል የመንሳት ኃይል ያለው ሕያው ፍጥረት ነው” ብሏል።
መጽሐፍ ቅዱስ ለአንዳንዶች የእርዳታና የመጽናኛ ምንጭ ሆኖላቸዋል። የአሜሪካን ኰንፌዴራዊ ጦር መሪ የነበሩት ጄኔራል ሮበርት ኢ.ሊ “ግራ በምጋባበትና በምጨነቅበት ጊዜ ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስ ብርሃንና ብርታት ሳይሰጠኝ ቀርቶ አያውቅም” ብለዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት የነበሩት ጆን ክዊንሲ አዳምስ ለመጽሐፉ ያላቸውን አድናቆት ሲገልጹ “ለረጅም ዓመታት ያህል በዓመት አንድ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ በጠቅላላ ከዳር እስከ ዳር አንብቤ መጨረስን ልማዴ አድርጌአለሁ” በማለት ተናግረዋል።
መጽሐፍ ቅዱስን ለሰው ልጆች የሰጠው ኃያሉ አምላክ ከሆነ በእርሱ መለኮታዊ ትዕዛዝ መጽሐፉን የሚያረጋግጡ መረጃዎች መኖር ይገባቸዋል። ከሌሎች መጻሕፍት ሁሉ የላቀ መጽሐፍ መሆን ይኖርበታል። መጽሐፍ ቅዱስ ብርታትና መመሪያ የሚገኝበት መጽሐፍ እንዲሆን ከተፈለገ አስተማማኝና ትምክህት ሊጣልበት የሚችል መጽሐፍ መሆን ይኖርበታል። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ በእርግጥ ከአምላክ የተሰጠ ስጦታ ነውን? ብለን እንጠይቃለን። እስቲ ከዚህ ቀጥለን የዚህን ጥያቄ መልስ እንፈልግ።
[የግርጌ ማስታወሻ]
[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ዊልያም ኢ.ግላድስተን
[ምንጭ]
U.S. National Archives photo
አብርሃም ሊንከን
[ምንጭ]
U.S. National Archives photo
ፓትሪክ ሄንሪ
[ምንጭ]
Harper’s U.S. History
ናፖሊዮን ቦናፓርት
[ምንጭ]
Drawn by E. Ronjat
ጆን ክዊንሲ አዳምስ
[ምንጭ]
Harper’s U.S. History
ሮበርት ኢ.ሊ
[ምንጭ]
U.S. National Archives photo