ክርስቲያናዊ ሕይወት
ይሖዋ ሕዝቡን ይጠብቃል
የመጀመሪያው ፋሲካ ወሳኝ ክንውን ነበር። በዚያ ምሽት ፈርዖን የበኩር ልጁ መሞቱን ካወቀ በኋላ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ተነሱ፣ እናንተም ሆናችሁ ሌሎቹ እስራኤላውያን ከሕዝቤ መካከል ውጡ። ሂዱ፣ እንዳላችሁት ይሖዋን አገልግሉ።” (ዘፀ 12:31) በእርግጥም ይሖዋ ሕዝቡን እንደሚታደግ አሳይቷል።
የይሖዋን ሕዝብ ዘመናዊ ታሪክ መለስ ብለን ስንመረምር ይሖዋ አሁንም ቢሆን ሕዝቡን እንደሚመራና እንደሚጠብቅ የሚያሳይ ግልጽ ማስረጃ እናገኛለን። በዋናው መሥሪያ ቤት “ለይሖዋ ስም የሚሆን ሕዝብ” በሚል ጭብጥ የተዘጋጀው ቤተ መዘክር ይህን ጎላ አድርጎ ያሳያል።
የዎርዊክ ቤተ መዘክር ጉብኝት፦ “ለይሖዋ ስም የሚሆን ሕዝብ” የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች፣ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እምነት እንዲያዳብሩ ለመርዳት ከ1914 አንስቶ የትኛውን አዲስ ዘዴ ተጠቅመዋል? ውጤቱስ ምን ነበር?
በ1916 እና በ1918 ምን ዓይነት ፈታኝ ሁኔታዎች አጋጥመው ነበር? በወቅቱ ይሖዋ ድርጅቱን እየመራ እንደነበር የሚያሳይ ምን ማስረጃ አለ?
የይሖዋ ሕዝቦች ተቃውሞ ቢያጋጥማቸውም በእምነት ጸንተው የቆሙት እንዴት ነው?
የይሖዋ ሕዝቦች በ1935 ምን አዲስ ግንዛቤ አገኙ? ይህስ ምን ውጤት አስገኘ?
የዎርዊክ ቤተ መዘክር ጉብኝት፦ “ለይሖዋ ስም የሚሆን ሕዝብ” የሚለውን ቪዲዮ ስትመለከት ይሖዋ ሕዝቡን እንደሚመራና እንደሚጠብቅ ያለህን እምነት የሚያጠናክር ምን ነገር አይተሃል?