የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w92 11/1 ገጽ 3-4
  • ኃጢአትን እንዴት ትመለከተዋለህ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኃጢአትን እንዴት ትመለከተዋለህ?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በምዕራቡ ዓለም እየጠፋ የሄደው የኃጢአት አመለካከት
  • ኃጢአት የሌለበት ዓለም እንዴት ይገኛል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • ኃጢአት የማይኖርበት ጊዜ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • ሰዎች ስለ ኃጢአት ያላቸውን አመለካከት የለወጠው ምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • ኃጢአት ምንድን ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
w92 11/1 ገጽ 3-4

ኃጢአትን እንዴት ትመለከተዋለህ?

ከይሖዋ ምስክሮች አንዷ ከሆነች ሴት ጋር መጽሐፍ ቅዱስን ታጠና የነበረች አንዲት የቤት እመቤት “በጸሎቷ ውስጥ ኃጢአታችንን ይቅር እንዲልልን እየደጋገመች የምትጠይቀው ለምንድን ነው?” ስትል በምሬት ተናገረች። “ወንጀለኛ የሆንኩ ነው የሚያስመስለው።” ዛሬ ብዙዎች ልክ እንደዚህች ሴት ወንጀል እስካልፈጸሙ ድረስ ኃጢአታቸውን አይገነዘቡትም።

ከአይሁድና ከክርስትና የመነጩ ሃይማኖቶች የሚያስተምሩትን የሚወረስ ኃጢአት በሚመለከት በባህላቸው ምንም ግንዛቤ በሌላቸው በተለይ በምሥራቃዊ አገሮች ውስጥ ይህ ነገር እውነት ነው። (ዘፍጥረት 3:1-5, 16-19፤ ሮሜ 5:12) ለምሳሌ ያህል የሺንቶ ሃይማኖት ተከታዮች ኃጢአትን አንዱ ካህን በሚያወዛውዘው ጫፉ ላይ ወረቀት ወይም ተልባ በተጣበቀበት እንጨት በቀላሉ ሊጠረግ እንደሚችል ቆሻሻ አድርገው ይመለከቱታል። ይህ ዓይነቱ ሂደት ስለተፈጸመው ኃጢአት ንሥሐ መግባትን አይጠይቅም። ለምን? ኮዳንሻ ኢንሳይክሎፔድያ ኦፍ ጃፓን “መጥፎ ድርጊቶች ብቻ ሳይሆኑ ሊቆጣጠሯቸው የማይቻሉት የተፈጥሮ አደጋዎችም እንደ ጹሚ [ኃጢአት] ተደርገው ስለሚታዩ ነው” በማለት ያብራራል። እንደ ጹሚ የሚቆጠሩት ሰዎች ተጠያቂ የማይሆኑባቸው የተፈጥሮ አደጋዎች ሁሉ የማንጻት ሥነ ሥርዓት ሊያቆማቸው እንደሚችል ኃጢአቶች ተደርገው ይቆጠራሉ።

ይህም ማንኛውም ኃጢአት፣ ሆን ተብለው የተፈጸሙ መጥፎ ድርጊቶችም ቢሆኑ (በሕግ ከሚያስቀጡት የወንጀል ድርጊቶች በስተቀር) በማንጻት ሥርዓት ሊወገዱ ይችላሉ ወደሚለው አስተሳሰብ መርቷል። ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ “ፖለቲካዊ የማንጻት ሥነ ሥርዓት በጃፓን” በሚል ርዕስ ሥር ይህን አመለካከት ጠቅሶ ሲያብራራ በመጥፎ ድርጊት ውስጥ ሲሳተፉ የነበሩ በጃፓን ያሉ ፖለቲከኞች በድምፅ ሰጪዎች እንደገና ሲመረጡ ራሳቸውን “እንደነጹ” አድርገው ይቆጥሩታል። በዚህ መንገድ እውነተኛ የሆነ እርማት ስለማይደረግ ተመሳሳይ መጥፎ ድርጊቶች እንደገና ይከሰታሉ።

በሳምሳራ ወይም እንደገና በመወለድና በካርማ መሠረተ ትምህርት የሚያምኑ ቡዲሂስቶች የተለየ አስተያየት አላቸው። ዘ ኒው ኢንሳይክሎፔድያ ብሪታኒካ ሲያብራራ “በካርማ መሠረተ ትምህርት መሠረት ጥሩ ጠባይ ደስ የሚል ውጤት ያመጣል፤ ተመሳሳይ የሆኑ ጥሩ ድርጊቶች የማድረግ ዝንባሌም ይፈጥራል። መጥፎ ጠባይ ደግሞ መጥፎ ውጤት ያመጣል፤ ተደጋጋሚ የሆኑ መጥፎ ድርጊቶችን የማድረግ ዝንባሌም ይፈጥራል” ብሏል። በሌላ አባባል ኃጢአተኛ ጠባይ መጥፎ ፍሬ ያፈራል። የካርማ ትምህርት እንደገና ከመወለድ ትምህርት ጋር በጥብቅ የተያያዘ ነው። አንዳንድ ካርማዎችም ድርጊቱ የተፈጸመበት ሕይወት ካለፈ ከብዙ ዓመታት በኋላ በሚመጣው ሕይወት ውስጥ ፍሬያቸውን ያፈራሉ ይባላል።

ይህ ትምህርት አማኞቹን እንዴት ይነካል? በካርማ ከልቧ ታምን የነበረች አንዲት ቡድሂስት “ምኑንም ነገር ሳላውቀው አብሬው በተወለድኩት ነገር የተነሣ መከራዬን ማየቴ ምንም ትርጉም እንደማይሰጥ አሰብኩ። ዕድሌ እንደሆነ አድርጌ መቀበል ነበረብኝ። የቡድሃ መዝሙሮችን መዘመርና ጥሩ ኑሮ ለመኖር መጣጣር ችግሮቼን አላስወግዳቸውም። ቁጡና ደስታ የሌለኝ ሁልጊዜ ነገሮችን የማማርር ሰው ሆንኩ።” መጥፎ ጠባይ ስለሚያመጣቸው ውጤቶች የሚገልጸው የቡድሂስት ትምህርት የዋጋቢስነት ስሜት እንዲሰማት አደረጋት።

ሌላው የምሥራቅ ሃይማኖት የሆነው ኮንፊዩሻኒዝም የሰውን ክፋት ለመቋቋም የሚቻልበትን የተለየ መንገድ ያስተምራል። ከሦስቱ የኮንፊዩሺያን ታላላቅ ፈላስፎች አንዱ በነበሩት በሺንድዙ አመለካከት የሰው ተፈጥሮ ክፉ ነው፤ ወደ ራስወዳድነትም ያደላል። ኃጢአተኛ ዝንባሌዎች ባሏቸው ሰዎች መካከል ማኅበራዊ ሥርዓትን ጠብቆ ለመኖር ከተፈለገ ሊ አስፈላጊ እንደሆነ አጥብቀው ገልጸዋል። ትርጉሙም ሥነ ሥርዓት፣ ይሉኝታና የነገሮች ደንብ ማለት ነው። መንግትዙ የተባሉት ሌላው የኮንፊዩሺያን ፈላስፋ የሰው ተፈጥሮ ጥሩ ነው በማለት ተቃራኒ በሆነ ሁኔታ ቢገልጹትም ማኅበራዊ ችግሮች መኖራቸውን አምነዋል። መፍትሔውም ራስን በራስ ማሻሻል እንደሆነ ይተማመናሉ። በሁለቱም መንገድ ኮንፊዩሺያን ፈላስፎች በዓለም ላይ ያለውን ኃጢአት ለመዋጋት የትምህርትና የሥልጠናን አስፈላጊነት አስተምረዋል። ትምህርቶቻቸው በሊ አስፈላጊነት ላይ ቢስማሙም ስለ ኃጢአትና ክፋት ያላቸው አመለካከት ግልጽ አይደለም።—ከመዝሙር 14:3፤ 51:5 ጋር አወዳድሩ።

በምዕራቡ ዓለም እየጠፋ የሄደው የኃጢአት አመለካከት

በምዕራቡ ዓለም ስለ ኃጢአት ያለው አመለካከት በባሕላዊ መንገድ በግልጽ የተቀመጠ ነበር። እንዲሁም አብዛኞቹ ሰዎች በኃጢአት መኖርና ሊታቀብ የሚገባው ነገር እንደሆነ ይስማሙ ነበር። ይሁን እንጂ በምዕራቡ ዓለም ስለ ኃጢአት የነበረው አመለካከት በመለወጥ ላይ ነው። ብዙዎች በሕሊናቸው ውስጥ የሚሰማቸውን “የጥፋተኝነት ስሜት” መወገድ እንደሚገባው ነገር አድርገው በመውሰድ ኃጢአት እንዳይፈጽሙ መጠንቀቃቸውን አቁመዋል። ከ40 ከሚበልጡ ዓመታት በፊት ፖፕ ፓየስ 12ኛ “የዚህ መቶ ዘመን ኃጢአት የኃጢአተኝነት ስሜት እጦት ነው” በማለት እሮሮአቸውን አሰምተዋል። ለ ፔለረ በተባለው በየሳምንቱ የሚወጣ የካቶሊክ ጽሑፍ ላይ በታተመ አንድ ጥናት መሠረት ከፈረንሳይ ነዋሪዎች 90 በመቶ የሚሆነው ነዋሪ የሮማ ካቶሊክ ተከታይ እንደሆነ ቢናገርም የኃጢአትን መኖር አለማመናቸው የሚያስደንቅ ነው።

በእርግጥ በአሁኑ ጊዜ በምሥራቁም ሆነ በምዕራቡ ያለው አብዛኛው ሕዝብ በኃጢአት መኖር ሳይጨነቅ በደንብ ረክቶና ተዝናንቶ እየኖረ ያለ ይመስላል። ይሁን እንጂ ይህ ማለት ኃጢአት የለም ማለት ነውን? ችግር በማይፈጥርብን ሁኔታ ነገሩን ችላ ለማለት እንችላለንን? ኃጢአት አንድ ቀን ይጠፋ ይሆን?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ