ዓመታዊ ስብሰባ
ጥቅምት 1, 1994
የፔንሲልቫንያ የመጠበቂያ ግንብ የመጽሐፍ ቅዱስና የትራክት ማኅበር አባላት ዓመታዊ ስብሰባ ጥቅምት 1, 1994 በኒው ጀርሲ ክፍለ ሀገር በጀርሲ ከተማ 2932 ኬኔዲ ቦሊቫርድ በሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል። በመጀመሪያ አባላቱ ብቻ የሚገኙበት ስብሰባ ጠዋት በ3:30 ይደረግና በ4 ሰዓት አጠቃላዩ ዓመታዊው ስብሰባ ይከተላል።
ካለፈው ዓመት ወዲህ የፖስታ አድራሻቸውን የለወጡ የማኅበሩ አባላት በሐምሌ ወር መደበኛ የማስታወቂያ ደብዳቤዎችና ውክልናዎች ይደርሷቸው ዘንድ ለውጡን አሁኑኑ ለጸሐፊው ቢሮ ማስታወቅ ይኖርባቸዋል።
ለአባላቱ ከዓመታዊው የስብሰባ ማስታወቂያዎች ጋር የሚላኩላቸው ውክልናዎች ግፋ ቢል እስከ ነሐሴ 1 ድረስ ለማኅበሩ ጽሕፈት ቤት እንዲደርሱ አድርገው መመለስ አለባቸው። እያንዳንዱ አባል በስብሰባው ላይ ራሱ ይገኝ ወይም አይገኝ እንደሆነ በመግለጽ ውክልናውን ወዲያውኑ ሞልቶ መመለስ አለበት። በእያንዳንዱ የውክልና ቅጽ ላይ የሚሰጠው መረጃ በዚህ ነጥብ ላይ ግልጽ መሆን ይኖርበታል። ምክንያቱም ማን በስብሰባው ላይ እንደሚገኝ የሚታወቀው በዚህ መሠረት ነው።
መደበኛውን የሥራ ጉዳይና ሪፖርት ጨምሮ ጠቅላላው ስብሰባ በ7 ሰዓት ወይም ከዚያ ብዙ ሳይቆይ ያበቃል ተብሎ ይጠበቃል። ከሰዓት በኋላ ስብሰባ አይኖርም። ያለው ቦታ የተወሰነ በመሆኑ መግባት የሚቻለው በትኬት ብቻ ይሆናል። ዓመታዊውን ስብሰባ በስልክ ወደ ሌሎች አዳራሾች ለማስተላለፍ የተደረገ ዝግጅት የለም።