ዓመታዊ ስብሰባ
ጥቅምት 7, 1995
የፔንሲልቫንያ የመጠበቂያ ግንብ የመጽሐፍ ቅዱስና ትራክት ማኀበር አባላት ዓመታዊ ስብሰባ ጥቅምት 7, 1995 በኒው ጀርሲ ክፍለ ሀገር በጀርሲ ከተማ 2932 ኬኔዲ ቦሊቫርድ በሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል። በመጀመሪያ አባላቱ ብቻ የሚገኙበት ስብሰባ ጠዋት በ3:30 ይደረግና በ4 ሰዓት አጠቃላዩ ዓመታዊ ስብሰባ ይከተላል።
ካለፈው ዓመት ወዲህ የፖስታ አድራሻቸውን የለወጡ የማኀበሩ አባላት በሐምሌ ወር መደበኛ የማስታወቂያ ደብዳቤዎችና ውክልናዎች ይደርሷቸው ዘንድ ለውጡን አሁኑኑ ለጸሐፊው ቢሮ ማስታወቅ ይኖርባቸዋል።
ለአባላቱ ከዓመታዊው የስብሰባ ማስታወቂያዎች ጋር የሚላኩላቸው ውክልናዎች ግፋ ቢል እስከ ነሐሴ 1 ድረስ ለማኅበሩ ጽሕፈት ቤት እንዲደርሱ አድርገው መመለስ አለባቸው። እያንዳንዱ አባል በስብሰባው ላይ ራሱ ይገኝ ወይም አይገኝ እንደሆነ በመግለጽ ውክልናውን ወዲያውኑ ሞልቶ መመለስ አለበት። በእያንዳንዱ የውክልና ቅጽ ላይ የሚሰጠው መረጃ በዚህ ነጥብ ላይ ግልጽ መሆን ይኖርበታል። ምክንያቱም ማን በስብሰባው ላይ እንደሚገኘ የሚታወቀው በዚህ መሠረት ነው።
መደበኛውን የሥራ ጉዳይና ሪፖርት ጨምሮ ጠቅላለው ስብሰባ በ7 ሰዓት ወይም ከዚያ ብዙ ሳይቆይ ያበቃል ተብሎ ይጠበቃል። ከሰዓት በኋላ ስብሰባ አይኖርም። ያለው ቦታ የተወሰነ በመሆኑ መግባት የሚቻለው በቲኬት ብቻ ይሆናል። ዓመታዊውን ስብሰባ በስልክ ወደ ሌሎች አዳራሾች ለማስተላለፍ የተደረገ ዝግጅት የለም።