የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w96 4/1 ገጽ 9
  • መልካም ሥራዎች ይሖዋን ያስከብራሉ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መልካም ሥራዎች ይሖዋን ያስከብራሉ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ‘አምላክ ለሰው ፊት አያደላም’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • “ጥበብን የሚያገኝ ሰው ምስጉን [ደስተኛ አዓት] ነው”
    መጠበቂያ ግንብ—1993
  • የኢየሱስ በጎች ድምፁን ይሰማሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
w96 4/1 ገጽ 9

የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ሪፖርት

መልካም ሥራዎች ይሖዋን ያስከብራሉ

ኢየሱስ በተራራው ስብከቱ ላይ ለደቀ መዛሙርቱ “መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ . . . በሰው ፊት ይብራ” ብሏቸው ነበር። (ማቴዎስ 5:16) በተመሳሳይም በዛሬው ጊዜ እውነተኛ ክርስቲያኖች ይሖዋን በሚያስከብሩ ‘መልካም ሥራዎች’ ይሳተፋሉ።

እነዚህ መልካም ሥራዎች የትኞቹ ናቸው? ምንም እንኳ እነዚህ ሥራዎች የምሥራቹን ስብከት የሚጨምሩ ቢሆኑም ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ጠባያችንም በጣም አስፈላጊ ነው። ብዙውን ጊዜ ሰዎችን በመጀመሪያ ወደ ክርስቲያን ጉባኤ የሚስባቸው መልካም ጠባያችን ነው። የሚከተሉት ተሞክሮዎች በማርቲኒክ የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች ‘ብርሃናቸውን በሰው ፊት በማብራት’ ላይ የሚገኙት እንዴት እንደሆነ ያሳያሉ።

◻ አንዲት የይሖዋ ምሥክር ከቤት ወደ ቤት በምታገለግልበት ወቅት የካቶሊክ እምነት ተከታይ የሆነች ሴት አነጋገረች። ይህች ሴት ከአንድ ሰውዬ ጋር ሳታገባው ለ25 ዓመታት አብራ ኖራለች። ከሰባት ዓመት በፊት በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ የተባለውን መጽሐፍ አግኝታ ስለ ነበር የይሖዋ ምሥክሮች ከሚያስተምሯቸው ትምህርቶች ጋር ተዋውቃለች።a ሴትየዋ ለይሖዋ ምሥክሯ “በጣም ብዙ ሃይማኖቶች አሉ። ከእነዚህ ሁሉ ግራ የሚያጋቡ ሃይማኖቶች መካከል የትኛውን እንደማምን አላውቅም” በማለት ነገረቻት። ምሥክሯ እውነት የሚገኘው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብቻ እንደሆነና እውነትን ለማግኘት ከፈለገች ቅዱሳን ጽሑፎችን በጥንቃቄ ማጥናትና መንፈሱንና መመሪያውን እንዲሰጣት ወደ አምላክ መጸለይ እንደሚኖርባት ገለጸችላት።

ሴትየዋ መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት ፍላጎት ቢኖራትም ለተወሰነ ጊዜ ያህል በይሖዋ ምሥክሮች የመንግሥት አዳራሽ በሚደረጉ ክርስቲያናዊ ስብሰባዎች ላይ እንድትገኝ የቀረቡላትን በርካታ ግብዣዎች ሳትቀበል ቀረች። ይህን ያደረገችው ለምን ነበር? በጣም ዓይነ አፋር ስለ ነበረች ነው። ቢሆንም በክርስቶስ ሞት መታሰቢያ በዓል ላይ እንድትገኝ የቀረበላትን ግብዣ ከተቀበለች በኋላ ዓይነ አፋርነቷን ተቋቁማ በስብሰባው ላይ ተገኘች።

እርሷን በጣም የማረካት በመንግሥት አዳራሹ ውስጥ የተመለከተችው የፍቅር መንፈስ ነበር። በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ እንዲህ ያለ እውነተኛ ወዳጅነት አይታ አታውቅም! ከዚህ ስብሰባ በኋላ በአካባቢው የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች በሚያደርጓቸው በሁሉም ስብሰባዎች ላይ መገኘት ጀመረች፤ ብዙም ሳይቆይ አብሯት ይኖር የነበረውን ሰው አገባች። በአሁኑ ጊዜ የተጠመቀች የጉባኤው አባል ሆናለች።

◻ የሌላዋ የይሖዋ ምሥክር መልካም ሥራዎችም ጥሩ ውጤቶች አስገኝተዋል። እርሷ በአንድ ቢሮ ውስጥ በኃላፊነት ቦታ ትሠራ ነበር። አንድ ከሪዩኒየን ደሴት የመጣ ሰው በመሥሪያ ቤቱ ውስጥ ከተቀጠረ በኋላ አንዳንድ ሠራተኞች ቁመቱ አጭር በመሆኑ ምክንያት ያሾፉበት ጀመር። ሰውዬው መቀለጃ ሆነ። ከዚህ በተቃራኒ ምሥክሯ ሁልጊዜ ለሰውዬው አሳቢነትና አክብሮት ታሳየው ነበር። ወዲያው እርሷ ከሌሎች ሰዎች የተለየችበት ምክንያት ምን እንደሆነ ጠየቃት።

ምሥክሯ ለሰዎች አክብሮት የምታሳየው ከይሖዋ ምሥክሮች በተማረቻቸው የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ምክንያት እንደሆነ ገለጸችለት። በተጨማሪም ቅዱሳን ጽሑፎች ስለ አምላክ ዓላማዎችና ስለ አዲስ ዓለም ተስፋ የሚናገሩትን አሳየችው። ሰውዬው መጽሐፍ ቅዱስ ለማጥናት ተስማማና በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ መገኘት ጀመረ። ከዚያም አብራው ትኖር የነበረችውን ሴት አገባ።

ከጊዜ በኋላ ወደ ሪዩኒየን ተመለሰ። ቀደም ሲል ዘመዶቹ በተለይም የሚስቱ ዘመዶች ያስቸግሩት ነበር። አሁን ግን በመልካም ክርስቲያናዊ ጠባዩ በጣም ተገረሙ። ይህ ሰው ተጠምቆ በአሁኑ ጊዜ ዲያቆን ሆኗል። በተጨማሪም ሚስቱንና ሁለት ልጆቹን ጨምሮ ከቤተሰቡ ውስጥ በርካታ ሰዎች የአምላክ መንግሥት የምሥራች አስፋፊዎች ሆነው በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ በማገልገል ላይ ናቸው።

[የግርጌ ማስታወሻ]

a  ኒው ዮርክ በሚገኘው የመጠበቂያ ግንብ መጽሐፍ ቅዱስና ትራክት ማኅበር የታተመ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ