የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w99 2/15 ገጽ 24-25
  • ለአንድ “ቅዱስ” ሥፍራ መፋለም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለአንድ “ቅዱስ” ሥፍራ መፋለም
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሃይማኖት ለሰላም የቆመ ኃይል ነው?
    ንቁ!—2011
  • ቅዱስ መሆን ሲባል ምን ማለት ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የመንፈስ ቅዱስን ምንነት ለይቶ ማወቅ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ካለፈው ታሪኩ አንጻር ሲታይ ክፍል 15:- ከ1095-1453 እዘአ​—ሰይፍ መምዘዝ
    ንቁ!—1996
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
w99 2/15 ገጽ 24-25

ለአንድ “ቅዱስ” ሥፍራ መፋለም

ሐምሌ 15, 1099 ላይ በሮማው ሊቀ ጳጳስ ትእዛዝ የተካሄደው የመጀመሪያው የመስቀል ጦርነት ኢየሩሳሌምን ለመቆጣጠር የነበረው ግብ ሰመረለት። ጭፍጨፋው በጣም አሰቃቂ ነበር! ከከተማዋ ነዋሪዎች መካከል ከእልቂቱ በሕይወት የተረፉ ሰዎች ቢኖሩ አገረ ገዥውና ዐጃቢው ብቻ ሲሆኑ እነሱም ሊተርፉ የቻሉት ጠቀም ያለ ጉቦ ከተከፈለ በኋላ ነበር። ቄሱ አንቶኒ ብሪጅ ዘ ክሩሴድስ በተባለው መጽሐፋቸው ላይ በተቀሩት ሙስሊምና አይሁዳዊ ነዋሪዎች ላይ የደረሰውን ነገር እንዲህ ሲሉ ዘግበዋል:- “የመስቀል ጦርነቱ ተዋጊዎች ከተማዋ ውስጥ ያሻቸውን እንዲያደርጉ ነፃ ከተለቀቁ በኋላ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ደም የማፍሰስ ጥማታቸውን ተያያዙት። . . . ወንድ፣ ሴት፣ ሕፃን ሳይሉ በከተማዋ ውስጥ ያገኙትን ሁሉ ጨፈጨፉ . . . ሁሉንም ገድለው ከጨረሱ በኋላ ድል አድራጊዎቹ ለአምላክ ምስጋና ለማቅረብ በከተማዋ ጎዳና ላይ በሰልፍ . . . ወደ ቅዱስ ሴፑልክሬ ቤተ ክርስቲያን አመሩ።”

የመስቀል ጦርነት ተዋጊዎች ድል ከተቀዳጁበት ማለትም ሕዝበ ክርስትና በኢየሩሳሌም መኖር ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በሮማ ካቶሊክ፣ በምሥራቅ ኦርቶዶክስና በሌሎች ክርስቲያን ነን በሚሉ ሃይማኖቶች መካከል ግጭት ጠፍቶ አያውቅም። በ1850 በኢየሩሳሌም ውስጥም ሆነ በአካባቢዋ በሚገኙ ቅዱስ ሥፍራዎች ባለቤትነት ላይ በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች መካከል የተካሄደው የይገባኛል ውዝግብ ለክሬሚያን ጦርነት ዋና መንስኤ ነበር። እንግሊዝ፣ ፈረንሳይና የኦቶማን መንግሥት ከሩሲያ ጋር ባደረጉት ፍልሚያ ግማሽ ሚልዮን ሕይወት ጠፍቷል።

ጦርነቱ ኢየሩሳሌምንና ቅዱስ ቦታዎችዋን በተመለከተ በሕዝበ ክርስትና መካከል ላለው አለመግባባት መፍትሔ አላመጣም። ቅራኔ መፍትሔ እንዲያገኝ አላደረገም። በወቅቱ አገሪቱን ይቆጣጠሩ የነበሩት ኦቶማኖች ቅዱስ ቦታዎቹን ለተለያዩ ሃይማኖቶች በማከፋፈል ሰላም ለማስፈን ሞክረው ነበር። ዶክተር ሚናሺ ሃሬል ዚስ ኢዝ ጀሩሳሌም በተባለው መጽሐፋቸው ላይ “ይህ መሠረተ ሐሳብ የተባበሩት መንግሥታት ኅዳር 1947 የመሬት ክፍፍልን አስመልክቶ ባስተላለፈው ውሳኔ . . . ተቀባይነት አግኝቷል። ይህም በመሆኑ ሐሳቡ የዓለም አቀፋዊ ሕግ ክፍል ነው” ሲሉ ገልጸዋል። ከዚህ የተነሳ የቅዱስ ሴፑልክሬ ቤተ ክርስቲያን ለሮማ ካቶሊኮች፣ ለግሪክ ኦርቶዶክስ፣ ለአርመናውያን፣ ለአሶራውያንና ለኮፕቲኮች ተከፋፍሎ ተሰጥቷል። በመጨረሻም የኢትዮጵያ መነኮሳት አንዳንድ አባላቶቻቸው ሰገነቱ ላይ በጎጆዎች ውስጥ እንዲኖሩ በማድረግ በዚህ ቤተ ክርስቲያን ላይ የባለቤትነት ድርሻ አግኝተዋል። ብዙዎች የቅዱስ ሴፑልክሬን ቤተ ክርስቲያን ሕዝበ ክርስትና ያላት እጅግ የተቀደሰ ቦታ አድርገው ይመለከቱታል። ቤተ ክርስቲያኑ በንዋየ ቅዱሳት፣ በምስሎችና በቅርጻ ቅርጾች የተሞላ ነው። ሌላው ቅዱስ ቦታ እንደሆነ የሚነገርለት የጎርዶን ካልቨሪ ሲሆን አንዳንድ ፕሮቴስታንቶች ኢየሱስ የተገደለበትና የተቀበረበት ቦታ አድርገው በመቁጠር ከፍተኛ አክብሮት ይሰጡታል።

ከረጅም ጊዜ በፊት ኢየሱስ በቅዱስ ሥፍራዎች ታምን ለነበረች ሴት እንዲህ ብሏል:- “በዚህ ተራራ ወይም በኢየሩሳሌም ለአብ የማትሰግዱበት ጊዜ ይመጣል። . . . በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል።” (ዮሐንስ 4:​21-24) ስለዚህ እውነተኛ ክርስቲያኖች ለቅዱስ ቦታዎች አምልኮታዊ ክብር አይሰጡም። ከዳተኛዋ ኢየሩሳሌም በ70 እዘአ በሮም ሠራዊት አማካኝነት የደረሰባት ጥፋት ለሕዝበ ክርስትና ትልቅ ማስጠንቀቂያ ነው። ጣዖት አምላኪነቷ፣ መከፋፈሏና ያለባት የደም ዕዳ ክርስቲያን ነኝ ባይነቷ ውሸት መሆኑን ያጋልጣል። ስለዚህ አምላክ ታላቂቱ ባቢሎንን ያዋቀሩትን ሃይማኖቶች በሙሉ አስመልክቶ የተናገረው ጥፋት በሕዝበ ክርስትና ላይም ይደርሳል።​—⁠ራእይ 18:​2-8

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ