የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w99 9/1 ገጽ 3
  • የምንታመምበት ምሥጢሩ ምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የምንታመምበት ምሥጢሩ ምንድን ነው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጉዳዩን ምሥጢር ማድረግ
  • እንድንታመም የሚያደርገን ዲያብሎስ ነውን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • ከክፉ መናፍስት ጥቃት ራስህን ጠብቅ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • የእምነት ፈውስ የአምላክ ድጋፍ አለውን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • እምነት አንድን የታመመ ሰው ሊረዳ የሚችለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
w99 9/1 ገጽ 3

የምንታመምበት ምሥጢሩ ምንድን ነው?

ትንሿ ኦማጂ የተቅማጥ በሽታ ይዟታል። እናቷ ሐዋ በልጅዋ ሰውነት ውስጥ ያለው ፈሳሽ ያልቃል ብላ ተጨንቃለች። በሌላ መንደር ያለችው የአክስቷ ልጅ በቅርቡ ልጅዋን በዚህ ምክንያት በሞት እንዳጣች ሰምታ ነበር። ለሐዋ አማት የሆኑት የኦማጂ አያት ልጅቷን ወደ አንድ የጎሳ ጠንቋይ ለመውሰድ ፈልገዋል። “ልጅቷ እንድትታመም ያደረገው ክፉ መንፈስ ነው። ሊጠብቃት የሚችለውን ክታብ ልታደርጊላት ፈቃደኛ ባለመሆንሽ ይኸው አሁን ችግሩ ጀመረ!” አሏት።

ይህ ሁኔታ በአብዛኛው የዓለማችን ክፍል የተለመደ ነው። በመቶ ሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ስውር የሆኑት የሕመም መንስኤዎች ክፉ መናፍስት ናቸው ብለው ያምናሉ። ይህ ነገር እውነት ነውን?

ጉዳዩን ምሥጢር ማድረግ

ምናልባት አንተ የማይታዩ መናፍስት በሽታ ያመጣሉ የሚል እምነት አይኖርህ ይሆናል። እንዲያውም አብዛኛዎቹ በሽታዎች የሚመጡት በቫይረሶችና ባክቴሪያዎች ምክንያት መሆኑን ሳይንቲስቶች አረጋግጠው እያለ እንዴት አንድ ሰው እንደዚህ ያስባል ብለህ ትገረም ይሆናል። ይሁን እንጂ የሰው ዘር ስለ እነዚህ ጥቃቅን በሽታ አማጭ ሕዋሳት ያወቀው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደሆነ አስታውስ። አንቶኒ ቫን ሌወንሁክ በ17ኛው መቶ ዘመን አጉልቶ የሚያሳይ መነጽር አሻሽሎ እስከሠራበት ጊዜ ድረስ ረቂቅ ሕዋሳት በሰው ዓይን አይታዩም ነበር። ከዚያም በኋላ ቢሆን ሳይንስ በበሽታና በሽታን በሚያመጡ ሕዋሳት መካከል ያለውን ግንኙነት ለመረዳት የቻለው በሉዊ ፓስተር የ19ኛው መቶ ዘመን ግኝት አማካኝነት ነው።

በሰው ዘር ታሪክ ውስጥ ለብዙ ዘመናት የበሽታ መንስኤ ምን እንደሆነ ሳይታወቅ ስለኖረ ሁሉም በሽታዎች የሚመጡት በክፉ መናፍስት ምክንያት ነው የሚለውን ንድፈ ሐሳብ ጨምሮ ብዙ አጉል እምነቶች እየዳበሩ መጥተዋል። ዘ ኒው ኢንሳይክለፒዲያ ብሪታኒካ ይህ አስተሳሰብ እያደገ ሊመጣ የቻለበትን አንድ መንገድ ይጠቁማል። የቀድሞዎቹ ፈዋሾች የታመሙ ሰዎችን በተለያዩ ሥራ ሥሮች፣ ቅጠላ ቅጠሎችና በቅርብ ባገኙት ነገር ሁሉ ለማከም ይሞክሩ ነበር ይላል። አንዳንድ ጊዜ ከእነዚህ መካከል አንዱ ይሠራል። በዚህ ጊዜ ፈዋሹ ያዳናቸው ነገር በትክክል እንዳይታወቅ ሲል በሕክምናው ላይ ብዙ ከአጉል እምነቶች ጋር የተያያዙ ሥነ ሥርዓቶችንና ድርጊቶችን ይጨምራል። በዚህ መንገድ ሰዎች እርሱ ከሚሰጠው አገልግሎት መጠቀማቸውን እንዲቀጥሉ ያደርጋል። ከዚህ የተነሳ መድኃኒት ምሥጢራዊ እየሆነ የሄደ ሲሆን ሰዎችም እርዳታ ለማግኘት ከሰው በላይ ወደ ሆነ ኃይል ዞር ለማለት ተገድደዋል።

እነዚህ ባሕላዊ የሆኑ የሕክምና ዘዴዎች አሁንም ቢሆን በበርካታ አገሮች ውስጥ እየተሠራባቸው ነው። ብዙ ሰዎች በሽታን የሚያመጡት የቀድሞ አባቶች መናፍስት ናቸው ይላሉ። ሌሎች ደግሞ በሽታ ለኃጢአታችን የሚከፈለን ቅጣት ስለሆነ እንድንታመም የሚያደርገን አምላክ ነው ይላሉ። የተማሩ ሰዎችም እንኳ የበሽታን ባዮሎጂያዊ ባሕርይ ቢያውቁም ከሰው በላይ የሆኑ ኃይላትን ተጽዕኖ ይፈሩ ይሆናል።

ጠንቋዮችና ባሕላዊ መድኃኒተኞች ይህን ፍርሃት ሰዎችን ለመበዝበዝ ይጠቀሙበታል። ታዲያ እኛ ምን ብለን ማመን ይኖርብናል? ጤንነታችን እንዲጠበቅ ሲባል በመናፍስት ተስፋ ማድረጉ ያዋጣል? መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ