የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w05 11/15 ገጽ 3
  • ዲያብሎስ በእርግጥ አለ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ዲያብሎስ በእርግጥ አለ?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2016
  • ዓለምን እየገዛ ያለው ማን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • የዘላለም ሕይወት ጠላት
    በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
w05 11/15 ገጽ 3

ዲያብሎስ በእርግጥ አለ?

ስለ ዲያብሎስ ምን አመለካከት አለህ? ዲያብሎስ የሰው ልጆች መጥፎ ነገሮችን እንዲያደርጉ የሚፈትን እውን አካል ነው ወይስ አንድ ዓይነት የክፋት ባሕርይ? ዲያብሎስ ሊፈራ የሚገባው ፍጡር ነው ወይስ ከአጉል እምነት ወይም ከአፈ ታሪክ የመነጨ ሐሳብ እንደሆነ በማሰብ ችላ ሊባል የሚገባው አካል? “ዲያብሎስ” የሚለው ቃል በአጽናፈ ዓለም ውስጥ የሚገኝን ሕልውና የሌለው አጥፊ የሆነ ኃይል የሚያመለክት ነው? በርካታ ዘመናዊ የሃይማኖት ምሑራን እንደሚሉት ቃሉ በሰዎች ውስጥ የሚያድር የክፋት ባሕርይን የሚያመለክት ነው?

የዲያብሎስን ማንነት በተመለከተ ሰዎች የተለያየ አመለካከት መያዛቸው የሚያስደንቅ አይደለም። ራሱን በመደበቅ ረገድ ጥሩ ችሎታ ያለውን ሰው እውነተኛ ማንነት ማወቅ ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሚሆን መገመት አያዳግትም! በተለይ ደግሞ ግለሰቡ እውነተኛ ማንነቱን ደብቆ ለመኖር ከቆረጠ ሁኔታው ይበልጥ አስቸጋሪ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ ዲያብሎስን የሚገልጸው በዚህ መንገድ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ዲያብሎስ ሰይጣን ተብሎም የሚጠራ ሲሆን ስለ እርሱም “ሰይጣን ራሱ የብርሃን መልአክ ለመምሰል ራሱን ይለዋውጣል” በማለት ይናገራል። (2 ቆሮንቶስ 11:14) ዲያብሎስ ክፉ ቢሆንም ጥሩ እንደሆነ አድርጎ ራሱን በማቅረብ ሌሎችን ያታልላል። ሰዎች ዲያብሎስ የለም ብለው እንዲያምኑ ማድረግ ከቻለ ደግሞ ዓላማውን ለማሳካት ይበልጥ ተስማሚ ይሆንለታል።

ታዲያ ዲያብሎስ ማን ነው? ወደ ሕልውና የመጣውስ መቼ እና እንዴት ነው? በዛሬው ጊዜ በሰዎች ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድረው እንዴት ነው? ይህንን ተጽዕኖ ለመቋቋም ልናደርገው የምንችለው ነገር ይኖር ይሆን? መጽሐፍ ቅዱስ ከመጀመሪያው አንስቶ የዲያብሎስን እውነተኛ ታሪክ የሚናገር ከመሆኑም ሌላ ከላይ ላሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ ይሰጣል።

[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ራሱን ደብቆ ለመኖር የቆረጠን ሰው እውነተኛ ማንነት ማወቅ ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሚሆን መገመት አያዳግትም!

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ