የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w09 11/1 ገጽ 18
  • ኤደን ገነት የጠፋችው እንዴት ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኤደን ገነት የጠፋችው እንዴት ነው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የግድያ ሴራ የጠነሰሱት ሰዎች ራሳቸው ተገደሉ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ኢየሱስ ፈተናን ተቋቁሟል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • የሰዶምና የገሞራ ጥፋት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • የአልዓዛር ትንሣኤ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
w09 11/1 ገጽ 18

ለወጣት አንባቢያን

ኤደን ገነት የጠፋችው እንዴት ነው?

መመሪያ፦ ይህን መልመጃ ጸጥታ በሰፈነበት ቦታ ሆነህ ሥራ። ጥቅሶቹን ስታነብ በቦታው እንዳለህ አድርገህ አስብ። ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል እንዲሁም በታሪኩ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ሲነጋገሩ ድምፃቸውን ለመስማትና ስሜታቸውን ለመረዳት ሞክር። ታሪኩ ሕያው እንዲሆንልህ አድርግ።

ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።—ዘፍጥረት 3:1-24⁠ን አንብብ።

ሔዋን እባቡ ሲያናግራት መጀመሪያ ላይ ምን የተሰማት ይመስልሃል?

․․․․․

ከቁጥር 7-10 ላይ እንደተገለጸው አዳምና ሔዋን በወቅቱ ምን የተሰማቸው ይመስልሃል? (ኃጢአት የሠሩት ሆን ብለው እንደሆነ አስታውስ።)

․․․․․

ከቁጥር 22-24 ላይ በተገለጸው መሠረት አዳምና ሔዋን ከኤደን ገነት በተባረሩበት ጊዜ የነበረውን ሁኔታ እንዴት ትገልጸዋለህ?

․․․․․

ጥልቅ ምርምር አድርግ።

ሔዋን ዓይኗ ለውድቀት የዳረጋት እንዴት ነው? (ቁጥር 6⁠ን በድጋሚ አንብብ።)

․․․․․

ሔዋን ፍሬውን ለመብላት ‘የጓጓችው’ ለምንድን ነው? (ቁጥር 4 እና 5⁠ን በድጋሚ አንብብ።)

․․․․․

አዳም ከሔዋን ጋር በኃጢአቷ እንዲተባበር ያነሳሳው ምን ሊሆን ይችላል? (ቁጥር 6⁠ን በድጋሚ አንብብ።)

․․․․․

ኃጢአት፣ ከአዳምና ሔዋን በኋላ ባሉት ትውልዶች ውስጥ በወንዶችና በሴቶች መካከል ባለው ግንኙነት ላይ ምን መጥፎ ውጤት አስከትሏል? (ቁጥር 16⁠ን በድጋሚ አንብብ።)

․․․․․

አዳምና ሔዋን ኃጢአት በመሥራታቸው የተነሳ በመካከላቸው ያለው ግንኙነት እንደሻከረ የሚያሳየው ምንድን ነው? (ቁጥር 12⁠ን በድጋሚ አንብብ።)

․․․․․

ይሖዋ ዓላማውን ከግቡ ለማድረስ ሲል ለችግሩ ወዲያው መፍትሔ ያዘጋጀው እንዴት ነው? (ቁጥር 15⁠ን በድጋሚ አንብብ።)

․․․․․

ከዚህ ታሪክ ያገኘኸውን ትምህርት ተግባራዊ አድርግ። ከዚህ በታች ስለተዘረዘሩት ነገሮች ምን ትምህርት እንዳገኘህ ጻፍ፦

በራስ የመመራት መንፈስ ስላለው አደጋ።

․․․․․

ዓይን መጥፎ ምኞቶች እንዲያድሩብን የሚያደርግ ስለመሆኑ።

․․․․․

የሠራነውን ስህተት በሌሎች ማሳበብ ጥቅም የሌለው ስለመሆኑ።

․․․․․

ከዚህ ታሪክ ውስጥ ልብህን ይበልጥ የነካው ምንድን ነው? ለምንስ?

․․․․․

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ