የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w14 7/1 ገጽ 14-15
  • የማይታየውን አምላክ ማየት ትችላለህ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የማይታየውን አምላክ ማየት ትችላለህ?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ከፍጥረት በግልጽ ይታያል
  • “ስለ እሱ የገለጸልን”
  • የማይታየው አምላክ ነጸብራቅ የሆነ ሰው
  • መረጃዎቹን አንድ ላይ መገጣጠም
  • ፍጥረትን በማየት ስለ ይሖዋ ይበልጥ ተማሩ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2023
  • ምሥራቹን ለማየት የታወሩ ዓይኖችን መግለጥ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • ዓይነ ስውራን ስለ ይሖዋ እንዲማሩ እርዷቸው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2015
  • ‘ወልድ አብን ለመግለጥ ፈቃደኛ ነው’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
w14 7/1 ገጽ 14-15
የተፈጥሮ ውበት—ተራሮች፣ ሐይቅ፣ አረንጓዴ ደን

የማይታየውን አምላክ ማየት ትችላለህ?

“አምላክ መንፈስ ነው”፤ በመሆኑም በዓይናችን ልናየው አንችልም። (ዮሐንስ 4:24) ሆኖም አንዳንድ ሰዎች አምላክን እንዳዩት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ተገልጿል። (ዕብራውያን 11:27) ይህ ሊሆን የቻለው እንዴት ነው? በእርግጥ ‘የማይታየውን አምላክ’ ማየት ትችላለህ?—ቆላስይስ 1:15

የእኛን ሁኔታ ዓይነ ስውር ሆኖ ከተወለደ ሰው ጋር ማወዳደር ይቻላል። ይህ ሰው ማየት አለመቻሉ በዙሪያው ያለውን ዓለም እንዳያውቅ ያግደዋል? የሚያግደው ሙሉ በሙሉ አይደለም። ዓይነ ስውር የሆነ ሰው በዙሪያው ስላሉ ሰዎች፣ ነገሮችና እንቅስቃሴዎች እንዲገነዘብ የሚያስችለውን መረጃ በተለያዩ መንገዶች ያገኛል። “የምናየው በዓይናችን ሳይሆን በአእምሯችን ነው” በማለት ዓይነ ስውር የሆነ አንድ ሰው ተናግሯል።

በተመሳሳይም አምላክን በሰብዓዊ ዓይን ልታየው ባትችልም ‘የልብህን ዓይኖች’ ተጠቅመህ ልታየው ትችላለህ። (ኤፌሶን 1:18) ይህን ልታደርግ የምትችልባቸውን ሦስት መንገዶች እስቲ እንመልከት።

ከፍጥረት በግልጽ ይታያል

አንድ ዓይነ ስውር ሰው፣ ማየት የማይችላቸውን ነገሮች ለመረዳት በሌሎች የስሜት ሕዋሳቱ ይጠቀማል፤ በመሆኑም ብዙውን ጊዜ የመስማትና የመዳሰስ ችሎታው ከፍ ያለ ነው። አንተም በተመሳሳይ፣ የስሜት ሕዋሳትህን ተጠቅመህ በዙሪያህ ያለውን ዓለም በመቃኘት እነሱን የፈጠረውን የማይታይ አምላክ ማየት ትችላለህ። “የማይታዩት ባሕርያቱ . . . ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ አንስቶ በግልጽ ይታያሉ፤ ምክንያቱም ባሕርያቱን ከተሠሩት ነገሮች ማስተዋል ይቻላል።”—ሮም 1:20

ለምሳሌ ያህል፣ መኖሪያችን ስለሆነችው ምድር አስብ። ምድር ልዩ በሆነ መንገድ የተሠራች ሲሆን እንደ ነገሩ እንድንኖር ሳይሆን በሕይወት እንድንደሰት የሚያስችሉ ነገሮችን ይዛለች። ለስለስ ያለ ነፋስ ሲነፍስብን፣ ፀሐይ ስንሞቅ፣ ጣፋጭ ፍሬ ስናጣጥም ወይም የወፎችን አስደሳች ዝማሬ ስንሰማ እንደሰታለን። እነዚህ ስጦታዎች የፈጣሪያችንን አሳቢነት፣ ርኅራኄና ለጋስነት የሚያሳዩ አይደሉም?

በግዑዙ አጽናፈ ዓለም ውስጥ ከምታያቸው ነገሮች ስለ አምላክ ምን መማር ትችላለህ? ለምሳሌ ሰማያት የአምላክን ኃይል ይገልጣሉ። በቅርብ የተገኘ ሳይንሳዊ መረጃ እንደሚጠቁመው አጽናፈ ዓለም ከዚህ ቀደም ከሚታሰበው በሚበልጥ ከፍተኛ ፍጥነት እየሰፋ ነው! በማታ ሰማዩን ቀና ብለህ ስትመለከት አጽናፈ ዓለም እንዲህ በፍጥነት እንዲሰፋ የሚያደርገው ኃይል ከየት እንደመጣ አስብ። መጽሐፍ ቅዱስ ፈጣሪ ‘ታላቅ ኃይል’ እንዳለው ይነግረናል። (ኢሳይያስ 40:26) የአምላክ የፍጥረት ሥራዎች ‘ኃይሉ ታላቅ’ የሆነና “ሁሉን የሚችል” አምላክ እንደሆነ ያሳያሉ።—ኢዮብ 37:23

“ስለ እሱ የገለጸልን”

ማየት የተሳናቸው ሁለት ልጆች ያሏት አንዲት እናት እንዲህ ብላለች፦ “ማየት የተሳናቸው ሰዎች መማር ከሚችሉባቸው ዋና ዋናዎቹ መንገዶች አንዱ ንግግር ነው። የምታዩትንና የምትሰሙትን ሁሉ ንገሯቸው፤ [እንዲሁም] ስለሚያጋጥማችሁ ነገር ረጅም ማብራሪያ ለመስጠት ዝግጁ ሁኑ። የእነሱ ዓይኖች እናንተ ናችሁ።” በተመሳሳይም “በየትኛውም ጊዜ ቢሆን አምላክን ያየው አንድም ሰው የለም፤ ስለ እሱ የገለጸልን በአባቱ እቅፍ ያለው . . . ልጁ” ይኸውም ኢየሱስ ነው። (ዮሐንስ 1:18) ኢየሱስ የአምላክ የመጀመሪያ ፍጥረት እንዲሁም አንድያ ልጅ እንደ መሆኑ መጠን በሰማያት ያለውን ነገር የምናይበት “ዓይን” ሆኖልናል። ስለማይታየው አምላክ ከሁሉ የበለጠ መረጃ ልናገኝ የምንችለው ከእሱ ነው።

ከአባቱ ጋር ስፍር ቁጥር ለሌላቸው ዘመናት የኖረው ኢየሱስ ስለ አምላክ ከገለጻቸው ነገሮች መካከል አንዳንዶቹን እስቲ እንመልከት።

  • አምላክ በትጋት ይሠራል። “አባቴ እስካሁን እየሠራ ነው።”—ዮሐንስ 5:17

  • አምላክ የሚያስፈልገንን ሁሉ ያውቃል። “አባታችሁ . . . ገና ሳትለምኑት ምን እንደሚያስፈልጋችሁ ያውቃል።”—ማቴዎስ 6:8

  • አምላክ በለጋስነት ይሰጠናል። “አባታችሁ . . . በክፉና በጥሩ ሰዎች ላይ ፀሐዩን ያወጣል፤ ጻድቅ በሆኑና ጻድቅ ባልሆኑ ሰዎች ላይም ዝናብ ያዘንባል።”—ማቴዎስ 5:45

  • አምላክ እያንዳንዳችንን ከፍ አድርጎ ይመለከተናል። “ሁለት ድንቢጦች የሚሸጡት አነስተኛ ዋጋ ባላት ሳንቲም አይደለም? ሆኖም ከእነሱ አንዷም እንኳ አባታችሁ ሳያውቅ መሬት ላይ አትወድቅም። የእናንተ ግን የራሳችሁ ፀጉር እንኳ አንድ ሳይቀር ተቆጥሯል። ስለዚህ አትፍሩ፤ እናንተ ከብዙ ድንቢጦች የላቀ ዋጋ አላችሁ።”—ማቴዎስ 10:29-31

የማይታየው አምላክ ነጸብራቅ የሆነ ሰው

ዓይነ ስውራን ነገሮችን የሚረዱበት መንገድ ማየት ከሚችሉ ሰዎች ይለያል። አንድ ዓይነ ስውር፣ ጥላን የሚረዳው የፀሐይ ብርሃን የሌለበት ጨለምለም ያለ አካባቢ እንደሆነ አድርጎ ሳይሆን የፀሐይ ሙቀት ያልደረሰበት ቀዝቀዝ ያለ ቦታ እንደሆነ አድርጎ ሊሆን ይችላል። ሙሉ በሙሉ ዓይነ ስውር የሆነ ሰው ጥላንም ሆነ የፀሐይ ብርሃንን ማየት እንደማይችል ሁሉ እኛም ይሖዋን በራሳችን ልናውቀው አንችልም። በመሆኑም ይሖዋ የእሱን ባሕርያትና ስብዕና ፍጹም በሆነ መንገድ ማንጸባረቅ የቻለ አንድ ሰው ልኮልናል።

ይህ ሰው ደግሞ ኢየሱስ ነው። (ፊልጵስዩስ 2:7) ኢየሱስ ስለ አባቱ በመናገር ብቻ ሳይወሰን አምላክ ምን ዓይነት ባሕርይ እንዳለው በተግባር አሳይቶናል። የኢየሱስ ደቀ መዝሙር የሆነው ፊልጶስ “ጌታ ሆይ፣ አብን አሳየን” ብሎ ጠይቆት ነበር። ኢየሱስም “እኔን ያየ አብንም አይቷል” ብሎ መለሰለት። (ዮሐንስ 14:8, 9) ታዲያ ኢየሱስ ያደረጋቸው ነገሮች አብን ‘የሚያሳዩን’ እንዴት ነው?

ኢየሱስ አፍቃሪ፣ ትሑትና በቀላሉ የሚቀረብ ሰው ነበር። (ማቴዎስ 11:28-30) ሰዎች ከእሱ ጋር እንዲሆኑ የሚጋብዝ ስብዕና ነበረው። ኢየሱስ የሌሎች ሥቃይ ይሰማው እንዲሁም ደስታቸውን ይጋራ ነበር። (ሉቃስ 10:17, 21፤ ዮሐንስ 11:32-35) ስለ ኢየሱስ የሚገልጹ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን ስታነብ ወይም ስትሰማ ክስተቶቹ በአእምሮህ ሕያው እንዲሆኑልህ አድርግ። ኢየሱስ ሰዎችን ስለያዘበት መንገድ የምታሰላስል ከሆነ የአምላክ ድንቅ ማንነት ይበልጥ ግልጽ የሚሆንልህ ከመሆኑም በላይ ወደ እሱ ትቀርባለህ።

መረጃዎቹን አንድ ላይ መገጣጠም

አንድ ዓይነ ስውር ሰው በዙሪያው ያለውን ዓለም መመልከት የሚችልበትን መንገድ በተመለከተ አንዲት ደራሲ እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል፦ “ግለሰቡ መረጃ የሚቀበለው ከተለያዩ ምንጮች (በመዳሰስ፣ በማሽተት፣ በመስማትና በመሳሰሉት መንገዶች) ነው፤ ከዚያም በእነዚህ መንገዶች ያገኛቸውን መረጃዎች አንድ ላይ ማገጣጠም አለበት።” በተመሳሳይም የአምላክን የፍጥረት ሥራዎች ስትመለከት፣ ኢየሱስ ስለ አባቱ የተናገረውን ነገር ስታነብና የአምላክን ባሕርያት ያንጸባረቀበትን መንገድ ስትመረምር ይሖዋ ምን ያህል ግሩም አምላክ እንደሆነ በአእምሮህ መሳል ትችላለህ። እንዲሁም ይበልጥ እውን ይሆንልሃል።

በጥንት ዘመን የኖረው ኢዮብ ለዚህ እንደ ምሳሌ ሊጠቀስ ይችላል። ኢዮብ መጀመሪያ ላይ የተናገረው ‘ሳይገባው’ ነበር። (ኢዮብ 42:3) ኢዮብ የአምላክን አስደናቂ ፍጥረታት በደንብ ከተመለከተ በኋላ ግን “ጆሮዬ ስለ አንተ ሰምታ ነበር፤ አሁን ግን ዐይኔ አየችህ” ለማለት ተገፋፍቷል።—ኢዮብ 42:5

‘ይሖዋን ከፈለግኸው ታገኘዋለህ’

አንተም እንዲህ እንዲሰማህ ማድረግ ትችላለህ። ይሖዋን “ከፈለግኸው ታገኘዋለህ።” (1 ዜና መዋዕል 28:9) የይሖዋ ምሥክሮች የማይታየውን አምላክ ፈልገህ እንድታገኘው አንተን ለመርዳት ፈቃደኞች ናቸው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ