የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w14 9/15 ገጽ 28-32
  • በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ውስጥ ያሉትን አስቧቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ውስጥ ያሉትን አስቧቸው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የመጀመሪያው መቶ ዘመን ክርስቲያኖች
  • በዘመናችን ያሉ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች
  • አቅኚዎችን ማገዝ
  • ተጓዥ የበላይ ተመልካቾችን መደገፍ
  • የቤቴል ቤተሰብ አባላትን መደገፍ
  • በሌላ አገር የተመደቡ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮችን መደገፍ
  • አገልግሎትህን ማስፋት የምትችልባቸው መንገዶች
    የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ
  • የአቅኚነት አገልግሎት የሚያስገኛቸው በረከቶች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • ከፍተኛ ግምት የሚሰጣቸው የቅዱስ አገልግሎት መብቶች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
  • በአቅኚነት አገልግሎት ጽኑ
    መጠበቂያ ግንብ—1993
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
w14 9/15 ገጽ 28-32
ሁለት አቅኚ እህቶች የመስክ አገልግሎት ላይ
ሁለት አቅኚ እህቶች የመስክ አገልግሎት ላይ

በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ውስጥ ያሉትን አስቧቸው

‘የእምነት ሥራችሁንና ከፍቅር የመነጨ ድካማችሁን ዘወትር እናስባለን።’—1 ተሰ. 1:3

ምን ብለህ ትመልሳለህ?

  • በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩ አንዳንድ የሙሉ ጊዜ አገልግሎት መስኮች የትኞቹ ናቸው? በዚያ የተሰማሩትስ በቁሳዊ የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች የሚያገኙት እንዴት ነበር?

  • በዘመናችን ካሉ የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ዘርፎች የምትወደው የትኞቹን ነው?

  • የሙሉ ጊዜ አገልጋዮችን ለመርዳት ምን ማድረግ ትችላለህ?

1. ጳውሎስ ይሖዋን በትጋት ስለሚያገለግሉ ክርስቲያኖች ምን ተሰምቶታል?

ሐዋርያው ጳውሎስ፣ ምሥራቹን ለማስፋፋት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የሚደክሙትን ያስባቸው ነበር። እንዲህ ሲል ጽፏል፦ “የእምነት ሥራችሁን፣ ከፍቅር የመነጨ ድካማችሁንና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ባላችሁ ተስፋ የተነሳ የምታሳዩትን ጽናት በአምላካችንና በአባታችን ፊት ዘወትር እናስባለን።” (1 ተሰ. 1:3) ይሖዋም ሁኔታቸው ምንም ይሁን ምን አቅማቸው በፈቀደ መጠን የሚያገለግሉትን የታማኝ አምላኪዎቹን ከፍቅር የመነጨ ድካም ያስባል።—ዕብ. 6:10

2. በዚህ ርዕስ ላይ የትኞቹን ነጥቦች እንመረምራለን?

2 በጥንት ዘመንም ሆነ ዛሬ በርካታ የይሖዋ ሕዝቦች እሱን በሙሉ ጊዜ ለማገልገል ብዙ መሥዋዕትነት ከፍለዋል። እስቲ በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩ አንዳንድ ምሳሌዎችን እንመልከት። ከዚያም በዘመናችን ያሉ አንዳንድ የሙሉ ጊዜ አገልግሎት መስኮችን እንመረምራለን፤ እንዲሁም ለየት ባሉ መንገዶች ለማገልገል ራሳቸውን ያቀረቡትን እነዚህን ውድ ክርስቲያኖች እንዴት ማሰብ እንደምንችል እንመለከታለን።

የመጀመሪያው መቶ ዘመን ክርስቲያኖች

3, 4. (ሀ) በመጀመሪያው መቶ ዘመን አንዳንዶች በየትኞቹ የአገልግሎት መስኮች ይካፈሉ ነበር? (ለ) በቁሳዊ የሚያስፈልጋቸውን ነገር የሚያገኙት እንዴት ነበር?

3 ኢየሱስ ከተጠመቀ ብዙም ሳይቆይ፣ ዓለም አቀፋዊ ይዘት ያለው ሥራ አስጀመረ። (ሉቃስ 3:21-23፤ 4:14, 15, 43) እሱ ከሞተ በኋላ ደግሞ ሐዋርያቱ በዚህ የስብከት ሥራ ግንባር ቀደም ሆነው ተካፍለዋል። (ሥራ 5:42፤ 6:7) እንደ ፊልጶስ ያሉ አንዳንድ ክርስቲያኖች ወንጌላውያንና ሚስዮናውያን በመሆን በፓለስቲና ምድር አገልግለዋል። (ሥራ 8:5, 40፤ 21:8) ጳውሎስና ሌሎች ክርስቲያኖች፣ ራቅ ወዳሉ አካባቢዎች ተጉዘዋል። (ሥራ 13:2-4፤ 14:26፤ 2 ቆሮ. 1:19) አንዳንዶች ለምሳሌ ስልዋኖስ (ሲላስ)፣ ማርቆስና ሉቃስ ጸሐፊዎች ሆነውም አገልግለዋል። (1 ጴጥ. 5:12) ክርስቲያን እህቶችም ከእነዚህ ታማኝ ወንድሞች ጋር በዚህ ሥራ ተካፍለዋል። (ሥራ 18:26፤ ሮም 16:1, 2) የእነዚህ ክርስቲያኖች አስደሳች ተሞክሮ፣ የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍትን ለማንበብ እንድንጓጓ ያደረገን ከመሆኑም በላይ ይሖዋ አገልጋዮቹን በመልካም እንደሚያስባቸው ያረጋግጣል።

4 በጥንት ዘመን የነበሩት የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች በቁሳዊ የሚያስፈልጋቸውን ነገር የሚያገኙት እንዴት ነበር? አንዳንድ ጊዜ የእምነት ባልንጀሮቻቸው በእንግድነት ያስተናግዷቸው እንዲሁም ሌላ ዓይነት እርዳታ ያደርጉላቸው ነበር፤ እርግጥ ይህ እንዲደረግላቸው አይጠይቁም። (1 ቆሮ. 9:11-15) አንዳንድ ወንድሞችና ጉባኤዎች በፈቃደኝነት ይደግፏቸው ነበር። (የሐዋርያት ሥራ 16:14, 15⁠ን እና ፊልጵስዩስ 4:15-18⁠ን አንብብ።) በተጨማሪም ጳውሎስና የጉዞ ጓደኞቹ ወጪዎቻቸውን ለመሸፈን ለተወሰነ ጊዜ ሰብዓዊ ሥራ ይሠሩ ነበር።

በዘመናችን ያሉ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች

5. አንድ ባልና ሚስት በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ስለሚያሳልፉት ሕይወት ምን ተሰምቷቸዋል?

5 በዛሬው ጊዜም በርካታ ክርስቲያኖች በተለያዩ የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ዘርፎች ተግተው ይሠራሉ። (“የሙሉ ጊዜ አገልግሎት መስኮች” የሚለውን ሣጥን ተመልከት።) እነዚህ ክርስቲያኖች ስለመረጡት የአገልግሎት ዘርፍ ምን ይሰማቸዋል? ይህን ጥያቄ እነሱን ራሳቸውን እንድትጠይቃቸው እናበረታታሃለን፤ የሚሰጡህ መልስ እንደሚጠቅምህ የታወቀ ነው። አንድ ምሳሌ እንውሰድ፦ የዘወትር አቅኚ፣ ልዩ አቅኚ፣ ሚስዮናዊና በሌላ አገር ቤቴላዊ ሆኖ ያገለገለ አንድ ወንድም እንዲህ ብሏል፦ “ወደ ሙሉ ጊዜ አገልግሎት መግባቴ በሕይወቴ ውስጥ ካደረግኋቸው ምርጫዎች ሁሉ የተሻለው እንደሆነ ይሰማኛል። ዕድሜዬ 18 ዓመት ሲሆን ዩኒቨርሲቲ ከመግባት፣ ሙሉ ጊዜዬን በሰብዓዊ ሥራ ከማሳለፍ ወይም አቅኚ ከመሆን አንዱን መምረጥ ነበረብኝ። ይሖዋ እሱን በሙሉ ጊዜ ለማገልገል የምንከፍላቸውን መሥዋዕቶች እንደማይረሳ ከራሴ ተሞክሮ መናገር እችላለሁ። ይሖዋ የሰጠኝን ማንኛውንም ተሰጥኦና ችሎታ፣ ሰብዓዊ ሥራ ብሠራ ኖሮ ፈጽሞ ልጠቀምበት በማልችል መንገድ መጠቀም ችያለሁ።” ባለቤቱም እንዲህ ብላለች፦ “የተሰጠኝ እያንዳንዱ ምድብ እድገት እንዳደርግ ረድቶኛል። በተደጋጋሚ ጊዜያት ይሖዋ ጥበቃ እንደሚያደርግልንና እንደሚመራን መመልከት ችለናል፤ የለመድነውን የተመቻቸ ሕይወት ለመተው ፈቃደኛ ባንሆን ኖሮ ይህን ማየት አንችልም ነበር። በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ለምናሳልፈው ሕይወት ይሖዋን በየዕለቱ አመሰግነዋለሁ።” አንተስ እንዲህ ዓይነት ሕይወትህ መምራት አትፈልግም?

6. ይሖዋ ለአገልጋዮቹ ምን ዓይነት አመለካከት አለው?

6 እርግጥ ነው፣ አንዳንዶች ያሉበት ሁኔታ በአሁኑ ወቅት በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ለመካፈል አያስችላቸው ይሆናል። እነዚህ ክርስቲያኖችም በሙሉ ነፍሳቸው የሚያቀርቡትን አገልግሎት ይሖዋ ከፍ አድርጎ እንደሚመለከተው እርግጠኞች ነን። እስቲ በ⁠ፊልሞና 1-3 ላይ ጳውሎስ የጠቀሳቸውን የቆላስይስ ጉባኤ አባላትና በስም የዘረዘራቸውን ሌሎች ክርስቲያኖች አስብ። (ጥቅሱን አንብብ።) ጳውሎስ ለእነዚህ ክርስቲያኖች አድናቆቱን ገልጿል፤ ይሖዋም እንደሚያደንቃቸው የታወቀ ነው። በተመሳሳይም የሰማዩ አባታችን አንተ የምታከናውነውን አገልግሎት ያደንቃል። ይሁንና በአሁኑ ጊዜ በሙሉ ጊዜ አገልግሎት የሚካፈሉትን መደገፍ የምትችለው እንዴት ነው?

አቅኚዎችን ማገዝ

7, 8. አቅኚዎች ምን ይጠበቅባቸዋል? ሌሎች የጉባኤው አባላት አቅኚዎችን ሊደግፏቸው የሚችሉት እንዴት ነው?

7 በመጀመሪያው መቶ ዘመን እንደነበሩት ወንጌላውያን ሁሉ በዛሬው ጊዜ ያሉ ቀናተኛ አቅኚዎችም ለጉባኤዎች ታላቅ የብርታት ምንጭ ናቸው። ብዙዎቹ በወር ውስጥ 70 ሰዓት ለማገልገል ጥረት ያደርጋሉ። ታዲያ አንተስ እነዚህን አቅኚዎች ለመርዳት ምን ማድረግ ትችላለህ?

8 ሻሪ የተባለች አንዲት አቅኚ እህት “አቅኚዎች በየቀኑ አገልግሎት ስለሚወጡ ጠንካሮች ይመስላሉ። ያም ቢሆን ማበረታቻ ያስፈልጋቸዋል” ብላለች። (ሮም 1:11, 12) ለተወሰኑ ዓመታት አቅኚ ሆና ያገለገለች ሌላ እህት ደግሞ በጉባኤዋ ስላሉ አቅኚዎች ስትናገር እንዲህ ብላለች፦ “ምንጊዜም ጠንክረው ይሠራሉ። በመሆኑም ሌሎች እነሱን በመኪና ወደ አገልግሎት ቢወስዷቸው፣ ምግብ ቢጋብዟቸው፣ የትራንስፖርት ወጪያቸውን ቢሸፍኑላቸው ወይም ለሌላ ነገር የሚሆን ትንሽ ገንዘብ ቢሰጧቸው በጣም አመስጋኝ ናቸው። እነዚህ ነገሮች እንደምታስቡላቸው ያሳዩዋቸዋል።”

9, 10. አንዳንዶች በጉባኤያቸው ያሉትን አቅኚዎች ለመርዳት ምን አድርገዋል?

9 አቅኚዎችን በአገልግሎት መደገፍ ትፈልጋለህ? ባቢ የተባለ አንድ አቅኚ “በሳምንቱ መሃል አብሮን የሚያገለግል ሰው በጣም ያስፈልገናል” በማለት ስሜቱን ገልጿል። በዚያው ጉባኤ የምታገለግል ሌላ አቅኚ እህት ደግሞ “ከሰዓት በኋላ የአገልግሎት ጓደኛ ማግኘት በጣም አስቸጋሪ ነው” ብላለች። አሁን በብሩክሊን ቤቴል የምታገለግል አንዲት እህት በአቅኚነት ስላሳለፈችው አስደሳች ጊዜ ስታስታውስ እንዲህ ትላለች፦ “መኪና ያላት አንዲት እህት ‘በማንኛውም ጊዜ የአገልግሎት ጓደኛ ካጣሽ ደውዪልኝ፤ አብሬሽ እወጣለሁ’ ብላኝ ነበር። በአቅኚነት አገልግሎት እንድጸና በጣም ረድታኛለች።” ሻሪ ደግሞ ትኩረት ልንሰጠው ስለሚገባ ጉዳይ ስትናገር እንዲህ ብላለች፦ “ነጠላ የሆኑ አቅኚዎች ከአገልግሎት በኋላ አብዛኛውን ጊዜ ብቻቸውን ይሆናሉ። ያላገቡ ወንድሞችንና እህቶችን አልፎ አልፎ በቤተሰብ አምልኳችሁ ላይ ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ። በሌሎች እንቅስቃሴዎችም አብረዋችሁ እንዲካፈሉ ብታደርጉ ይበረታታሉ።”

10 በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ወደ 50 ዓመት ገደማ ያሳለፈች አንዲት እህት ካላገቡ እህቶች ጋር በአቅኚነት ስታገለግል ስለነበረችበት ጊዜ ስትናገር እንዲህ ብላለች፦ “የጉባኤያችን ሽማግሌዎች አቅኚዎችን በየተወሰኑ ወራት የመጠየቅ ልማድ ነበራቸው። ስለ ጤንነታችንና ሥራችን እንዲሁም ሌሎች የሚያስጨንቁን ነገሮች ካሉ ይጠይቁናል። ከልባቸው ያስቡልናል። የሚያስፈልገን ነገር መኖሩን ለማየት ወደምንኖርበት አፓርታማ ይመጣሉ።” ይህ ተሞክሮ፣ ጳውሎስ በኤፌሶን የሚገኝ አንድ የቤተሰብ ኃላፊ ላደረገለት ነገር የተሰማውን አድናቆት ያስታውስህ ይሆናል።—2 ጢሞ. 1:18

11. ልዩ አቅኚዎች ምን ይጠበቅባቸዋል?

11 አንዳንድ ጉባኤዎች ደግሞ አብረዋቸው የሚያገለግሉ ልዩ አቅኚዎች ተመድበውላቸዋል። ከእነዚህ ወንድሞችና እህቶች ብዙዎቹ በወር ውስጥ በመስክ አገልግሎት 130 ሰዓት ለማሳለፍ ጥረት ያደርጋሉ። እነዚህ ክርስቲያኖች በአገልግሎትና በሌሎች የጉባኤ እንቅስቃሴዎች ስለሚጠመዱ ሰብዓዊ ሥራ ለመሥራት የሚኖራቸው ጊዜ በጣም ትንሽ ነው፤ አሊያም ጨርሶ ጊዜ የላቸውም። በአገልግሎታቸው ላይ ትኩረት ማድረግ እንዲችሉ ሲባል ቅርንጫፍ ቢሮው በየወሩ መጠነኛ የሆነ ገንዘብ ይሰጣቸዋል።

12. ሽማግሌዎችና ሌሎች የጉባኤ አባላት ልዩ አቅኚዎችን መርዳት የሚችሉት እንዴት ነው?

12 ልዩ አቅኚዎችን መደገፍ የምንችለው እንዴት ነው? በቅርንጫፍ ቢሮ ውስጥ የሚያገለግልና ከብዙ ልዩ አቅኚዎች ጋር የሚገናኝ አንድ ሽማግሌ እንዲህ ብሏል፦ “ሽማግሌዎች፣ ልዩ አቅኚዎችን ማዋራት፣ ያሉበትን ሁኔታ ማወቅ እንዲሁም እንዴት ሊረዷቸው እንደሚችሉ መወሰን ይኖርባቸዋል። ልዩ አቅኚዎች የተወሰነ ገንዘብ ስለሚሰጣቸው የሚያስፈልጋቸው ሁሉ እንደሚሟላላቸው የሚያስቡ ክርስቲያኖች አሉ፤ ሆኖም በአካባቢያቸው ያሉ ወንድሞች በብዙ መንገዶች ሊረዷቸው ይችላሉ።” እንደ ዘወትር አቅኚዎች ሁሉ ልዩ አቅኚዎችም በመስክ አገልግሎት አብረዋቸው የሚያገለግሉ ጓደኞች ይፈልጋሉ። ታዲያ አንተ በዚህ ረገድ ልትረዳቸው ትችላለህ?

ተጓዥ የበላይ ተመልካቾችን መደገፍ

13, 14. (ሀ) ከወረዳ የበላይ ተመልካቾች ጋር በተያያዘ ምን ማስታወስ ይኖርብናል? (ለ) በወረዳ ሥራ የሚካፈሉትን ለመርዳት ምን ማድረግ ትችላለህ?

13 የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና ሚስቶቻቸው አብዛኛውን ጊዜ በመንፈሳዊ ጠንካራና ብርቱ እንደሆኑ ተደርገው ይታያሉ። ይህ እውነት ቢሆንም እነሱም ማበረታቻና የአገልግሎት ጓደኛ ያስፈልጋቸዋል፤ እንዲሁም ሚዛናዊ በሆነ መዝናኛ አብረውን ቢካፈሉ ደስ ይላቸዋል። ታምመው ሆስፒታል ቢገቡ ምናልባትም ቀዶ ጥገና ወይም ሌላ ዓይነት ሕክምና ቢያስፈልጋቸውስ? በአካባቢያቸው ያሉ ወንድሞችና እህቶች በሚያስፈልጋቸው ነገር ድጋፍ ሲያደርጉላቸውና አሳቢነት ሲያሳዩአቸው እነዚህ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች በጣም እንደሚበረታቱ የታወቀ ነው። የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍን የጻፈው “የተወደደው ሐኪም ሉቃስ” ሐዋርያው ጳውሎስንና የጉዞ ጓደኞቹን ይንከባከባቸው እንደነበር መገመት እንችላለን።—ቆላ. 4:14፤ ሥራ 20:5 እስከ 21:18

14 ተጓዥ የበላይ ተመልካቾችና ሚስቶቻቸው የቅርብ ጓደኞች ያስፈልጓቸዋል፤ እንዲህ ያሉ ወዳጆችንም ከፍ አድርገው ይመለከታሉ። አንድ የወረዳ የበላይ ተመልካች እንዲህ ሲል ጽፏል፦ “ጓደኞቼ መቼ ማበረታቻ እንደሚያስፈልገኝ ያውቃሉ። ማስተዋል የተንጸባረቀባቸው ጥያቄዎች ይጠይቁኛል፤ ይህ ደግሞ ስለሚያሳስቡኝ ነገሮች እንድነግራቸው ያበረታታኛል። የምነግራቸውን ነገር ጆሮ ሰጥተው ማዳመጣቸው በራሱ ትልቅ እገዛ ነው።” የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና ሚስቶቻቸው ወንድሞችና እህቶች የሚያሳዩአቸውን አሳቢነት በጣም ያደንቃሉ።

የቤቴል ቤተሰብ አባላትን መደገፍ

15, 16. በቤቴልና በትላልቅ ስብሰባ አዳራሾች ውስጥ የሚያገለግሉ ክርስቲያኖች ምን ሥራ ያከናውናሉ? ልንደግፋቸው የምንችለውስ እንዴት ነው?

15 በዓለም ዙሪያ በቤቴልና በትላልቅ ስብሰባ አዳራሾች ውስጥ የሚያገለግሉ ክርስቲያኖች በቅርንጫፍ ቢሯቸው ሥር ባሉ አገሮች ውስጥ ለሚከናወነው የመንግሥቱ ሥራ ትልቅ ድጋፍ ያደርጋሉ። ታዲያ በጉባኤያችሁ ወይም በወረዳችሁ ውስጥ ቤቴላውያን ካሉ እንደምታስቧቸው ማሳየት የምትችሉት እንዴት ነው?

16 እነዚህ ክርስቲያኖች ቤቴል ሲገቡ ቤተሰቦቻቸውንና የቅርብ ጓደኞቻቸውን ትተው ስለሚመጡ መጀመሪያ ላይ ናፍቆት ያስቸግራቸው ይሆናል። በመሆኑም ሌሎች ቤቴላውያንና የተመደቡበት ጉባኤ አባላት ሲያቀርቧቸው በጣም እንደሚደሰቱ የታወቀ ነው። (ማር. 10:29, 30) መደበኛ የሥራ ፕሮግራማቸው በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ ለመገኘትና በየሳምንቱ በመስክ አገልግሎት ለመካፈል ያስችላቸዋል። ይሁንና ቤቴላውያን አልፎ አልፎ ተጨማሪ ሥራዎችን መሥራት ይኖርባቸዋል። ጉባኤዎች ይህን በመገንዘብ ቤቴላውያኑን እና የሚያከናውኑትን ሥራ እንደሚያደንቁ ሲያሳዩ ሁሉም ይጠቀማሉ።—1 ተሰሎንቄ 2:9⁠ን አንብብ።

በሌላ አገር የተመደቡ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮችን መደገፍ

17, 18. በሌላ አገር የተመደቡ ክርስቲያኖች በየትኞቹ የአገልግሎት መስኮች ይካፈላሉ?

17 በሌላ አገር ተመድበው የሚያገለግሉ ክርስቲያኖች ከለመዱት በእጅጉ የተለየ ምግብ፣ ቋንቋ፣ ባሕልና ሌሎች ሁኔታዎች ያጋጥሟቸው ይሆናል። ለመሆኑ በሌላ አገር የሚያገለግሉት እነዚህ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ምን ዓይነት የሥራ ምድብ ይሰጣቸዋል?

18 አንዳንዶቹ በዋነኝነት መስክ አገልግሎት ላይ የሚያተኩሩ ሚስዮናውያን ይሆናሉ፤ እነዚህ ክርስቲያኖች ያገኙት ልዩ ሥልጠና ብዙዎችን ይጠቅማል። ቅርንጫፍ ቢሮው፣ ለሚስዮናውያን መኖሪያና መሠረታዊ ወጪዎቻቸውን ለመሸፈን የሚያስችል ገንዘብ ይሰጣቸዋል። በሌላ አገር የሚያገለግሉ ሌሎች ክርስቲያኖች ደግሞ በቅርንጫፍ ቢሮ ውስጥ እንዲሠሩ ወይም በቅርንጫፍ ቢሮዎች፣ በትርጉም ቢሮዎች፣ በትላልቅ ስብሰባ አዳራሾች አሊያም በመንግሥት አዳራሾች ግንባታ እንዲካፈሉ ይመደባሉ። ለእነዚህ ወንድሞች ምግብ፣ መኖሪያና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮች ይቀርቡላቸዋል። እንደ ቤቴል ቤተሰብ አባላት ሁሉ እነሱም አዘውትረው በስብሰባዎች ላይ ይገኛሉ እንዲሁም ከጉባኤው ጋር በአገልግሎት ይካፈላሉ፤ በመሆኑም በተለያዩ መንገዶች ለጉባኤው በረከት ናቸው።

19. በሌላ አገር ስለሚያገለግሉ ክርስቲያኖች ምን ማስታወስ ይኖርብናል?

19 እንዲህ ያሉ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮችን ማሰብ የምንችለው እንዴት ነው? በተለይ ከአገራቸው መጀመሪያ እንደመጡ፣ አንዳንድ የአካባቢውን ምግቦች መልመድ ሊያስቸግራቸው እንደሚችል አስታውሱ። ቤታችሁ ምግብ ስትጋብዟቸው ይህን በአእምሯችሁ መያዛችሁ ጠቃሚ ነው፤ ምናልባትም ምን ዓይነት ምግብ እንደሚመርጡ ወይም መሞከር እንደሚፈልጉ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። የአካባቢውን ቋንቋና ባሕል ለመልመድ ሲሞክሩ በትዕግሥት ያዟቸው። የምትናገሩትን ሁሉ መረዳት እስኪችሉ ድረስ ጊዜ ሊወስድ ይችላል፤ ሆኖም ቃላትን እንዴት መጥራት እንደሚችሉ በደግነት ልታስተምሯቸው ትችላላችሁ። ምክንያቱም ቋንቋውን መማር ይፈልጋሉ!

20. የሙሉ ጊዜ አገልጋዮችንና ወላጆቻቸውን ማሰብ የምንችለው እንዴት ነው?

20 የሙሉ ጊዜ አገልጋዮችም ሆኑ ወላጆቻቸው ማርጀታቸው አይቀርም። የይሖዋ ምሥክሮች የሆኑ ወላጆች፣ ልጆቻቸው በተመደቡበት ቦታ ማገልገላቸውን እንዲቀጥሉ ይፈልጋሉ። (3 ዮሐ. 4) በእርግጥ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች፣ ወላጆቻቸው እርዳታ የሚፈልጉ ከሆነ እነሱን ለመርዳት የተቻላቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፤ ሁኔታቸው በፈቀደላቸው መጠን አዘውትረው እነሱን ለመጠየቅ ይጥራሉ። ያም ቢሆን በዕድሜ የገፉት ወላጆች በሚኖሩበት አካባቢ ያሉ ክርስቲያኖች እነሱን ለመንከባከብ ፈቃደኛ በመሆን የሙሉ ጊዜ አገልጋዮችን መደገፍ ይችላሉ። የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች በዓለም ላይ ከሚከናወኑት ሁሉ እጅግ አስፈላጊ በሆነው ሥራ ላይ ትልቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው መዘንጋት አይኖርብንም። (ማቴ. 28:19, 20) አንተም ሆንክ የጉባኤህ አባላት የአንድ የሙሉ ጊዜ አገልጋይ ወላጆች እርዳታ ካስፈለጋቸው እነሱን መርዳት ትችሉ ይሆን?

21. በሙሉ ጊዜ አገልግሎት የተሰማሩ ክርስቲያኖች ሌሎች ስለሚያደርጉላቸው ድጋፍና ስለሚሰጧቸው ማበረታቻ ምን ይሰማቸዋል?

21 በሙሉ ጊዜ አገልግሎት የሚሰማሩ ክርስቲያኖች ይህን የሚያደርጉት በቁሳዊ ለመበልጸግ ሳይሆን ይሖዋን እና ሌሎችን ማገልገል ስለሚፈልጉ ነው። የምታደርጉላቸውን ድጋፍ ሁሉ ከልብ ያደንቃሉ። በሌላ አገር የምታገለግል አንዲት እህት የተናገረችው ሐሳብ የበርካታ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮችን ስሜት የሚገልጽ ነው፤ እንዲህ ብላለች፦ “አድናቆትን የሚገልጽ አጭር ማስታወሻ እንኳ ሌሎች ስለ እናንተ እንደሚያስቡና በምታከናውኑት ሥራ እንደሚደሰቱ ያሳያል።”

22. ስለ ሙሉ ጊዜ አገልግሎት ምን ይሰማሃል?

22 ይሖዋን ሙሉ ጊዜ ማገልገል እጅግ የሚክስ ምርጫ ነው። ይህ አገልግሎት ተፈታታኝ፣ አስተማሪ እንዲሁም እርካታ የሚያስገኝ ነው። በተጨማሪም ሁሉም ታማኝ የይሖዋ አገልጋዮች በአምላክ መንግሥት አገዛዝ ሥር ለሚጠብቃቸው አስደሳችና ማለቂያ የሌለው አገልግሎት የሙሉ ጊዜ አገልጋዮችን ከአሁኑ የሚያዘጋጅ ግሩም አጋጣሚ ነው። እንግዲያው ሁላችንም የሙሉ ጊዜ አገልጋዮችን ‘የእምነት ሥራ እና ከፍቅር የመነጨ ድካም ዘወትር እናስብ።’—1 ተሰ. 1:3

የሙሉ ጊዜ አገልግሎት መስኮች

  • ሁለት የዘወትር አቅኚዎች ምሥራቹን ለአንድ ሰው ሲሰብኩ
    ሁለት የዘወትር አቅኚዎች ምሥራቹን ለአንድ ሰው ሲሰብኩ

    የዘወትር አቅኚዎች አብዛኛውን ጊዜ በወር 70 ሰዓት በመስክ አገልግሎት ያሳልፋሉ፤ የሚያገለግሉት በጉባኤያቸው ወይም ሰባኪዎች ይበልጥ በሚያስፈልጉበት ቦታ ነው።

  • ሁለት ልዩ አቅኚ እህቶች የመስክ አገልግሎት ላይ
    ሁለት ልዩ አቅኚ እህቶች የመስክ አገልግሎት ላይ

    ልዩ አቅኚዎች አብዛኛውን ጊዜ በወር 130 ሰዓት በመስክ አገልግሎት ያሳልፋሉ፤ ብዙውን ጊዜ የሚመደቡት ሰባኪዎች ይበልጥ በሚያስፈልጉበት ቦታ ነው።

  • አንድ የወረዳ የበላይ ተመልካችና ባለቤቱ በጉዞ ላይ
    አንድ የወረዳ የበላይ ተመልካችና ባለቤቱ በጉዞ ላይ

    የወረዳ የበላይ ተመልካቾች በአገልግሎት ቅድሚያውን ወስደው በመካፈልና ጉባኤዎችን በተለያዩ መንገዶች በመደገፍ በርካታ ጉባኤዎችን ያገለግላሉ።

  • አንድ ቤቴላዊ ጽሑፎችን ሲያሽግ
    አንድ ቤቴላዊ ጽሑፎችን ሲያሽግ

    የቤቴል ቤተሰብ አባላት በቅርንጫፍ ቢሮ ወይም በትርጉም ቢሮ ውስጥ የሚያገለግሉ ሲሆን በሚያገለግሉበት ቅርንጫፍ ቢሮ ሥር ላሉ አገሮች ጽሑፎችን በማቅረቡና አመራር በመስጠቱ ሥራ ይካፈላሉ።

  • አንድ ሚስዮናውያን ባልና ሚስት ሞተር ብስክሌት ላይ ሲወጡ
    አንድ ሚስዮናውያን ባልና ሚስት ሞተር ብስክሌት ላይ ሲወጡ

    ሚስዮናውያን ብዙውን ጊዜ የሚመደቡት በሌላ አገር እንዲያገለግሉ ነው። ብዙ ሚስዮናውያን በወር 130 ሰዓት በመስክ አገልግሎት ያሳልፋሉ።

  • አንድ ዓለም አቀፍ አገልጋይ በግንባታ ሥራ ላይ
    አንድ ዓለም አቀፍ አገልጋይ በግንባታ ሥራ ላይ

    ዓለም አቀፍ አገልጋዮችና ፈቃደኛ ሠራተኞች በቅርንጫፍ ቢሮዎች፣ በትርጉም ቢሮዎች፣ በትላልቅ ስብሰባ አዳራሾችና በመንግሥት አዳራሾች ግንባታ ለመካፈል ወደተለያዩ አገሮች ይሄዳሉ።

  • የመንግሥት አዳራሽ ግንባታ አገልጋይ ጋሪ ሲገፋ
    የመንግሥት አዳራሽ ግንባታ አገልጋይ ጋሪ ሲገፋ

    የመንግሥት አዳራሽ ግንባታ አገልጋዮች በአገራቸው የመንግሥት አዳራሾችን እንዲገነቡና በሌሎች የግንባታ ሥራዎች እገዛ እንዲያደርጉ ይሠለጥናሉ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ