የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w15 4/1 ገጽ 15
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አንድ መቶ አለቃ ትልቅ እምነት አሳየ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • ሮማዊው ደግ የመቶ አለቃ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ይሖዋ እኔን የሚመለከተኝ እንዴት ነው?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2014
  • የአውራጃ ስብሰባው ለአምላክ ክብር እንድንሰጥ አነሳስቶናል!
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
w15 4/1 ገጽ 15

ይህን ያውቁ ኖሯል?

በሮም የጦር ሠራዊት ውስጥ የአንድ የመቶ አለቃ የሥራ ድርሻ ምን ነበር?

የሮምን የመቶ አለቃ የሚያሳይ ሐውልት

ማርከስ ፋቮኒየስ ፋሲለስ የተባለውን የመቶ አለቃ የሚያሳይ ሐውልት

የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት በተለያየ ቦታ ላይ ስለ ሮም ሠራዊት የመቶ አለቃ ይናገራሉ። ኢየሱስ ሲገደል በቦታው የነበረው ወታደር የመቶ አለቃ ነበር፤ እንዲሁም የአሕዛብ ወገን ከሆኑ ሰዎች ወደ ክርስትና ለመለወጥ የመጀመሪያ የሆነው ቆርኔሌዎስ የመቶ አለቃ ነበር። ሐዋርያው ጳውሎስን ሊያስገርፈው የነበረው ወታደርም ሆነ ጳውሎስን ወደ ሮም የወሰደው ዩልዮስ የመቶ አለቃ ማዕረግ ነበራቸው።—ማርቆስ 15:39፤ የሐዋርያት ሥራ 10:1፣ የግርጌ ማስታወሻ፤ 22:25፤27:1

አንድ የመቶ አለቃ አብዛኛውን ጊዜ ከ50 እስከ 100 የሚሆኑ እግረኛ ወታደሮችን ያቀፈ ሠራዊት ያስተዳድራል። የመቶ አለቃው ካሉበት ኃላፊነቶች መካከል በእሱ ሥር ላሉት ወታደሮች ሥልጠና መስጠት፣ ልብሳቸውንና ትጥቃቸውን መገምገም እንዲሁም ለክተት እንዲዘጋጁ ማዘዝ ይገኙበታል።

አንድ ተራ ወታደር ሊያገኝ የሚችለው የመጨረሻው ከፍተኛ ማዕረግ የመቶ አለቃነት ነው። ይህ ማዕረግ ይሰጥ የነበረው ለረጅም ጊዜ በውትድርና ላገለገሉና ጥሩ አመራር የመስጠት ችሎታ ላላቸው ወታደሮች ነው። የሮም የጦር ሠራዊት ዲሲፕሊን ያለውና ውጤታማ መሆኑ የተመካው በእነዚህ የመቶ አለቃዎች ላይ ነበር። አንድ የመረጃ ምንጭ እንደገለጸው የመቶ አለቃዎች “አብዛኛውን ጊዜ በሠራዊቱ ውስጥ ካሉት ወታደሮች ሁሉ የበለጠ ከፍተኛ ልምድና ጥሩ እውቀት ያላቸው ነበሩ።”

በጥንት ዘመን የነበረው መስተዋት ከአሁኑ ዘመን የሚለየው እንዴት ነው?

ጥንታዊ የግብፃውያን መስተዋት

ጥንታዊ የግብፃውያን መስተዋት

በዘመናችን ካሉት የብርጭቆ መስተዋቶች በተለየ መልኩ በጥንት ዘመን መስተዋት የሚሠራው በደንብ ከታሹ ማዕድናት ነበር፤ አብዛኛውን ጊዜ ይጠቀሙበት የነበረው ማዕድን ነሐስ ሲሆን ከመዳብ፣ ከብር፣ ከወርቅ ወይም ኤሌክትረም ከተባለ በተፈጥሮ የሚገኝ የወርቅና የብር ቅይጥም ሊሠራ ይችል ነበር። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ፣ መስተዋት ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሰው የማደሪያው ድንኳን ተብሎ ከሚጠራው የእስራኤላውያን የአምልኮ ማዕከል ግንባታ ጋር በተያያዘ ነው። ለቅዱስ አገልግሎት ይውል የነበረውን የመዳብ ገንዳና ማስቀመጫውን ለመሥራት ሴቶች መስተዋታቸውን ሰጥተው ነበር። (ዘፀአት 38:8) መስተዋቶቹ ለዚህ ሥራ የዋሉት ከቀለጡ በኋላ ሳይሆን አይቀርም።

በእስራኤልና በአካባቢው በተደረጉ የአርኪኦሎጂ ቁፋሮዎች፣ መስተዋቶች ብዙውን ጊዜ ከጌጣ ጌጦችና ከሌሎች የሴቶች መዋቢያ ዕቃዎች ጋር ተገኝተዋል። በአጠቃላይ ሲታይ እነዚህ መስተዋቶች ክብ ቅርጽ የነበራቸው ሲሆን ባጌጠ እንጨት፣ ብረት ወይም የዝሆን ጥርስ የተሠሩና በአብዛኛው የሴት ሰውነት ቅርጽ ያላቸው እጀታዎች ነበሯቸው። ያልታሸው የመስተዋቱ የኋለኛው ክፍል አብዛኛውን ጊዜ ምንም ዓይነት ጌጥ አይደረግበትም።

ጥንታዊዎቹ መስተዋቶች በዘመናችን ካሉት የብርጭቆ መስተዋቶች ጋር ሲነጻጸሩ ጥርት አድርጎ የማሳየት ችሎታቸው አነስተኛ ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ “አሁን በብረት መስተዋት ብዥ ያለ ምስል ይታየናል” በማለት የተናገረው ከዚህ አንጻር ሳይሆን አይቀርም።—1 ቆሮንቶስ 13:12

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ