የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w15 11/15 ገጽ 14-15
  • ለይሖዋ ለጋስነት አድናቆት አሳዩ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለይሖዋ ለጋስነት አድናቆት አሳዩ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ከሁሉ የላቀ የልግስና ምሳሌ
  • “ሥራው . . . ታላቅ ነው”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016
  • የእነሱ ትርፍ የሌሎችን ጉድለት ሸፈነ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ይሖዋ በፈቃደኝነት የሚሰጡትን አብዝቶ ይባርካል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • ሌሎች የሚያስፈልጋቸውን ነገር ማሟላት የምንችለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
w15 11/15 ገጽ 14-15
አንዲት ሴት የባንክ ካርዷን የኤሌክትሮኒክ ካርድ ማንበቢያ ማሽን ውስጥ ስትከት

ለይሖዋ ለጋስነት አድናቆት አሳዩ

ይሖዋ ለጋስ አምላክ ነው። (ያዕ. 1:17) በምሽት ጨለማ በከዋክብት ተሞልተው የሚታዩት ሰማያትም ሆኑ ምድርን የሸፈናት ልምላሜ እንዲሁም ሌሎቹ የይሖዋ ፍጥረታት በአጠቃላይ የእሱን ልግስና ያንጸባርቃሉ።—መዝ. 65:12, 13፤ 147:7, 8፤ 148:3, 4

መዝሙራዊው ለፈጣሪው የነበረው አድናቆት እጅግ ጥልቅ ከመሆኑ የተነሳ የይሖዋን ሥራዎች የሚያወድስ መዝሙር ለማቀናበር ተገፋፍቷል። አንተም 104ኛውን መዝሙር ስታነብ የመዝሙራዊውን ስሜት እንደምትጋራ ምንም ጥርጥር የለውም። መዝሙራዊው “በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ለይሖዋ እዘምራለሁ፤ በሕይወት እስካለሁ ድረስ ለአምላኬ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ” ብሏል። (መዝ. 104:33) የአንተስ ምኞት ይህ ነው?

ከሁሉ የላቀ የልግስና ምሳሌ

ይሖዋ በልግስና ረገድ የእሱን ምሳሌ እንድንከተል ይፈልጋል። እንዲሁም ለጋስ ለመሆን የሚያነሳሱን አጥጋቢ ምክንያቶች ሰጥቶናል። ሐዋርያው ጳውሎስ በአምላክ መንፈስ መሪነት ያሰፈረውን ሐሳብ ልብ በል፦ “አሁን ባለው ሥርዓት ሀብታም የሆኑትን ሰዎች እንዳይታበዩ እንዲሁም ተስፋቸውን አስተማማኝነት በሌለው ሀብት ላይ ሳይሆን የሚያስደስቱንን ነገሮች ሁሉ አትረፍርፎ በሚሰጠን አምላክ ላይ እንዲጥሉ እዘዛቸው። በተጨማሪም መልካም ነገር እንዲያደርጉ፣ በመልካም ሥራዎች ባለጸጋ እንዲሆኑ እንዲሁም ለጋሶችና ለሌሎች ለማካፈል ፈቃደኞች እንዲሆኑ ምከራቸው፤ እውነተኛ የሆነውን ሕይወት አጥብቀው መያዝ ይችሉ ዘንድ ለራሳቸው ውድ ሀብት ማከማቸታቸውን ይኸውም ለወደፊቱ ጊዜ የሚሆን መልካም መሠረት መጣላቸውን ይቀጥሉ።”—1 ጢሞ. 6:17-19

ጳውሎስ በቆሮንቶስ ለሚገኘው ጉባኤ በመንፈስ መሪነት ሁለተኛውን ደብዳቤ በጻፈ ጊዜ ልግስናን በተመለከተ ሊኖረን የሚገባውን ትክክለኛ አመለካከት ጎላ አድርጎ ገልጿል። ጳውሎስ “አምላክ በደስታ የሚሰጠውን ሰው ስለሚወድ እያንዳንዱ ሰው ቅር እያለው ወይም ተገዶ ሳይሆን በልቡ ያሰበውን ይስጥ” ብሏል። (2 ቆሮ. 9:7) ጳውሎስ ቀጥሎም ልግስና እነማንን እንደሚጠቅም ገልጿል፤ ስጦታውን የሚቀበሉት ሰዎች የጎደላቸው ነገር ይሟላላቸዋል፤ ሰጪዎቹ ደግሞ መንፈሳዊ በረከት ያገኛሉ።—2 ቆሮ. 9:11-14

ጳውሎስ ሐሳቡን ሲደመድም፣ አምላክ ለጋስ መሆኑን የሚያሳየውን ከሁሉ የላቀ ማስረጃ ጠቅሷል። ጳውሎስ “በቃላት ሊገለጽ ለማይችለው ነፃ ስጦታው አምላክ የተመሰገነ ይሁን” በማለት ጽፏል። (2 ቆሮ. 9:15) የይሖዋ ስጦታ፣ አምላክ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለሕዝቦቹ የዘረጋውን የጥሩነቱን መግለጫዎች ሁሉ እንደሚያጠቃልል ግልጽ ነው። ስጦታው እጅግ የላቀ ዋጋ ያለው በመሆኑ በቃላት ሊገለጽ አይችልም።

ታዲያ ይሖዋና ልጁ ላደረጉልን እንዲሁም ወደፊት ለሚያደርጉልን ነገር ሁሉ አድናቆት ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? አንዱ መንገድ መጠኑ አነሰ በዛ ሳንል ጊዜያችንን፣ ጉልበታችንንና ጥሪታችንን የይሖዋን ንጹሕ አምልኮ ለማራመድ በልግስና በመስጠት ነው።—1 ዜና 22:14፤ 29:3-5፤ ሉቃስ 21:1-4

አንዳንዶች ለዓለም አቀፉ ሥራ መዋጮ የሚያደርጉባቸው መንገዶች

በሐዋርያው ጳውሎስ ዘመን እንደነበረው ሁሉ በዛሬው ጊዜም ብዙ ሰዎች፣ “ለዓለም አቀፉ ሥራ” ተብሎ የተለጠፈባቸው የጉባኤ ሣጥኖች ውስጥ የሚጨምሩት “የተወሰነ ገንዘብ” ያስቀምጣሉ ወይም ይመድባሉ። (1 ቆሮ. 16:2) ጉባኤዎች የተዋጣውን ገንዘብ በአገራቸው ሥራውን ለሚመራው የይሖዋ ምሥክሮች ቢሮ በየወሩ ይልካሉ። አንተም በአገርህ የይሖዋ ምሥክሮች ለሚጠቀሙበት ሕጋዊ ተቋም የገንዘብ መዋጮ በቀጥታ መላክ ትችላለህ። በምትኖርበት አገር የይሖዋ ምሥክሮች የሚጠቀሙበትን ዋነኛ ሕጋዊ ተቋም ስም ለማወቅ ቅርንጫፍ ቢሮውን ማነጋገር ትችላለህ። የቅርንጫፍ ቢሮው አድራሻ www.jw.org/am በተባለው ድረ ገጽ ላይ ይገኛል። ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ዓይነት መዋጮዎች በቀጥታ ለቢሮው መላክ ትችላለህ፦

የገንዘብና የቁሳቁስ መዋጮዎች

  • በባንክ በኩል የሚደረግ ኤሌክትሮኒክ የገንዘብ ዝውውርን እንዲሁም ዴቢት ካርድ ወይም ክሬዲት ካርድ በመጠቀም የሚደረግ መዋጮን ያካትታል። በአንዳንድ ቅርንጫፍ ቢሮዎች jw.org የተሰኘውን ድረ ገጽ ወይም ለዚህ ዓላማ የተዘጋጀ ሌላ ድረ ገጽ መጠቀም ይቻላል።

  • ገንዘብ፣ ውድ ጌጣጌጦችን ወይም ሌሎች ውድ ንብረቶችን በመዋጮ መልክ መስጠት ይቻላል። የምትልከው ገንዘብ ወይም ዕቃ በመዋጮ መልክ የተሰጠ መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ አያይዘህ ላክ።

ተመላሽ ሊሆን የሚችል ገንዘብ የሚሰጥበት ዝግጅት

  • አንድ ሰው ገንዘብ ሊሰጥና ባስፈለገው ጊዜ ገንዘቡ እንዲመለስለት ሊጠይቅ ይችላል።

  • የሰጠኸው ገንዘብ እንዲመለስልህ የምትፈልግ መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ አያይዘህ ላክ።

በዕቅድ የሚደረግ ስጦታ

ገንዘብና ውድ ንብረቶች በስጦታ ከመለገስ በተጨማሪ በመላው ዓለም የሚካሄደውን የመንግሥቱን ሥራ መደገፍ የሚቻልባቸው ሌሎች መንገዶች አሉ። እነሱም ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል። መዋጮ ለመስጠት የምትጠቀምበት መንገድ ምንም ሆነ ምን፣ ከቀረቡት አማራጮች መካከል የትኞቹን መጠቀም እንደምትችል ለማወቅ አንተ በምትኖርበት አገር ለሚካሄደው ሥራ አመራር የሚሰጠውን ቅርንጫፍ ቢሮ አስቀድመህ አነጋግር። የየአገሩ ሕጋዊ አሠራሮችና የቀረጥ ደንቦች የተለያዩ ሊሆኑ ስለሚችሉ መዋጮ የምታደርግበትን የተሻለ መንገድ ከመምረጥህ በፊት ከቀረጥና ከሕግ ጋር በተያያዘ ብቃት ያለው ባለሙያ ማማከርህ በጣም አስፈላጊ ነው።

ኢንሹራንስ፦ በምትኖርበት አገር ውስጥ የይሖዋ ምሥክሮች የሚጠቀሙበት ሕጋዊ ተቋም፣ የሕይወት ኢንሹራንስ ፖሊሲ ወይም የጡረታ ክፍያ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ ትችላለህ።

የባንክ ሒሳብ፦ የአገሩ የባንክ ደንብ በሚፈቅደው መሠረት የባንክ ሒሳቦችን፣ ገንዘብ መቀመጡን የሚገልጽ የምሥክር ወረቀትን አሊያም የግል ጡረታ ሒሳቦችን በአደራ ወይም በሞት ጊዜ የሚከፈል መሆኑ ተገልጾ የይሖዋ ምሥክሮች ለሚጠቀሙበት ሕጋዊ ተቋም መስጠት ይቻላል።

አክሲዮኖችና ቦንዶች፦ አክሲዮኖችንና ቦንዶችን በስጦታ መልክ ማበርከት ወይም ደግሞ ግለሰቡ ሲሞት የይሖዋ ምሥክሮች ለሚጠቀሙበት ሕጋዊ ተቋም እንዲሰጥ ማድረግ ይቻላል።

የማይንቀሳቀስ ንብረት፦ የይሖዋ ምሥክሮች ለሚጠቀሙበት ሕጋዊ ተቋም፣ ሊሸጥ ሊለወጥ የሚችል የማይንቀሳቀስ ንብረት በስጦታ መስጠት ወይም መኖሪያ ቤት በሚሆንበት ጊዜ ደግሞ ባለ ንብረቱ በሕይወት እስካለ ድረስ ሲጠቀምበት ቆይቶ ከዚያ በኋላ ማውረስ ይቻላል።

የስጦታ አበል፦ አንድ ሰው ገንዘቡን ወይም የባለቤትነት መብቱን የሚያረጋግጡ ሰነዶችን የይሖዋ ምሥክሮች ለሚጠቀሙበት ሕጋዊ ተቋም በስጦታ መልክ መስጠት ይችላል። በምላሹም ለጋሹ በሕይወት እስካለበት ጊዜ ድረስ የተወሰነ መጠን ያለው ገንዘብ በየዓመቱ በአበል መልክ ይከፈለዋል። ለጋሹ የስጦታ አበሉን ለማስተላለፍ በተስማማበት ዓመት የገቢ ግብር ቅናሽ ሊያገኝ ይችላል።

ኑዛዜዎችና አደራዎች፦ ንብረት ወይም ገንዘብ በሕግ ፊት ተቀባይነት ባለው ኑዛዜ አማካኝነት፣ የይሖዋ ምሥክሮች ለሚጠቀሙበት ሕጋዊ ተቋም በውርስ ሊሰጥ ወይም ሕጋዊ ተቋሙ በአደራ የተሰጠው ንብረት ተጠቃሚ እንደሆነ ሊገለጽ ይችላል። ይህ ዝግጅት ከቀረጥ ጋር የተያያዙ አንዳንድ ጥቅሞች ሊያስገኝ ይችላል።

“በዕቅድ የሚደረግ ስጦታ” የሚለው አገላለጽ፣ እነዚህን የመሳሰሉ መዋጮዎች የሚያደርገው ግለሰብ ዕቅድ ማውጣት እንደሚያስፈልገው ይጠቁማል። የይሖዋ ምሥክሮችን ዓለም አቀፍ ሥራ በዕቅድ በሚደረግ ስጦታ መደገፍ ለሚፈልጉ ግለሰቦች ጉዳዩን ይበልጥ ግልጽ ለማድረግ ሲባል ዓለም አቀፉን የመንግሥቱን ስብከት ሥራ ለመደገፍ በዕቅድ የሚደረግ ስጦታ የሚል ብሮሹር በእንግሊዝኛና በስፓንኛ ተዘጋጅቷል። ይህ ብሮሹር የተዘጋጀው ሰዎች ስጦታ ለመስጠት ወይም በሚሞቱበት ጊዜ በኑዛዜ ውርስ ለመተው የሚችሉባቸውን የተለያዩ መንገዶች አስመልክቶ መረጃ ለመስጠት ነው። በዚህ ብሮሹር ላይ የቀረበው መረጃ አንተ በምትኖርበት አገር ከሚሠራባቸው የቀረጥ ወይም ሌሎች ጉዳዮችን ከሚመለከቱ ሕጎች ጋር ሙሉ በሙሉ ላይጣጣም ይችላል። በመሆኑም ይህን ብሮሹር ካነበብክ በኋላ ከሕግ ወይም ከቀረጥ አማካሪዎችህ ጋር መመካከር ይኖርብሃል። ስጦታ ማድረግ የሚቻልባቸውን እንዲህ ያሉ ዘዴዎች በመጠቀም ብዙዎች በዓለም ዙሪያ የምናከናውነውን ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴና ሰብዓዊ እርዳታ መደገፍ ከመቻላቸውም በላይ ከቀረጥ ጋር በተያያዘ የተሻለ ጥቅም ማግኘት ችለዋል። ይህ ብሮሹር አንተ ባለህበት አገር ውስጥ የሚገኝ ከሆነ የጉባኤህን ጸሐፊ በመጠየቅ ማግኘት ትችላለህ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ቅርንጫፍ ቢሮውን ማነጋገር ትችላለህ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ