የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w16 ኅዳር ገጽ 19-20
  • “ሥራው . . . ታላቅ ነው”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ሥራው . . . ታላቅ ነው”
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለይሖዋ ለጋስነት አድናቆት አሳዩ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ይሖዋ በፈቃደኝነት የሚሰጡትን አብዝቶ ይባርካል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • የእነሱ ትርፍ የሌሎችን ጉድለት ሸፈነ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ሌሎች የሚያስፈልጋቸውን ነገር ማሟላት የምንችለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016
w16 ኅዳር ገጽ 19-20

‘ሥራው ታላቅ ነው’

በኢየሩሳሌም አንድ በጣም አስፈላጊ ስብሰባ እየተካሄደ ነው። ንጉሥ ዳዊት መኳንንቱን፣ የቤተ መንግሥት ባለ ሥልጣናቱን እንዲሁም ኃያላኑን በሙሉ ሰበሰበ። ሁሉም በስብሰባው ላይ አንድ ልዩ ማስታወቂያ በመስማታቸው በጣም ተደሰቱ። ይሖዋ፣ የዳዊት ልጅ የሆነውን ሰለሞንን ለእሱ አምልኮ የሚሆን ታላቅ ቤተ መቅደስ እንዲሠራ መርጦታል። ይሖዋ የሕንፃውን ንድፍ በዕድሜ ለገፋው የእስራኤል ንጉሥ በመንፈስ የገለጠለት ሲሆን ንጉሡም ይህን ንድፍ ለሰለሞን ሰጠው። ከዚያም ዳዊት “ሥራው . . . ታላቅ ነው፤ ቤተ መቅደሱ የሚሠራው ለሰው ሳይሆን ለይሖዋ አምላክ ነውና” በማለት ተናገረ።—1 ዜና 28:1, 2, 6, 11, 12፤ 29:1

ዳዊት በመቀጠል “ታዲያ ዛሬ ለይሖዋ የሚሰጥ ስጦታ በእጁ ይዞ ለመቅረብ ፈቃደኛ የሆነ ማን ነው?” ሲል ጠየቀ። (1 ዜና 29:5) አንተ በቦታው ብትኖር ኖሮ ምን ምላሽ ትሰጥ ነበር? ይህን ታላቅ ሥራ ለመደገፍ ትነሳሳ ነበር? እስራኤላውያን ፈጣን ምላሽ ሰጡ። ዘገባው እንደሚገልጸው “በፈቃደኝነት መባ በመስጠታቸው እጅግ ተደሰቱ፤ በፈቃደኝነት ተነሳስተው ለይሖዋ መባ የሰጡት በሙሉ ልባቸው ነበርና።”—1 ዜና 29:9

ከብዙ መቶ ዘመናት በኋላ ይሖዋ ከቤተ መቅደሱ የሚበልጥ ዝግጅት አደረገ። ታላቁን መንፈሳዊ ቤተ መቅደስ፣ ይኸውም በኢየሱስ መሥዋዕት አማካኝነት ሰዎች እሱን ማምለክ የሚችሉበትን ዝግጅት አቋቋመ። (ዕብ. 9:11, 12) በዛሬው ጊዜ ይሖዋ ሰዎች ከእሱ ጋር እንዲታረቁ እያደረገ ያለው እንዴት ነው? ደቀ መዛሙርት በማድረጉ ሥራችን አማካኝነት ነው። (ማቴ. 28: 19, 20) በዚህ ሥራችን የተነሳ በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ይመራሉ፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ደቀ መዛሙርት ይጠመቃሉ፤ እንዲሁም በመቶዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ ጉባኤዎች ይመሠረታሉ።

እንዲህ ያለ እድገት መኖሩ ደግሞ ተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎችን ማተም፣ የመንግሥት አዳራሾችን መገንባትና ማደስ እንዲሁም የትላልቅ ስብሰባ አዳራሾችን ማግኘት አስፈላጊ እንዲሆን ያደርጋል። ምሥራቹን የማስፋፋቱ ሥራ ታላቅና የሚክስ ነው ቢባል አትስማማም?—ማቴ. 24:14

የአምላክ ሕዝቦች ለአምላክና ለባልንጀራቸው ፍቅር ያላቸው መሆኑ እንዲሁም የመንግሥቱን ምሥራች መስበክ አጣዳፊ መሆኑን መገንዘባቸው፣ በፈቃደኝነት መዋጮ በማድረግ ‘ለይሖዋ የሚሰጥ ስጦታ በእጃቸው ይዘው እንዲቀርቡ’ ያነሳሳቸዋል። ‘ባሉን ውድ ነገሮች ይሖዋን ማክበር’ መቻላችን እንዲሁም ድርጅቱ የምናደርገውን መዋጮ በሰው ዘር ታሪክ ውስጥ ከሁሉ ይበልጥ ታላቅ የሆነውን ሥራ ለመሥራት በታማኝነትና በጥበብ ሲጠቀምበት ማየታችን ምንኛ አስደሳች ነው!—ምሳሌ 3:9

አንዳንዶች ለዓለም አቀፉ ሥራ መዋጮ የሚያደርጉባቸው መንገዶች

ብዙ ሰዎች፣ “ለዓለም አቀፉ ሥራ” ተብሎ የተለጠፈባቸው የጉባኤ ሣጥኖች ውስጥ የሚጨምሩት “የተወሰነ ገንዘብ” ያስቀምጣሉ ወይም ይመድባሉ። (1 ቆሮ. 16:2) ጉባኤዎች የተዋጣውን ገንዘብ በአገራቸው ሥራውን ለሚመራው የይሖዋ ምሥክሮች ቢሮ በየወሩ ይልካሉ። አንተም በአገርህ የይሖዋ ምሥክሮች ለሚጠቀሙበት ሕጋዊ ተቋም የገንዘብ መዋጮ በቀጥታ መላክ ትችላለህ። በምትኖርበት አገር የይሖዋ ምሥክሮች የሚጠቀሙበትን ዋነኛ ሕጋዊ ተቋም ስም ለማወቅ ቅርንጫፍ ቢሮውን ማነጋገር ትችላለህ። የቅርንጫፍ ቢሮው አድራሻ www.jw.org/am በተባለው ድረ ገጽ ላይ ይገኛል። ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ዓይነት መዋጮዎች በቀጥታ ለቢሮው መላክ ትችላለህ፦

የገንዘብና የቁሳቁስ መዋጮዎች

  • በባንክ በኩል የሚደረግ ኤሌክትሮኒክ የገንዘብ ዝውውርን እንዲሁም ዴቢት ካርድ፣ ክሬዲት ካርድ ወይም ሞባይል ስልክ በመጠቀም የሚደረግ መዋጮን ያካትታል። በአንዳንድ ቅርንጫፍ ቢሮዎች jw.org የተሰኘውን ድረ ገጽ ወይም ለዚህ ዓላማ የተዘጋጀ ሌላ ድረ ገጽ መጠቀም ይቻላል።

  • ገንዘብ፣ ውድ ጌጣጌጦችን ወይም ሌሎች ውድ ንብረቶችን በመዋጮ መልክ መስጠት ይቻላል። የምትልከው ገንዘብ ወይም ዕቃ በመዋጮ መልክ የተሰጠ መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ አያይዘህ ላክ።

ተመላሽ ሊሆን የሚችል ገንዘብ የሚሰጥበት ዝግጅት

  • አንድ ሰው ገንዘብ ሊሰጥና ባስፈለገው ጊዜ ገንዘቡ እንዲመለስለት ሊጠይቅ ይችላል።

  • የሰጠኸው ገንዘብ እንዲመለስልህ የምትፈልግ መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ አያይዘህ ላክ።

በዕቅድ የሚደረግ ስጦታ

ገንዘብና ውድ ንብረቶች በስጦታ ከመለገስ በተጨማሪ በመላው ዓለም የሚካሄደውን የመንግሥቱን ሥራ መደገፍ የሚቻልባቸው ሌሎች መንገዶች አሉ። እነሱም ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል። መዋጮ ለመስጠት የምትጠቀምበት መንገድ ምንም ሆነ ምን፣ ከቀረቡት አማራጮች መካከል የትኞቹን መጠቀም እንደምትችል ለማወቅ አንተ በምትኖርበት አገር ለሚካሄደው ሥራ አመራር የሚሰጠውን ቅርንጫፍ ቢሮ አስቀድመህ አነጋግር። የየአገሩ ሕጋዊ አሠራሮችና የቀረጥ ደንቦች የተለያዩ ሊሆኑ ስለሚችሉ መዋጮ የምታደርግበትን የተሻለ መንገድ ከመምረጥህ በፊት ከቀረጥና ከሕግ ጋር በተያያዘ ብቃት ያለው ባለሙያ ማማከርህ በጣም አስፈላጊ ነው።

ኢንሹራንስ፦ በምትኖርበት አገር ውስጥ የይሖዋ ምሥክሮች የሚጠቀሙበት ሕጋዊ ተቋም፣ የሕይወት ኢንሹራንስ ፖሊሲ ወይም የጡረታ ክፍያ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ ትችላለህ።

የባንክ ሒሳብ፦ የአገሩ የባንክ ደንብ በሚፈቅደው መሠረት የባንክ ሒሳቦችን፣ ገንዘብ መቀመጡን የሚገልጽ የምሥክር ወረቀትን አሊያም የግል ጡረታ ሒሳቦችን በአደራ ወይም በሞት ጊዜ የሚከፈል መሆኑ ተገልጾ የይሖዋ ምሥክሮች ለሚጠቀሙበት ሕጋዊ ተቋም መስጠት ይቻላል።

አክሲዮኖችና ቦንዶች፦ አክሲዮኖችንና ቦንዶችን በስጦታ መልክ ማበርከት ወይም ደግሞ ግለሰቡ ሲሞት የይሖዋ ምሥክሮች ለሚጠቀሙበት ሕጋዊ ተቋም እንዲሰጥ ማድረግ ይቻላል።

የማይንቀሳቀስ ንብረት፦ የይሖዋ ምሥክሮች ለሚጠቀሙበት ሕጋዊ ተቋም፣ ሊሸጥ ሊለወጥ የሚችል የማይንቀሳቀስ ንብረት በስጦታ መስጠት ወይም መኖሪያ ቤት በሚሆንበት ጊዜ ደግሞ ባለ ንብረቱ በሕይወት እስካለ ድረስ ሲጠቀምበት ቆይቶ ከዚያ በኋላ ማውረስ ይቻላል።

የስጦታ አበል፦ አንድ ሰው ገንዘቡን ወይም የባለቤትነት መብቱን የሚያረጋግጡ ሰነዶችን የይሖዋ ምሥክሮች ለሚጠቀሙበት ሕጋዊ ተቋም በስጦታ መልክ መስጠት ይችላል። በምላሹም ለጋሹ በሕይወት እስካለበት ጊዜ ድረስ የተወሰነ መጠን ያለው ገንዘብ በየዓመቱ በአበል መልክ ይከፈለዋል። ለጋሹ የስጦታ አበሉን ለማስተላለፍ በተስማማበት ዓመት የገቢ ግብር ቅናሽ ሊያገኝ ይችላል።

ኑዛዜዎችና አደራዎች፦ ንብረት ወይም ገንዘብ በሕግ ፊት ተቀባይነት ባለው ኑዛዜ አማካኝነት፣ የይሖዋ ምሥክሮች ለሚጠቀሙበት ሕጋዊ ተቋም በውርስ ሊሰጥ ወይም ሕጋዊ ተቋሙ በአደራ የተሰጠው ንብረት ተጠቃሚ እንደሆነ ሊገለጽ ይችላል። ይህ ዝግጅት ከቀረጥ ጋር የተያያዙ አንዳንድ ጥቅሞች ሊያስገኝ ይችላል።

“በዕቅድ የሚደረግ ስጦታ” የሚለው አገላለጽ፣ እነዚህን የመሳሰሉ መዋጮዎች የሚያደርገው ግለሰብ ዕቅድ ማውጣት እንደሚያስፈልገው ይጠቁማል። የይሖዋ ምሥክሮችን ዓለም አቀፍ ሥራ በዕቅድ በሚደረግ ስጦታ መደገፍ ለሚፈልጉ ግለሰቦች ጉዳዩን ይበልጥ ግልጽ ለማድረግ ሲባል ዓለም አቀፉን የመንግሥቱን ስብከት ሥራ ለመደገፍ በዕቅድ የሚደረግ ስጦታ የሚል ብሮሹር ተዘጋጅቷል። በእንግሊዝኛና በስፓንኛ የተዘጋጀው የዚህ ብሮሹር ዓላማ፣ ሰዎች ስጦታ ለመስጠት ወይም በሚሞቱበት ጊዜ በኑዛዜ ውርስ ለመተው የሚችሉባቸውን የተለያዩ መንገዶች አስመልክቶ መረጃ መስጠት ነው። በዚህ ብሮሹር ላይ የቀረበው መረጃ አንተ በምትኖርበት አገር ከሚሠራባቸው የቀረጥ ወይም ሌሎች ጉዳዮችን ከሚመለከቱ ሕጎች ጋር ሙሉ በሙሉ ላይጣጣም ይችላል። ስጦታ ማድረግ የሚቻልባቸውን እንዲህ ያሉ ዘዴዎች በመጠቀም ብዙዎች በዓለም ዙሪያ የምናከናውነውን ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴና ሰብዓዊ እርዳታ መደገፍ ከመቻላቸውም በላይ ከቀረጥ ጋር በተያያዘ የተሻለ ጥቅም ማግኘት ችለዋል። ይህ ብሮሹር አንተ ባለህበት አገር ውስጥ የሚገኝ ከሆነ የጉባኤህን ጸሐፊ በመጠየቅ ማግኘት ትችላለህ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በjw.org መነሻ ገጽ ግርጌ ላይ የሚገኘውን “ለዓለም አቀፉ ሥራችን የገንዘብ መዋጮ ለማድረግ” የሚለውን ሊንክ መጠቀም አሊያም ቅርንጫፍ ቢሮውን ማነጋገር ትችላለህ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ