የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w17 ኅዳር ገጽ 18-19
  • “ለጋስ ሰው ይባረካል”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ለጋስ ሰው ይባረካል”
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “ሥራው . . . ታላቅ ነው”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016
  • ለይሖዋ ለጋስነት አድናቆት አሳዩ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • የእነሱ ትርፍ የሌሎችን ጉድለት ሸፈነ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ይሖዋ በፈቃደኝነት የሚሰጡትን አብዝቶ ይባርካል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017
w17 ኅዳር ገጽ 18-19
ሐና ትንሹን ሳሙኤልን ወደ ማደሪያው ድንኳን ስታመጣው

“ለጋስ ሰው ይባረካል”

መሥዋዕት ማቅረብ ከጥንትም ጀምሮ የእውነተኛው አምልኮ ዋነኛ ክፍል ነበር። እስራኤላውያን የእንስሳት መሥዋዕት ያቀርቡ የነበረ ሲሆን ክርስቲያኖችም የሚታወቁት “የውዳሴ መሥዋዕት” በማቅረብ ነው። ሆኖም አምላክን እጅግ የሚያስደስቱት ሌሎች መሥዋዕቶችም አሉ። (ዕብ. 13:15, 16) ቀጥሎ የቀረቡት ምሳሌዎች እንደሚያሳዩት እነዚህ መሥዋዕቶች ደስታና በረከት ያመጣሉ።

በጥንት ዘመን የኖረችው ሐና የተባለች ታማኝ የአምላክ አገልጋይ፣ ወንድ ልጅ ለመውለድ በጣም ብትመኝም መሃን ነበረች። ሐና፣ ወንድ ልጅ ብትወልድ “በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ለይሖዋ [እንደምትሰጠው]” በጸሎት በመግለጽ ተሳለች። (1 ሳሙ. 1:10, 11) ከጊዜ በኋላ ሐና የፀነሰች ሲሆን ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሳሙኤል አለችው። ሐና በተሳለችው መሠረት፣ ሳሙኤል ጡት ከጣለ በኋላ ወደ ማደሪያው ድንኳን ወሰደችው። ሐና የራሷን ጥቅም መሥዋዕት የማድረግ መንፈስ በማሳየቷ ይሖዋ ባርኳታል። ሐና አምስት ተጨማሪ ልጆችን በማግኘት የተካሰች ሲሆን ሳሙኤልም ነቢይና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች አንዱ የመሆን መብት አግኝቷል።—1 ሳሙ. 2:21

በዛሬው ጊዜ ያሉ ክርስቲያኖችም ልክ እንደ ሐና እና ሳሙኤል ሕይወታቸውን ለአምላክ ወስነው ፈጣሪያቸውን የማገልገል መብት ተሰጥቷቸዋል። በተጨማሪም ይሖዋን ለማምለክ ስንል የምንከፍለው ማንኛውም መሥዋዕት የተትረፈረፈ በረከት እንደሚያስገኝ ኢየሱስ ቃል ገብቷል።—ማር. 10:28-30

በመጀመሪያው መቶ ዘመን የኖረች ዶርቃ የምትባል አንዲት ክርስቲያን “መልካም በማድረግና ምጽዋት በመስጠት” ማለትም ሌሎችን ለመርዳት ስትል መሥዋዕት በመክፈል ትታወቅ ነበር። የሚያሳዝነው ግን ዶርቃ “ታማ ሞተች”፤ በዚህም ምክንያት ጉባኤው ከባድ ሐዘን ላይ ወደቀ። ደቀ መዛሙርቱ፣ ጴጥሮስ በአቅራቢያው እንዳለ ሲሰሙ ቶሎ እንዲመጣ አጥብቀው ለመኑት። ጴጥሮስ መጥቶ ዶርቃን ከሞት ሲያስነሳት ደቀ መዛሙርቱ ምን ያህል እንደተደሰቱ መገመት ይቻላል፤ ይህም አንድ ሐዋርያ የፈጸመው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተመዘገበ የመጀመሪያው ትንሣኤ ነው! (ሥራ 9:36-41) አምላክ የዶርቃን መሥዋዕት አልረሳም። (ዕብ. 6:10) ዶርቃ ስላሳየችው ልግስና የሚገልጸው ታሪክም ለእኛ ምሳሌ እንዲሆን በአምላክ ቃል ውስጥ ተመዝግቧል።

ሐዋርያው ጳውሎስም በተመሳሳይ ለሰዎች ትኩረት በመስጠትና ሌሎችን ለመርዳት ጊዜውን በማዋል ልግስና አሳይቷል፤ በዚህ ረገድ ጥሩ ምሳሌ ይሆነናል። ጳውሎስ በቆሮንቶስ ለነበሩ ክርስቲያን ወንድሞቹ ሲጽፍ “በእኔ በኩል ስለ እናንተ ያለኝን ሁሉ፣ ራሴንም ጭምር ብሰጥ እጅግ ደስ ይለኛል” ብሏል። (2 ቆሮ. 12:15) ለሌሎች ሲባል የራስን ጥቅም መሥዋዕት ማድረግ እርካታ የሚያመጣ ከመሆኑም ሌላ ይበልጥ አስፈላጊ የሆነውን ነገር ይኸውም የይሖዋን በረከትና ሞገስ እንደሚያስገኝ ጳውሎስ ከራሱ ተሞክሮ ተምሯል።—ሥራ 20:24, 35

ከዚህ በግልጽ ማየት እንደሚቻለው ከመንግሥቱ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ለማራመድና የእምነት አጋሮቻችንን ለመርዳት ጊዜያችንንና ጉልበታችንን ስናውል ይሖዋ ይደሰታል። የመንግሥቱን ስብከት ሥራ መደገፍ የምንችልባቸው ሌሎች መንገዶችስ አሉ? እንዴታ! በፍቅር ተገፋፍተን ከምናከናውናቸው ነገሮች በተጨማሪ በፈቃደኝነት መዋጮ በማድረግ አምላክን ማክበር እንችላለን። እነዚህ መዋጮዎች ዓለም አቀፉን የስብከት ሥራ ለማስፋፋት የሚውሉ ሲሆን ይህም ሚስዮናውያንንና በልዩ የሙሉ ጊዜ አገልግሎት የተሰማሩ ሌሎች ክርስቲያኖችን መደገፍን ይጨምራል። ከዚህም ሌላ ጽሑፎችንና ቪዲዮዎችን ለማዘጋጀትና ለመተርጎም፣ በአደጋ ጊዜ የእርዳታ ቁሳቁሶችን ለማቅረብ እንዲሁም አዳዲስ የስብሰባ አዳራሾችን ለመገንባት የሚውለው ገንዘብ የሚገኘው በፈቃደኝነት ከምናደርገው መዋጮ ነው። “ለጋስ ሰው [እንደሚባረክ]” እርግጠኞች መሆን እንችላለን። ከዚህም በላይ ያሉንን ውድ ነገሮች ለይሖዋ ስንሰጥ እሱን እናከብረዋለን።—ምሳሌ 3:9፤ 22:9

አንዳንዶች ለዓለም አቀፉ ሥራ መዋጮ የሚያደርጉባቸው መንገዶች

በሐዋርያው ጳውሎስ ዘመን እንደነበረው ሁሉ በዛሬው ጊዜም ብዙ ሰዎች፣ “ለዓለም አቀፉ ሥራ” ተብሎ የተለጠፈባቸው የጉባኤ ሣጥኖች ውስጥ የሚጨምሩት “የተወሰነ ገንዘብ” ያስቀምጣሉ ወይም ይመድባሉ። (1 ቆሮ. 16:2) ጉባኤዎች የተዋጣውን ገንዘብ፣ ባሉበት አገር ሥራውን ለሚመራው የይሖዋ ምሥክሮች ቢሮ በየወሩ ይልካሉ። አንተም በምትኖርበት አገር የይሖዋ ምሥክሮች ለሚጠቀሙበት ሕጋዊ ተቋም የገንዘብ መዋጮ በቀጥታ መላክ ትችላለህ። በምትኖርበት አገር የይሖዋ ምሥክሮች የሚጠቀሙበትን ዋነኛ ሕጋዊ ተቋም ስም ለማወቅ ቅርንጫፍ ቢሮውን ማነጋገር ትችላለህ። የቅርንጫፍ ቢሮው አድራሻ www.jw.org/am በተባለው ድረ ገጽ ላይ ይገኛል። ሁኔታዎች ከአገር አገር ቢለያዩም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ዓይነት መዋጮዎች በቀጥታ ለቢሮው መላክ ትችል ይሆናል፦

የገንዘብና የቁሳቁስ መዋጮዎች

  • በባንክ በኩል የሚደረግ ኤሌክትሮኒክ የገንዘብ ዝውውርን እንዲሁም ዴቢት ካርድ፣ ክሬዲት ካርድ ወይም ሞባይል ስልክ በመጠቀም የሚደረግ መዋጮን ያካትታል። በአንዳንድ ቅርንጫፍ ቢሮዎች jw.org የተሰኘውን ድረ ገጽ ወይም ለዚህ ዓላማ የተዘጋጀ ሌላ ድረ ገጽ መጠቀም ይቻላል።

  • ገንዘብ፣ ውድ ጌጣጌጦችን ወይም ሌሎች ውድ ንብረቶችን በመዋጮ መልክ መስጠት ይቻላል። የምትልከው ገንዘብ ወይም ዕቃ በመዋጮ መልክ የተሰጠ መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ አያይዘህ ላክ።

ተመላሽ ሊሆን የሚችል ገንዘብ የሚሰጥበት ዝግጅት

  • አንድ ሰው ገንዘብ ሊሰጥና ባስፈለገው ጊዜ ገንዘቡ እንዲመለስለት ሊጠይቅ ይችላል።

  • የሰጠኸው ገንዘብ ወደፊት እንዲመለስልህ የምትፈልግ መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ አያይዘህ ላክ።

በዕቅድ የሚደረግ ስጦታ

ገንዘብና ውድ ንብረቶች በስጦታ ከመለገስ በተጨማሪ በመላው ዓለም የሚካሄደውን የመንግሥቱን ሥራ መደገፍ የሚቻልባቸው ሌሎች መንገዶች አሉ። እነሱም ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል። መዋጮ ለመስጠት የምትጠቀምበት መንገድ ምንም ሆነ ምን፣ ከቀረቡት አማራጮች መካከል የትኞቹን መጠቀም እንደምትችል ለማወቅ አንተ በምትኖርበት አገር ለሚካሄደው ሥራ አመራር የሚሰጠውን ቅርንጫፍ ቢሮ አስቀድመህ አነጋግር። የየአገሩ ሕጋዊ አሠራሮችና የቀረጥ ደንቦች የተለያዩ ሊሆኑ ስለሚችሉ መዋጮ የምታደርግበትን የተሻለ መንገድ ከመምረጥህ በፊት ከቀረጥና ከሕግ ጋር በተያያዘ ብቃት ያለው ባለሙያ ማማከርህ በጣም አስፈላጊ ነው።

ኢንሹራንስ እና የጡረታ አበል፦ በምትኖርበት አገር ውስጥ የይሖዋ ምሥክሮች የሚጠቀሙበት ሕጋዊ ተቋም፣ የሕይወት ኢንሹራንስ ፖሊሲ ወይም የጡረታ ክፍያ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ ትችላለህ።

የባንክ ሒሳብ፦ የአገሩ የባንክ ደንብ በሚፈቅደው መሠረት የባንክ ሒሳቦችን በሞት ጊዜ፣ የይሖዋ ምሥክሮች ለሚጠቀሙበት ሕጋዊ ተቋም እንዲከፈል መስጠት ይቻላል።

አክሲዮኖችና ቦንዶች፦ አክሲዮኖችንና ቦንዶችን በስጦታ መልክ ማበርከት ወይም ደግሞ ግለሰቡ ሲሞት የይሖዋ ምሥክሮች ለሚጠቀሙበት ሕጋዊ ተቋም እንዲሰጥ ማድረግ ይቻላል።

የማይንቀሳቀስ ንብረት፦ የይሖዋ ምሥክሮች ለሚጠቀሙበት ሕጋዊ ተቋም፣ ሊሸጥ ሊለወጥ የሚችል የማይንቀሳቀስ ንብረት በስጦታ መስጠት ይቻላል፤ ስጦታው መኖሪያ ቤት በሚሆንበት ጊዜ ደግሞ ባለ ንብረቱ በሕይወት እስካለ ድረስ ሲጠቀምበት ቆይቶ ከዚያ በኋላ ማውረስ ይችላል።

ኑዛዜዎችና አደራዎች፦ ንብረት ወይም ገንዘብ በሕግ ፊት ተቀባይነት ባለው ኑዛዜ አማካኝነት፣ የይሖዋ ምሥክሮች ለሚጠቀሙበት ሕጋዊ ተቋም በውርስ ሊሰጥ ወይም ሕጋዊ ተቋሙ በአደራ የተሰጠው ንብረት ተጠቃሚ እንደሆነ ሊገለጽ ይችላል። ይህ ዝግጅት ከቀረጥ ጋር የተያያዙ አንዳንድ ጥቅሞች ሊያስገኝ ይችላል።

“በዕቅድ የሚደረግ ስጦታ” የሚለው አገላለጽ፣ እነዚህን የመሳሰሉ መዋጮዎች የሚያደርገው ግለሰብ ዕቅድ ማውጣት እንደሚያስፈልገው ይጠቁማል። የይሖዋ ምሥክሮችን ዓለም አቀፍ ሥራ በዕቅድ በሚደረግ ስጦታ መደገፍ ለሚፈልጉ ግለሰቦች ጉዳዩን ይበልጥ ግልጽ ለማድረግ ሲባል ዓለም አቀፉን የመንግሥቱን ስብከት ሥራ ለመደገፍ በዕቅድ የሚደረግ ስጦታ የሚል ብሮሹር ተዘጋጅቷል። በእንግሊዝኛና በስፓንኛ የተዘጋጀው የዚህ ብሮሹር ዓላማ፣ ሰዎች ስጦታ መስጠት ወይም በሚሞቱበት ጊዜ በኑዛዜ ውርስ መተው የሚችሉባቸውን የተለያዩ መንገዶች አስመልክቶ መረጃ ማቅረብ ነው። በዚህ ብሮሹር ላይ የቀረበው መረጃ አንተ በምትኖርበት አገር ከሚሠራባቸው የቀረጥ ወይም ሌሎች ጉዳዮችን የሚመለከቱ ሕጎች ጋር ሙሉ በሙሉ ላይጣጣም ይችላል። ስጦታ ማድረግ የሚቻልባቸውን እንዲህ ያሉ ዘዴዎች በመጠቀም ብዙዎች በዓለም ዙሪያ የምናከናውነውን ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴና ሰብዓዊ እርዳታ መደገፍ ከመቻላቸውም በላይ ከቀረጥ ጋር በተያያዘ የተሻለ ጥቅም ማግኘት ችለዋል። ይህ ብሮሹር አንተ ባለህበት አገር ውስጥ የሚገኝ ከሆነ የጉባኤህን ጸሐፊ በመጠየቅ ማግኘት ትችላለህ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በjw.org/am መነሻ ገጽ ግርጌ ላይ የሚገኘውን “ለዓለም አቀፉ ሥራችን የገንዘብ መዋጮ ለማድረግ” የሚለውን ሊንክ መጠቀም አሊያም ቅርንጫፍ ቢሮውን ማነጋገር ትችላለህ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ