የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp18 ቁጥር 1 ገጽ 12-13
  • 3 ችግሮችን ለመቋቋም የሚረዳ ምክር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • 3 ችግሮችን ለመቋቋም የሚረዳ ምክር
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2018
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሥር የሰደደ ሕመም
  • ሐዘን
  • መጸለይህ ምን ጥቅም ያስገኝልሃል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
  • ጸሎት እንዴት ሊጠቅምህ ይችላል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • አንዳንዶች ለጥያቄዎቻቸው መልስ ያገኙት እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
  • እንደምትወጂያቸው ንገሪያቸው
    የይሖዋ ምሥክሮች ተሞክሮዎች
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2018
wp18 ቁጥር 1 ገጽ 12-13
አንዲት ሴት መቃብር ቦታ ጋ ሄዳ ስታለቅስ፤ በተሽከርካሪ ወንበር የምትጠቀም አንዲት ሴት የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክት ስታዳምጥ

3 ችግሮችን ለመቋቋም የሚረዳ ምክር

በአሁኑ ጊዜ ሊወገዱ አሊያም መፍትሔ ሊገኝላቸው የማይችሉ ችግሮች አሉ። ለምሳሌ ያህል፣ የምትወደውን ሰው በሞት አጥተህ ይሆናል፤ ወይም ደግሞ ሥር የሰደደ ሕመም ሊኖርብህ ይችላል፤ እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ካጋጠመህ ሥቃይህን ለመቋቋም የሚረዱህ መንገዶች ከመፈለግ ውጭ ሌላ ምርጫ ላይኖርህ ይችላል። ታዲያ እንዲህ ባሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስ ሊረዳህ ይችላል?

ሥር የሰደደ ሕመም

ሮዝ “በዘር የሚተላለፍ ሕመም አለብኝ፤ ሕመሙ ከባድና ፋታ የማይሰጥ ሥቃይ ስለሚያስከትል ሕይወቴን ምስቅልቅል አድርጎብኛል” ብላለች። ሮዝ በጣም ከሚረብሿት ነገሮች አንዱ፣ መጽሐፍ ቅዱስንና መንፈሳዊ ነገሮችን ስታጠና አንዳንድ ጊዜ ትኩረቷን መሰብሰብ አለመቻሏ ነው። በማቴዎስ 19:26 ላይ የሚገኘው ኢየሱስ የተናገረው ሐሳብ በእጅጉ ረድቷታል፤ ጥቅሱ “በአምላክ ዘንድ . . . ሁሉ ነገር ይቻላል” ይላል። ሮዝ ማጥናት የሚቻልባቸው የተለያዩ መንገዶች እንዳሉ ተገንዝባለች። ከሥቃይዋ የተነሳ ማንበብ አዳጋች ሲሆንባት በድምፅ ተቀርጾ የተዘጋጀ የመጽሐፍ ቅዱስና የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎችን ንባብ ማዳመጥ ጀመረች።a ሮዝ “እንዲህ ዓይነት አማራጭ ባይኖረኝ ኖሮ መንፈሳዊነቴን እንዴት መጠበቅ እንደምችል አላውቅም” ብላለች።

ሮዝ በአንድ ወቅት ታከናውናቸው የነበሩ ነገሮችን ማከናወን ባለመቻሏ በምታዝንበት ጊዜ በ2 ቆሮንቶስ 8:12 ላይ የሚገኘው ሐሳብ ያጽናናታል፤ ጥቅሱ “ለመስጠት ፈቃደኝነቱ ካለ ስጦታው ይበልጥ ተቀባይነት የሚኖረው አንድ ሰው ባለው መጠን ሲሰጥ እንጂ በሌለው መጠን ሲሰጥ አይደለም” ይላል። ይህ ጥቅስ አምላክ በምታደርገው ነገር እንደሚደሰት እንድታስታውስ ይረዳታል፤ ምክንያቱም ሮዝ አቅሟ የፈቀደውን ነገር ሁሉ እያደረገች ነው።

ሐዘን

ቀደም ሲል የተጠቀሰችው ዴልፊን የ18 ዓመት ወጣት የነበረችውን ልጇን በሞት ባጣችበት ወቅት የተሰማትን ስትገልጽ እንዲህ ብላለች፦ “ልጄ ስትሞት ሐዘኑ በጣም ስለከበደኝ በሕይወት መቀጠል የምችል አልመሰለኝም ነበር። ከዚያ በኋላ ሁሉም ነገር እንደ ድሮው ሊሆንልኝ አልቻለም።” ይሁንና ዴልፊን በመዝሙር 94:19 ላይ የሚገኘው ሐሳብ በጣም አጽናንቷታል፤ መዝሙራዊው፣ አምላክ ያደረገለትን እርዳታ አስመልክቶ ሲናገር “በጭንቀት በተዋጥኩ ጊዜ፣ አጽናናኸኝ፤ ደግሞም አረጋጋኸኝ” ብሎ ነበር። ዴልፊን “ሥቃዬን ለማስታገሥ በሚረዱኝ ነገሮች መጠመድ እንድችል ወደ ይሖዋ ጸለይኩ” ብላለች።

ከዚያም በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በመካፈል ራሷን በሥራ አስጠመደች። ዴልፊን ራሷን የምትመለከተው፣ ልጆች ሥዕሎችን ቀለም ለመቀባት እንደሚጠቀሙባቸው እርሳሶች አድርጋ እንደሆነ ትናገራለች፤ የተሰበሩት እርሳሶችም ቢሆኑ ሥዕሎችን ለማቅለም ያገለግላሉ። በተመሳሳይ እሷም እንደተሰበረች ቢሰማትም እንኳ ሌሎችን መርዳት እንደምትችል ተገነዘበች። እንዲህ በማለት ታስታውሳለች፦ “የአምላክን ቃል የማስጠናቸውን ሰዎች ለማጽናናት የመጽሐፍ ቅዱስን መመሪያዎችና በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ሐሳቦችን ስጠቀም እኔም እበረታታለሁ፤ ይሖዋ እኔን የሚያጽናናኝና የሚያረጋጋኝ በዚህ መንገድ እንደሆነ ማስተዋል ችያለሁ።” በተጨማሪም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጹ ከባድ ሐዘን የደረሰባቸው ሰዎችን ስም ዝርዝር ጻፈች። ዴልፊን “ሁሉም የጸሎት ሰዎች ነበሩ” ብላለች። አክላም “መጽሐፍ ቅዱስን ካላነበብን ከሐዘናችን መጽናናት እንደማንችል” መገንዘቧን ገልጻለች።

ዴልፊን መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናቷ ያስገኘላት ሌላም ጥቅም አለ፤ ያለፈውን እያሰበች ከመቆዘም ይልቅ በወደፊቱ ጊዜ ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለባት ተገንዝባለች። በሐዋርያት ሥራ 24:15 ላይ የሰፈረው “ጻድቃንም ሆኑ ዓመፀኞች ከሞት እንደሚነሱ” የሚገልጸው ተስፋ አጽናንቷታል። ዴልፊን፣ ይሖዋ ልጇን ከሞት እንደሚያስነሳላት ምን ያህል ትተማመናለች? እንዲህ ብላለች፦ “ወደፊት ልጄ ከሞት ተነስታ አብረን ስንሆን ይታየኛል። ከልጄ ጋር የምንገናኝበት ቀን ተቀጥሯል፤ ቀጠሯችን በይሖዋ የቀን መቁጠሪያ ላይ የሰፈረ ያህል ነው። ልጄ በተወለደችበት ቀን የነበረው ሁኔታ ከአእምሮዬ እንደማይጠፋ ሁሉ ወደፊት ከእሷ ጋር በአትክልት ቦታችን ውስጥ የምናሳልፈው ጊዜም ቁልጭ ብሎ ይታየኛል።”

a እንደዚህ ያሉ በድምፅ የተቀረጹ ነገሮች jw.org በተባለው ድረ ገጽ ላይ ይገኛሉ።

በጣም አስቸጋሪ በሆኑ ጊዜያትም ጭምር መጽሐፍ ቅዱስ ሊያጽናናህ ይችላል

አምላክ የሚረዳን እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ጥያቄ ግልጽ መልስ ይሰጣል። እንዲህ ይላል፦ “ይሖዋ ለሚጠሩት ሁሉ፣ በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው። የሚፈሩትን ሰዎች ፍላጎት ያረካል፤ እርዳታ ለማግኘት የሚያሰሙትንም ጩኸት ይሰማል፤ ደግሞም ይታደጋቸዋል።” (መዝሙር 145:18, 19) ይህን ማወቅ በጣም አስደሳች እንደሆነ ጥያቄ የለውም። ይሁንና አምላክ፣ እሱ እንዲመራቸው ከልባቸው የሚፈልጉ ሰዎች ለሚያቀርቡት ጸሎት መልስ የሚሰጠው እንዴት ነው?

ብርታት በመስጠት፦

ብዙውን ጊዜ ችግሮች ተስፋ እንድንቆርጥ እንዲሁም እንድንዝልና በመንፈሳዊ እንድንዳከም ያደርጉናል። (ምሳሌ 24:10) ይሁን እንጂ ይሖዋ “ለደከመው ኃይል፣ ጉልበት ለሌላቸውም የተሟላ ብርታት ይሰጣል።” (ኢሳይያስ 40:29) ከባድ ፈተናዎችን በጽናት የተቋቋመው ሐዋርያው ጳውሎስ “ኃይልን በሚሰጠኝ በእሱ አማካኝነት ለሁሉም ነገር የሚሆን ብርታት አለኝ” በማለት ተናግሯል። (ፊልጵስዩስ 4:13) ለጳውሎስ ኃይል የሰጠው የአምላክ ቅዱስ መንፈስ ነው። አንተም አምላክ መንፈስ ቅዱስን እንዲሰጥህ መጠየቅ ትችላለህ።—ሉቃስ 11:13

ጥበብ በመስጠት፦

የመጽሐፍ ቅዱስን ምክር ለመረዳትና በሥራ ላይ ለማዋል እርዳታ የሚያስፈልግህ ቢሆንስ? ደቀ መዝሙሩ ያዕቆብ “ከእናንተ መካከል ጥበብ የጎደለው ሰው ካለ አምላክን ያለማሰለስ ይለምን፤ አምላክ ማንንም ሳይነቅፍ ለሁሉም በልግስና ይሰጣልና፤ ይህም ሰው ይሰጠዋል” ሲል ጽፏል። (ያዕቆብ 1:5) መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብና የሚያስተምራቸውን ነገሮች በሥራ ላይ በማዋል ከጸሎትህ ጋር የሚስማማ እርምጃ መውሰድ ትችላለህ። (ያዕቆብ 1:23-25) እንዲህ ስታደርግ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠው ምክር ጥበብ የተሞላበት መሆኑን በገዛ ሕይወትህ ትመለከታለህ።

ሰላም በመስጠት፦

በጭንቀት በምትዋጥበት ጊዜም እንኳ ይሖዋ እንድትረጋጋ ሊረዳህ ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “ስለ ምንም ነገር አትጨነቁ፤ ከዚህ ይልቅ ስለ ሁሉም ነገር በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር ልመናችሁን ለአምላክ አቅርቡ፤ ከመረዳት ችሎታ ሁሉ በላይ የሆነው የአምላክ ሰላም በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት ልባችሁንና አእምሯችሁን ይጠብቃል።” (ፊልጵስዩስ 4:6, 7) አንተስ ይሖዋ ሰላም እንዲሰጥህ ለምን አትለምነውም?

ይሁንና ችግሮችህ ወዲያውኑ መፍትሔ ባያገኙስ? አምላክ እንደተወህ አድርገህ አታስብ። ችግሮችህ ቶሎ ባይፈቱም እንኳ አምላክ ለመጽናት የሚያስችልህን ድፍረትና ብርታት ሊሰጥህ ይችላል። (1 ቆሮንቶስ 10:13) በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ ችግሮቻችን ሁሉ ለዘለቄታው መፍትሔ የሚያገኙበት ጊዜ እንደሚመጣ ተስፋ ይሰጣል!

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ