ከጉባኤያችን የመጽሐፍ ጥናት መሪ ጋር መተባበር
1 የጉባኤ መጽሐፍ ጥናት የምሥራቹ አገልጋዮች የመሆን ችሎታችንን በማዳበር በኩል ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። ቡድኖቹ ትንንሽ እንዲሆኑ የተደረጉት ሆን ተብሎ ነው። ይኸውም መጽሐፍ ቅዱስና ከድርጅቱ ጽሑፎች አንዱ በሚጠናበት ጊዜ ጥናቱ ሞቅ ያለ የቤተሰብ ዓይነት መንፈስ እንዲኖረው ለማበረታታት ታስቦ ነው። እነዚህ ትንንሽ ቡድኖች በመስክ አገልግሎቱ ይበልጥ ውጤታማ እንድንሆን ለማሰልጠን የሚረዱ ተስማሚ ሁኔታዎችን ይፈጥራሉ። ለግለሰቦች በግል የሚሰጥ ማበረታቻና ትኩረት በጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት ዝግጅት በኩል በቀላሉ ለማግኘት ይቻላል። ከመጽሐፍ ጥናት መሪው ጋር ሙሉ በሙሉ ለመተባበርና ከእነዚህ መልካም ዝግጅቶች ልንጠቀም የምንችለው እንዴት ነው?
2 በመስክ አገልግሎቱ በቅንዓት መካፈል፦ በጣም አስፈላጊ ከሆኑት የመጽሐፍ ጥናት መሪው ኃላፊነቶች መካከል እያንዳንዱ የቡድኑ አባል በአገልግሎቱ በቅንዓት ተካፋይ እንዲሆን መርዳት ይገኝበታል። በዚህ ረገድ አገልግሎታችን የተባለው መጽሐፍ በገጽ 24 ላይ “በመስክ አገልግሎት የሚያሳየው አዘውታሪነት፣ ቅንዓትና የሚያነቃቃ ስሜት በአስፋፊዎቹ ላይ ይንጸባረቃል” በማለት ያስታውሰናል። አንዳንድ ጊዜ የመጽሐፍ ጥናት መሪው ከራሱ ቤተሰብ አባላት ጋር አገልግሎት ይሄድ ይሆናል፤ ነገር ግን ሁኔታዎቹ በፈቀዱለት መጠን ከሌሎች ጋር አንድ ላይ ሆኖ በልዩ ልዩ የአገልግሎት ዘርፎች መሳተፍ ደስ ይለዋል። ለመስክ አገልግሎት በሚደረጉት ስብሰባዎች አዘውትረህ ድጋፍ ልትሰጥ ትችላለህን? እንዲህ ማድረግህ የመጽሐፍ ጥናቱን መሪና ሌሎች አስፋፊዎችን በጣም ያስደስታል።
3 በስብከቱ ሥራ ውስጥ ሁሉም ቀናተኛ ተሳትፎ ይኖራቸው ዘንድ የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎች ምቹ በሆኑ ቦታዎች ይደረጋሉ። በአካባቢው ያሉትን ሁኔታዎች አመዛዝኖ እያንዳንዱ ቡድን አገልግሎቱን ቀደም ብሎ ለመጀመር ይፈልግ ይሆናል። ብዙ አስፋፊዎችና አቅኚዎች ቅዳሜና እሁድ ከሰዓት በኋላ ሲያገለግሉ ጥሩ ውጤት አግኝተዋል።
4 በአንዳንድ የአገልግሎቱ ዘርፎች እርዳታ ማግኘት ትፈልጋለህን? ምናልባት የመጽሐፍ ጥናትህ መሪ በቡድኑ ውስጥ ያሉ ችሎታ ካላቸው አስፋፊዎች አንዱ አብሮህ እንዲሠራ ዝግጅት ሊያደርግ ይችል ይሆናል። በወሩ መጨረሻ ላይ የመስክ አገልግሎት ሪፖርትህን ወዲያውኑ መመለስህን አረጋግጥ። የመጽሐፍ ጥናት መሪውም ሆነ ጸሐፊው በዚህ በኩል ትብብርህን ይፈልጋሉ። — ከሉቃስ 16:10 ጋር አወዳድር።
5 የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ቡድኑን በሚጎበኝበት ጊዜ፦ አስፋፊዎች በመስክ አገልግሎቱ የበለጠ እንዲሳተፉና ተሳትፎአቸውም ትርጉም ያለው እንዲሆን ለማበረታታት ብዙውን ጊዜ የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በየወሩ አንድ የመጽሐፍ ጥናት ቡድን ይጎበኛል። በመጽሐፍ ጥናቱ መጨረሻ ላይ የሚያቀርበው የ15 ደቂቃ ንግግር ቡድኑ በስብከቱ ሥራ የተለያዩ ዘርፎች መሻሻል ለማድረግ እንዲችል የሚረዱትን የተለዩ ነጥቦች የሚያሳይ ስለሆነ በጥሞና አዳምጠው። የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ቅዳሜና እሁድ ከመጽሐፍ ጥናቱ ቡድን የተለያዩ አባሎች ጋር ለመሥራት ዝግጁ ነው። ከተሞክሮውና በመስክ አገልግሎት ካለው ችሎታ ለመጠቀም ትችል ዘንድ ከዚህ ልዩ ዝግጅት ጥቅም ማግኘትህን አረጋግጥ።
6 ተባባሪ በመሆናችንና አነስተኛ ልምድ ያላቸውን ለመርዳት ባለን ፈቃደኝነት በኩል በግላችን በምናሳየው ምሳሌ “ለሰው ሁሉ ይልቁንም ለሃይማኖት ቤተ ሰዎች መልካም” እናደርጋለን። ይህም በጉባኤው መጽሐፍ ጥናት ውስጥ ሞቅ ያለ የወዳጅነት መንፈስ ለመፍጠር ይረዳል። — ገላ. 6:10