“ወቅታዊ መልዕክት
በጥር 1993 የመንግሥት አገልግሎታችን እትም ላይ በማስታወቂያ እንደተነገረው በዚህ ዓመት ለመታሰቢያው በዓል ሰሞን የተዘጋጀው ልዩ የሕዝብ ንግግር በብዙ ጉባኤዎች መጋቢት 28 ቀን ይቀርባል። ወቅታዊ መልዕክቱ “‘የአምላክ ሥራዎች’ — እንዴት ትመለከቷቸዋላችሁ?” የሚል ርዕስ አለው። ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች ሁሉ ለመጋበዝ ልዩ ጥረት መደረግ ይኖርበታል። በዚህ የሕዝብ ንግግር ላይ የተገኙ ሁሉ ሚያዝያ 6 በሚደረገው የመታሰቢያ በዓል ላይ እንዲገኙ ማበረታቻ ሊሰጣቸው ይቻላል።