ቲኦክራቲካዊ ዜናዎች
ሥራችን በቅርቡ ሕጋዊ እውቅና ባገኘባቸው በሚከተሉት አገሮች ውስጥ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ረገድ በኅዳር ወር የነበረው ከፍተኛ እንቅስቃሴ ሪፖርት ተደርጓል:-
አልባንያ፦ በጠቅላላው 99 የሆኑት አስፋፊዎች 210 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን እንደመሩ ሪፖርት አድርገዋል።
የቦልቲክ አገሮች፦ እነዚህ አገሮች በጠቅላላው 2,199 አስፋፊዎችና 4,632 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ሪፖርት አድርገዋል።
ቡልጋርያ፦ 296 አስፋፊዎች 657 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ሪፖርት አድርገዋል።
ከአፍሪካም በርካታ የሚያበረታቱ ሪፖርቶች መጥተዋል:-
የማዕከላዊው አፍሪካ ሪፑብሊክ፦ በጥቅምት ወር 1,600 የሆነ አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ላይ ደርሰዋል፤ እንዲሁም 2,966 የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ሪፖርት አድርገዋል።
ቻድ፦ 345 የሚሆኑት አስፋፊዎች በጥቅምት ወር በስድስት ቦታዎች ባደረጓቸው የልዩ ስብሰባ ቀናት ፕሮግራሞች ላይ 654 ተሰብሳቢዎች ተገኝተዋል።
ሩዋንዳ፦ 1,762 አስፋፊዎች በኅዳር ወር 6,270 የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን እንደመሩ ሪፖርት አድርገዋል።
እነዚህ ሪፖርቶች አንድ ላይ ተዳምረው ይሖዋ የስብከቱን ሥራ በዘመናችን እንደሚያፋጥነው የሰጠውን ተስፋ እየፈጸመ ለመሆኑ ከፍተኛ ማረጋገጫ ይሰጡናል። — ኢሳ. 60:22