አከትራክቶች ጋር አያይዛችሁ ሌሎች ጽሑፎችን አበርክቱ
1 በዛሬው ጊዜ ከሚታተሙት መጽሔቶች ሁሉ ቅን የሆኑ አንባቢዎች ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን መንገድ እንዲያገኙ ሊረዷቸው የሚችሉት መጽሔቶች መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! ብቻ ናቸው። በሚያዝያና በግንቦት ከሰዎች ጋር ስትነጋገሩ አንዳንዶች ለመንግሥቱ መልእክት የማያሻማ ፍላጎት ያሳዩ ይሆናል። በዚህ ጊዜ ትኩረታቸውን በቀጥታ በቅርብ ቀን ወደወጡት መጽሔቶች ወይም ከማኅበሩ ባለ ቀለም ብሮሹሮች ወደ አንዱ ዘወር ልታደርጉት ትችላላችሁ። ሌሎች ደግሞ በመጀመሪያ የሚያሳዩት ፍላጎት አነስተኛ ሊሆን ይችላል። እንዲህ በሚሆንበት ጊዜ በመጀመሪያ ከአንድ ትራክት ላይ አንድ ወይም ሁለት ነጥቦች አንስታችሁ ልታወያዩአቸው ትችላላችሁ፤ ከዚያም የቤቱ ባለቤት ተጨማሪ ፍላጎት ካሳየ ከትራክቱ ጋር አያይዛችሁ በወቅቱ ከምታበረክቷቸው ጽሑፎች አንዱን መጽሔት ወይም ብሮሹር አበርክቱለት።
2 እንዲህ ልትሉ ትችላላችሁ፦
◼ “በዛሬው ጊዜ ባለው ዓለም ውስጥ ከመፍትሔዎች ይልቅ ችግሮቹ በዝተው እንደሚገኙ አብዛኞቹ ሰዎች ይስማማሉ። በአሁኑ ጊዜ ካሉት አሳሳቢ ችግሮች ብዙዎቹ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አስቀድሞ የተነገሩ መሆናቸውን ያውቃሉ?” ከዚያ ይህ ዓለም ከመጥፋት ይተርፍ ይሆንን? የተባለውን ትራክት ገጽ 4 እና 5 ላይ ትገልጡና ከችግሮቹ አንዳንዶቹን ታወያዩታላችሁ።
3 የምታበረክቱት የመጋቢት 1ን መጠበቂያ ግንብ ከሆነና የቤቱ ባለቤት ከትራክቱ ባነበባችሁለት ነጥብ ላይ ፍላጎት ካሳየ “አምላክ የሚሰጠውን ማስጠንቀቂያ ሰምተህ እርምጃ ትወስዳለህን?” ወደሚለው ርዕሰ ትምህርት ወስዳችሁ የምልክቱ ሌሎች ዘርፎች ወይም ገጽታዎች እንዲሁም ማስጠንቀቂያውን ሰምተው እርምጃ ለሚወስዱ ሰዎች የወደፊቱ ጊዜ ምን እንደሚያመጣላቸው ልትገልጹለት ትችላላችሁ። መጽሔቱን አበርክቱለትና በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ውይይት ለማድረግ አመቺ በሚሆንበት ጊዜ ተመልሳችሁ ሂዱ።
4 ጉባኤያችሁ የሚያዝያ 8 “ንቁ!” መጽሔት ሲመጣለት በዚህ ርዕሰ ትምህርት አንቀጽ 2 ላይ በወጣው መግቢያ ከተጠቀማችሁ በኋላ እንዲህ በማለት ልትጨምሩ ትችላላችሁ፦
◼ “ብዙ ሰዎች ሃይማኖትና ፖለቲካ ችግሮቻችንን ሊያቃልሉልን የመቻላቸው ጉዳይ አጠራጣሪ ሆኖባቸዋል። ይሁን እንጂ ምናልባት ሳይንስ ለችግሮቻችን መልስ ይኖረው ይሆናል ብለው ያስባሉ።” ከዚያም “ሳይንስ የ21ኛውን መቶ ዘመን ፈታኝ ሁኔታዎች መቋቋም ችሏልን?” ከሚለው ርዕስ ውስጥ ተስማሚ የሆነ ነጥብ ልታነቡለት ትችላላችሁ። ይህ ርዕሰ ትምህርት ለብዙ ወጣቶች በተለይም ለተማሪዎች ተስማሚ ይመስላል።
5 “እነሆ!” የተባለውን ብሮሹር ስታበረክቱ ለየት ያለ አቀራረብ ልትጠቀሙ ትችላላችሁ፦
◼ “ብዙ ሰዎች በምንሞትበት ጊዜ ምን እንሆን ይሆን ብለው ያስባሉ። አንዳንዶች ወደ ሰማይ ወይም ወደ ሲኦል እንሄዳለን ይላሉ፤ ሌሎች ደግሞ ስለ ነገሩ እርግጠኞች አይደሉም። የመጽሐፍ ቅዱስ መልስ ግን የሚያስደንቅም የሚያጽናናም ነው።” ከዚያ የሞቱብን ዘመዶቻችንና ወዳጆቻችን ያላቸው ተስፋ ምንድን ነው? የሚለውን ትራክት አስተዋውቃችሁ ከትራክቱ ከፊሉን አወያዩት። ከዚያ በኋላ የቤቱ ባለቤት በትራክቱ ፍላጎት ካሳየ በብሮሹሩ ላይ በገጽ 16 እና 17 ያለውን እያሳያችሁ አወያዩት።
6 ሰላም በሰፈነበት አዲስ ዓለም ውስጥ የሚገኝ ሕይወት በተባለው ትራክት ተጠቅማችሁ በምትመሰክሩበት ጊዜ በትራክቱ የመጀመሪያ አንቀጽ ውስጥ የቀረቡትን ሁለቱን ጥያቄዎች ልትጠይቁት ትችላላችሁ። ለጥያቄዎቹ መልስ ከሰጠ በኋላ ትኩረቱን በገጽ 3 ላይ ወዳለው የመጀመሪያው አንቀጽ አዙሩት። ይህም ሰላም የሰፈነበት አዲስ ዓለም የሚመጣበትን መንገድ ይጠቁማል። የቤቱ ባለቤት ፍላጎት ካሳየ የመጋቢት 1ን መጠበቂያ ግንብ በዚህ ርዕሰ ትምህርት አንቀጽ 3 ላይ በቀረበው ሐሳብ መሠረት ተጠቀሙበት።
7 አዲስ አስፋፊ ከሆንክ ቀላል አቀራረብን እንደምትወድ አያጠራጥርም። ታዲያ ይህ ዓለም ከመጥፋት ይተርፍ ይሆንን? የምትለውን ትራክት ወስደህ ከላይ በአንቀጽ 2 ላይ የቀረቡትን ሐሳቦች ለምን አትከተልም?
8 የመዳንን መልእክት ወደ ሰዎች ቤት የመውሰድ ክብር አግኝተናል። ‘የሚገባቸውን ሰዎች’ በምንፈልግበት ጊዜ በትራክቶቻችን በሚገባ እንጠቀምባቸው፤ እንዲሁም ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች በምናገኝበት ጊዜ ከትራክቶቹ ጋር አያይዘን ሌሎች ጽሑፎችን እናበርክት። — ማቴ. 10:13