ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች
ካምቦዲያ፦ ለሥራችን ማካሄጃ የሚሆን ቢሮ ለመሥራትና ሚስዮናውያንም ወደ አገሪቱ ለመግባት የሚችሉበትን መንገድ የሚከፍት ሕጋዊ ሰነድ የካቲት 8 ቀን 1993 አግኝተናል። ከ25 ከሚበልጡ ዓመታት በኋላ የምሥራቹ በካምቦዲያ ውስጥ እንደገና በይፋ እየተሰበከ በመሆኑ በጣም ደስ ብሎናል።
ቆጵሮስ፦ በመጋቢት 1,462 የደረሰ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር የነበራቸው ከመሆኑም ሌላ በሰዓት፣ በተመላልሶና በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችም ረገድ አዲስ ከፍተኛ ቁጥር እንደነበራቸው ቅርንጫፍ ቢሮው ሪፖርት አድርጓል።
ላይቤሪያ፦ በመጋቢት ወንድሞች ቅርንጫፍ ቢሮውን በሚያዋስነው የማኅበሩ ንብረት የሆነ ባዶ መሬት ላይ “ብርሃን አብሪዎች” የተባለውን የወረዳ ስብሰባቸውን አድርገዋል። ከፍተኛው የተሰብሳቢዎች ቁጥር 2,711 የነበረ ሲሆን 78 ተጠምቀዋል።
ጃፓን፦ በመጋቢት የነበራቸው አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር 177,591 ነበር።
ፊሊፒንስ፦ በመጋቢት 115,044 የሆነ አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ላይ ደርሰዋል።