ቲኦክራቲካዊ ዜናዎች
አልባኒያ፦ ከታህሣሥ 1991 እስከ ታህሣሥ 1992 ባለው ጊዜ ውስጥ የአስፋፊዎች ቁጥር ከ24 ወደ 107 አድጓል። በዚያው ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ቁጥር ከ4 ወደ 221 ከፍ ብሏል።
የመካከለኛው አፍሪካ ሪፑብሊክ፦ ጥ ር 20, 1993 የአገሩ መንግሥት ታግዶ የነበረው የይሖዋ ምሥክሮች ሥራ ሙሉ በሙሉ እንዲቀጥል የሚፈቅድ ድንጋጌ አውጥቷል። በዚህ አገር የሚገኙት ወንድሞች በአሁኑ ጊዜ የመንግሥት አዳራሾቻቸውን ሊጠቀሙባቸው በመቻላቸውና የ“ብርሃን አብሪዎች”ን የወረዳ ስብሰባ በይፋ በማድረጋቸው ተደስተዋል። በተካሄዱት ስድስት ስብሰባዎች በጠቅላላው 4,739 ተሰብሳቢዎች ሲገኙ 121 ደግሞ ተጠምቀዋል።
ኢትዮጵያ፦ የ1993 የክልል ስብሰባ ፕሮግራም ሲጠናቀቅ በጠቅላላው 6,151 ተሰብሳቢዎች ሲገኙ 60 ተጠምቀዋል።