ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች
አንጎላ፦ በታኅሣሥ ወር በጠቅላላው የተበረከቱት መጽሔቶች ከ10,000 በላይ ነበሩ። ይህም እስካሁን ከተበረከቱት ሁሉ ይበልጣል። 21,965 የሚሆኑት አስፋፊዎች 60,691 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን እየመሩ ነው።
ላትቪያ፦ በላትቪያ ሥራው ወደፊት በመግፋት ላይ ነው። ባለፈው የታኅሣሥ ወር ላይ 577 የደረሰ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ሪፖርት አድርገዋል።
የሚከተሉት ጉባኤዎች በቅርቡ የመንግሥት አዳራሽ አስመርቀዋል:- አቃቂ፣ በኢትዮጵያ፤ ማቻሜ፣ በታንዛኒያ እንዲሁም ካምፓላ ኢስት፣ በኡ ጋንዳ።